ወንጌላችን
የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው። ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-4
ወንጌል ግልፅ ነው፡፡ ወንጌል ኢየሱስ ስለሰው
ልጆች ሃጢያት እንደሞተ እንደተቀረ በሶስተኛው ቀን ሞትን ደል አድርጎ ስለመነሳቱ ነው፡፡
ይህንን ለመረዳት የማያስቸግር ቀላል እውነት የማይረዱ
ሰዎች አሉ፡፡ ይህንን ቀላል እውነት ተረድተው ከመዳን ይልቅ በመቃወም ሳያውቁት ለጥፋት የተዘጋጁ ሰዎች አሉ፡፡
ሰይጣን የሰው ልጆች ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የሚመጣው
ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ እንጂ ሌላ አላማ የለውም፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10
ሰዎች ህይወት እንዲሆንልንና እንዲበዛልን የመጣውን
ኢየሱስን እንዳይረዱና እንዳይድኑ ሰይጣን የልባቸውን አይኖች በተለያየ የስህተት ሃሳብ ያጨልማል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተቀብለው እንዳይድኑ
ከወንጌል ሌላ የተሳሳተ አማራጭ ሃሳብ ይሰጣቸዋል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን አምነት ከዘላለም ፍርድ እንዳያመልጡ የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ
ያቃልልባቸዋል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተረድተው እንዳይከተሉ ክርስትና ሞኝነት በማስመሰል አእምሮዋቸውን ያጨልማል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን
ተረድተው እንዳይድኑ በተለያየ ነገር ባተሌ ያደርጋቸዋል፡፡
ብዙ
ነገሮችን የሚረዱ ሰዎች ይህንን ቀላል እውነት መረዳት ሳይችሉ ሲቀሩ በጣም እንገረማለን፡፡ ብዙ ነገሮችን የተመራመሩና ያገኙ ሰዎች
ይህንን ውስብስብ ያልሆነ ለመረዳት የማያዳግት እውነት ማየት ሲሳናቸው ያስገርማል፡፡
ሰይጣን
የሰው ልጆች ጠላት ነው፡፡ ሰዎች ተነግሮዋቸው ተመስክሮላቸው ይህንን እውነት የማያዩበት ምክኒያቱ የማያምኑትን ሃሳብ ያጨለመው ሰይጣን
ስለአለ ብቻ ነው፡፡
ሰይጣን
የማያምኑትን ሃሳብ ባሳወረ ቁጥር የሚያዩበትን የተገለጠልንን ብርሃን እናካፍላቸዋለን፡፡ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰዎች ብርሃንን
ከማካፈል ቸል አንልም፡፡ አንድ ቀን ጨለማውን የሚገፍ ብርሃን ይታያቸዋል፡፡
ከእግዚአብሔርም
ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ሐዋርያት ሥራ 26፡22-23
በክርስቶስ
ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡6
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #ጨለማ #አሳወረ #ብርሃን #ወንጌል #መመስከር #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment