የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም!
አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት ሀሰተኛ ሀይማኖት ነው። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት ከሰይጣን ነው።
ብዙ ሀይማኖቶች በምድር ላይ ቢኖሩም በአጠቃላይ ምድር ላይ ያሉት ሁለት አይነት ሀይማኖቶች ብቻ ናቸው። በምድር ላይ እውነተኛ እና ሀሰተኛ ሀይማኖት አለ። እግዚአብሔር አንድ ነው። ከአንድ በላይ እውነተኛ ሀይማኖት ሊኖር አይችልም። በአለም ላይ ከአንድ በላይ ሀሰተኛ ሀይማኖት ሊኖር ግን ይችላል።
ታዲያ ሀይማኖት መያዙ ሳይሆን እውነተኛውን አምላክ መያዛችንን እርግጠኛ እንሁን። እኔን በተመለከተ ፍለጋ አቁሜያለው እውነተኛውን አምላክ አግኝቻለሁ።
እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። ዮሐንስ 17:3 ሁሉም ሀይማኖት ወደ አንድ ፈጣሪ ያደርሳል የሚሉ በሰይጣን የተታለሉ ናቸው።
ኢየሱስም አለው፡— እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ዮሐንስ 14:6
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
