Popular Posts

Thursday, May 3, 2018

በምድር ላይ ያለንበት ዋነኛው አላማ

ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20
ብዙ ጊዜ የሚባል አባባል አለ፡፡ በምድር ላይ የምንፈፅመው የወንጌል አላማ ባይኖረው ልክ በክርስቶስ እንደዳንን እግዚአብሄር ወደ ራሱ ይሰበስበን ነበር፡፡ እውነት ነው ከምንም ነገር በላይ በምድር ላይ የወንጌል አደራ አለብን፡፡ በምድር ያለነው እግዚአብሄርን በሚመስል ኑሯችን ለአለም የመዳንን መንገድ ለማሳየት ነው፡፡
እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር። ሐዋርያት ሥራ 16፡17
በምድር ያለንው ብርሃን ልንሆን ነው፡፡ በምድር ያለነው የምድር ጨው ለመሆን ነው፡፡  
እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ማቴዎስ 5፡13-14
በምድር ያለነው በስራችን የእግዚአብሄርን መልካምነት ለማንፀባረቅ ነው፡፡ በምድር ያለነው የእግዚአብሄርን መንግስት ለመግለጥ ነው፡፡
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡16
በየእለት ነፍሳችንን የምንክደው በኑሮና በቃል ወንጌልን ለመሰበክ ነው፡፡
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን፥ እርሱም የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌልን መመስከር በሃሴት እፈጽም ዘንድ፥ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፡፡ ሐዋሪያት ሥራ 20:24
በምድር ያለነው ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ ነው፡፡
ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18-19
በምድር ያለነው የክርስቶስ አምባሳደሮች በመሆን ነው፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20
በምድር ላይ ሌሎች ሌሎች የምናደርጋቸው አላማዎች ቢኖሩንም ወንጌልን ስንኖርና ስንሰብክ እግረ መንገዳችን የምናደርጋቸው ነገሮች እንጂ ዋና ነገሮች አይደሉም፡፡ በምድር ላይ ያለንበት ዋናው ምክኒያት ወንጌልን መስበክ ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment