I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል። 1ኛዮሐንስ 3:19-20
-
Name it claim it Take it! “So Jesus answered and said to them, “Have faith in God. For assuredly, I say to you, whoever says to this mount...
-
Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deessi, maqaa isaas Amaanu'el jettee in mo...
-
የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16 ወንጌል በሃጢያታቸው ምክኒያት ለዘላለም ከእ...
-
ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 ፣6 7 ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለእኛ ነው። ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው እኛ በሃጢያታችን...
-
ጸሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው። ጸሎት ሊደረግ የሚችለው ከእግዚአብሄር ጋር በመግባባት ብቻ ነው። ጸሎት የሚሰምረው እንደ እግዚአብሄር አሳብ ስንጸልይ ብቻ ነው። በአጠቃላይ ለእግዚአብሄር ያለን አመለካከት ...
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
-
ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ኦሪት ዘጸአት 12:2 እውነተኛው አዲስ አመት የሚባለው ቃሉን ሰምተን ነጻ የምንወጣበትን ጊዜ ነው። እውነተኛው ዘመን መለወጫ የሚባለው ቃሉን ሰምተን በቃሉ ...
-
እግዚአብሄር - አባት የሁልጊዜ ነው፡፡ አባት ስሜቱን ዋጥ ያደርጋል፡፡ አባት ተለዋዋጭ ስሜቱን አይከተልም፡፡ አባት በመርህ ይመራል፡፡ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በ...
-
የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ነገር የመስራት እና የመለወጥ አቅም አለው። ያዕቆብ 5:16 … የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሀይል በፀሎታችን አይወሰንም። እግዚአብሔር ከምንለምነው ...
Showing posts with label Teaching. Show all posts
Showing posts with label Teaching. Show all posts
Sunday, June 21, 2020
ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 3፡12-13 ፣ 8፡5
ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 3፡12-13 ፣ 8፡5
Sunday, April 26, 2020
በምድር ያለነው
በተለያየ ጊዜ በህይወታችን የተለያዩ ተግዳሮቶች
ይመጣሉ፡፡ ታዲያ ይህን አልፈው ይሆን ብለን የምናስብበት ውጥረት በህይወታችን ይመጣል፡፡ እንደዚህ አይነት ውጥረት በህይወታችን
ሲገጥመን "በምድር ላይ ያለሁት ለምንድነው?" ብለን ይህን ጥያቄ ከልባችን እንጠይቃለን፡፡
በምድር ላይ ያለሁት ለምንድነው? የሚለው ጥያቄ
ሁል ጊዜ መጠየቅና በትክክል መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡
እውነት ግን በምድር ላይ ያለነው ለምንድነው?
የማንሞተው ለምንድነው ? ወይም መሞት የማንፈልገው
ለምንድነው ?
በምድር ላይ ያለነው ስላልሞትን ነው ? ወይስ
በምድር ላይ ስለመኖራችን ሌላ አለማ አለ?
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው አስቦና አቅዶና በአላማ
ነው፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27
ወደምድር ከመምጣታችን በፊት ወደምድር የመጣንበት
ልዩ አላማ ነበር፡፡
ማንም ሰው በድንገት ውይም በአጋጣሚ በምድር ላይ
የተወለደ ሰው የለም፡፡ ሰው በምድር ላይ የመወለዱ ምልክት ከመወለዱ በፊት የተወለደበት ልዩ አላማ የመኖሩ ምልክት ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና
ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11
እኛ በምድር ላይ ለመኖር ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር
በምድር ላይ እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ በምድር ላይ ለመኖር ካለን ፍላጎት በላይ በምድር ላይ እንድንኖር የተፈለገበት የእግዚአብሄር
አላማ ይበልጣል፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር
ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን
እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ኢሳያስ 46፡10
ይህን በህይወታችን ላይ ያለውን የእግዚአብሄርን
አላማ ስንረዳ እናርፋለን፡፡
እግዚአብሄር እንዴት እንደሚወደን ስንረዳ እና
በህይወት ለመኖራችን ልዩ አላማ እንዳለው ስንረዳ ከፍርሃት ነፃ እንወጣለን፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር
አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18-19
ፍርሃት የእግዚአብሄርን ፍቅር የመረዳታችንን ደረጃ
ያመለክታል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያለውን የፍቅር አላማ በተረዳን መጠን ፍርሃት ከህይወታችን ቦታ እያጣ ይሄዳል፡፡
የእግዚአብሄርን ፍቅር በተረዳን መጠን ከፍርሃት
ነፃ እንወጣለን፡፡ እግዚአብሄር እንዴት በፍቅር እንደሚያየን በህይወታች ላይ ያለውን የእግዚአብሄርን የፍቅር አላማ እየተረዳን ስንመጣ
በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር እንንቀሳቀሳለን፡፡
የእግዚአብሄርን የፍቅር አለማ ስንረዳ የሚያንቃቅሰን
ፍርሃት ሳይሆን ፍቅር ብቻ ይሆናል፡፡
በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡4
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ
#እይታ #አላማ
#ተስፋ #ፍፃሜ
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ተስፋ #ፍፃሜ
#የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Friday, April 24, 2020
Thursday, April 23, 2020
እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል። የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል። አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ። የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም ርቢ፥ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል። እንቅብህና ቡሃቃህ ቡሩክ ይሆናል። አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ። እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ። እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጐተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትጠብቅ፥ በመንገዱም ብትሄድ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለልህ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል። የምድር አሕዛብም ሁሉ የእግዚአብሔር ስም በአንተ ላይ እንደ ተጠራ አይተው ይፈሩሃል። እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ እግዚአብሔር በጎነቱን በላይህ ያበዛል። እግዚአብሔርም ለምድርህ በወራቱ ዝናብ ይሰጥ ዘንድ፥ የእጅህንም ሥራ ሁሉ ይባርክ ዘንድ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል፤ ለብዙ አሕዝብም ታበድራለህ፥ አንተ ግን ከማንም አትበደርም። ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። ኦሪት ዘዳግም 28፡1-14
Sunday, April 19, 2020
Tuesday, April 14, 2020
Saturday, April 4, 2020
ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
ማንም፦
እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:20
ፍቅር ረቂቅ ሃሳብ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን
እወደዋለሁ ቢል እግዚአብሄርን አትወድም ብለን መከራከር አንችልም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን እወዳለሁ ሲል እውነተኝነቱን በቀጥታ ለማረጋገጥ
ቀላል አይደለም፡፡ ምክኒያቱም ፍቅር የልብ ስለሆነና የሰው ልብ ደግሞ ተከፍቶ ስለማይታይና ስለማይታወቅ ነው፡፡
ፍቅር የልብ መሰጠት ስለሆነ ሰው እግዚአብሄርን
መውደዱ የሚረጋገጥበት ቀጥተኛ መንገድ የለም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን መውደዱንና አለመውደዱን በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ የሚያመለክቱ
ነገሮች ግን አሉ፡፡ እኛም እግዚአብሄርን እንዴት እንድምንወድ የምንፈትንባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ፡፡
ሰው እግዚአብሄርን መውደዱ መለኪያው ሰውን መውደዱ
ነው፡፡
ሰውን የመውደድ ጥቂቱን መመዘኛ የማያማላ ሰው እግዚአብሄርን እወዳለሁ ቢል ውሸቱን
ነው፡፡ ሰው የሚያየውን ሰው ካልወደደ የማያየውን እግዚአብሄርን እንደማይወድ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡
ለሰው ቅርቡ የሚያየውን ሰውን መውደድ ነው፡፡ ለሰው የሚቀለው ለሚያየው ሰው መልካምን
ማድረግ ነው፡፡ ለሰው የሚቀለው የሚያየውን ሰውን በርህራሄ ማየት ነው፡፡ ለሰው የሚቀለው የሚያየውን የሚዳስሰውን ሰውን መቀበል
ነው፡፡ ለሰው የሚቀለው የሚያየውን ሰውን መታገስ ነው፡፡ ለሰው የሚቀለው ከሚያየውን ሰው ጋር በትህትና መኖር ነው፡፡
ሰው እግዚአብሄርን እወዳለሁ እግዚአብሄርን አከብራለሁ የሚለው ለእግዚአብሄር ያለን
አክብሮት ለሰው እንዳለን አክብሮት በቀጥታ የማይታይ ስለሆነ ይሆናል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ፍቅር አለኝ የሚለው ስለማይታይ ይሆናል፡፡
ሰው በእግዚአብሄር ፊት ትሁት ነኝ የሚለው በቀጥታ ትህትናው በቀጥታ ስለማይለካ ይሆናል፡፡
ሰው ለሚያየው ሰው መልካምን ካላደረገ ለእግዚአብሄር መልካም ያደርጋል ማለት ዘበት
ነው፡፡ ሰው የሚያየውን ሰውን ካልተቀበለ የማያየውን እግዚአብሄርን ይቀበላል ማለት ውሸት ነው፡፡ ሰው የሚያየውን ሰውን በርህራሄ
ካላየ የማያየውን እግዚአብሄርን ይወዳል ማለት ከንቱ ነው፡፡ ሰው የሚያየውን ሰው ካልታገሰ እግዚአብሄርን እታገሳለሁ ማለቱ ከእውነት
የራቀ ነው፡፡ ሰው ከሚያየው ከሰው ጋር በትህትና መኖር ካልቻለ እኔ በእግዚአብሄር ፊት ትሁት ነኝ ቢል ተታልሎዋል፡፡
ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን
የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ሰላም #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #ፍቅር #ትህትና
#ርህራሄ #መልካም #ጠብ #መልካም #ፍርድ #እውቅና #ፍፁም #ችግር #መፍትሄ #አላማ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እምነት #ቃል
#ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
Saturday, March 28, 2020
Sunday, March 22, 2020
Saturday, March 21, 2020
Friday, March 20, 2020
እግዚአብሔር ተቀብሎታል
በእምነት
የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ። ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1-3
በዚህ ጊዜ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ መከላለያ
መንገዶች መካከል በክርስትያኖች መካከል መለያየት ይታያል፡፡ መለያየት በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ መለያየትን ተመስርቶ እርስ በእርስ
መናናቅ እና መፈራረድ ግን ክፉ ነው፡፡
1.
ተጨማሪ ቫይታሚን የሚወስደው
የማይወስደውን አይፍድበት፡፡
2.
ሆስፒታል ሔዶ የሚመረመረው
የማይመረመረውን አይናቀው፡፡
3.
የፊት መሸፈኛ ወይም ጓንት
የሚያደርገው የፊት መሸፈኛ የማያደርገው ላይ አይፍረድበት
4.
የቤተክርስትያንን ስብሰባ የሚካፈለው
የማይካፈለውን አይናቀው፡፡
5.
የሚጨብጠው የማይጨብጠውን አይናቀው፡፡
6.
ከቤቱ የሚወጣው የማይወጣውን
አይፍረድበት፡፡
አንተም
በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡10
እንግዲህ
ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤ ሆኖም
በደረስንበት በዚያ እንመላለስ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡15-16
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #የህይወትምስክርነት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Thursday, March 19, 2020
ዘመኑን ዋጁ
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ
በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16
በዘመናችን የሚሆን ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር
ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስገርመው
ነገር የለም፡፡ ከመሆኑ በፊት ምን እንደሚሆን መቼ አንደሚሆን ለምን እንደሚሆን ሁሉ ያውቀዋል፡፡
አስገራሚ የሚሆነው ሁሉንም ለማናውቅ ለእኛ ነው፡፡
ይህ ነገር እንደመጣ ይሄዳል፡፡ ይህ ነገር ተራራ እንደሆነብን ይህ ነገር አለፈ እንዴ እንላለን፡፡
የማያልፍ የሚመስለው በቅርቡ እንደተረት ይወራል፡፡
የእኛ ሃላፊነት ከእንደዚህ አይነት ጊዜ ውስጥ የተሻለ ነገር ማውጣት ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት ዘመኑን ለእግዚአብሄር መንግስት መጠቀም ነው፡፡
ክፉ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡
እግዚአብሄር ግን ክፉውን ለውጦ ለመልካምነታችን
ይጠቀምበታል፡፡
እግዚአብሔርንም
ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡28
ዘመኑን የምንገዛውና ለራሳችን ጥቅም የምንጠቀምበት
ዘጠኝ መንገዶች
1. እግዚአብሄርን ማመስገን
እግዚአብሄር
እንከን የማይወጣለት መልካም ነው፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር
ምስጋና ሊመሰገን ይገባል፡፡ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን የሚያዩ ሰዎች ሁልጊዜ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ ያመሰግኑታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር
ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡16-18
የሰው አመስጋኝነት የሚለካው በእንደዚህ አይነት ጊዜ ነው፡፡ ሰው ያለው ሃይል የሚለካው በፈተና ጊዜ ነው፡፡
በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 24፡10
2. አለመፍራት
ፍርሃት ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡
በፍርሃት የምናደርጋቸው ማንኛውም ድርጊቶች ይጎዱናል እንጂ አይጠቅሙንም፡፡
በፍርሃት የምናደርጋቸው ነገሮች ስለእግዚአብሄር ልጅነታችን አይመሰክርም፡፡ በፍርሃት የምናደርጋቸው ነገሮች በተለምዶው ማድረግ የምንቻለችውን ነገሮች እንኳን እንዳናደርግ
ሽባ ያደርገናል፡፡
ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች ብሎ መለሰለት። የሉቃስ ወንጌል 8፡50
3. አለመጨነቅ
ከጭንቀት የሚጠቀመው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ሰው ለመጨነቅ ሲፈተን ያንን ሃይል ፀሎት ላይ ማፍሰስ አለበት፡፡ ለመጨነቅ ሲፈተን ለጭንቀት የሚያባክነውን ጊዜ በፀሎት ላይ ማዋል ፍሬያማ ያደርገዋል፡፡ ለመጨነቅ ሲፈተን የጭንቀቱን ጉልበት በፀሎት ላይ ማፍሰስ ፍሬያማ ኢንቨስትመንት
ነው፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6
4. ሌሎችን ማበረታታት
ሰዎች ተጨንቀዋል፡፡ እኛ ደግሞ ላለመጨነቅ
100% ምክኒያት አለን፡፡ እግዚአብሄር
እረኛችን ነው፡፡ እግዚአብሄር
ጠባቂያችን ነው፡፡ እግዚአብሄር
መመኪያችን ነው፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ቃል ተበረታተን ሰዎችን ማበረታታት ሰዎች እግዚአብሄርን በእኛ እንዲያዩ ያደርጋቸዋል፡፡
ሰዎችን ማበረታታት የእኛ መንፈስ የተለየ መንፈስ እንዳለን ያሳያቸዋል፡፡ ሰዎችን ማበተታታት ብርታት ከመስጠቱ በተጨማሪ የሌላቸውን ያንን በመንፈስ ቅዱስ የሆነ የሃይል መንፈስ እንዲፈልጉት
እንዲጓጉ ያደርጋል፡፡
በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ
ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ
በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡14-16
5. ለሌሎች መልካምን ማድረግ
ይህ ጊዜ ደግሞ ያልፋል፡፡ ሰዎች መልካም ስራችንን የሚያዩበት ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ ከመንገዳችን ወጥተን ለሰዎች መልካም ማድረግ እውነተኛ ሰዎች መሆናችንን ለማሳየት እና የቀመስነውን የእግዚአብሄር
መንግስት መልካምነት እንዲቀምሱ ያበረታታቸዋል፡፡
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ
ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡16
6. ለራሳችን ጊዜ መውሰድ
አንዳንድ ጊዜ ሳናስበው በጣም ባተሌ ከመሆናቸን የተነሳ እግዚአብሄር ራሱ ከእኛ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ይናፍቀናል፡፡ ታዲያ ህይወት ዝም በሚልበት ጊዜ ለመፀለይ የእግዚአብሄርን
ፊት ለመፈለግ መጠቀም ዘመኑን ለመግዛት ያስችለናል፡፡ ይህንን አይነት ጊዜ በቀላሉ አናገኘውም፡፡
እግዚአብሄር በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሊያድሰን ሊለውጠን ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጊዜ ተጠቅመን የእግዚአብሄር ቃል በሙላት እንዲኖርብን
ቃሉን ማንበብና ማሰላለስ የማይገኝ እድል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚመስበው
ሁኔታው ሳይሆን የሚለወጠው እኛ ነን፡፡ እምነታችን ይፈተናል ይጠራል፡፡ አመለካከታችን
ይፈተናል ይለወጣል፡፡ ዋጋ አሰጣችን ይፈተናል ይለወጣል፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ
ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። የሉቃስ ወንጌል 10፡41-42
7. ዱለት ነው ከሚሉ ጋር ዱለት አለማለት
ሰዎች በፍርሃት ጠፋን ተቆረጥን ተፈለጥን ሲሉ እኛ መፍራት ያለብን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እኛ የምንፈራው በቂ እና ብቸኛ ፍርሃት አለን፡፡ እኛ ኮሮናን አናመልክም እግዚአብንሄርን
ብቻ እናመልካለን፡፡ እኛ ኮሮናን አንፈራም እግዚአብሄርን በፍፁም ልባችን እንፈራለን፡፡
እኛ ኮሮናን አንቀድስም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄርን እንቀድሳለን፡፡
በልባችን ልዩ ስፍራ ያለው ኮሮና ሳይሆን ክርስቶስ ነው፡፡ ኮሮናንና ክርስቶስን እኩል አንፈራም፡፡ የክርስቶስን
የዙፋን ቦታ ለኮሮና አንሰጠም፡፡
ማስፈራራታቸውንም
አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡14
8. ለሰዎች መፀለይ፡
ተስፋ ያለን ሰዎች ነን፡፡ ከምድር ያለፈ ተስፋ አለን፡፡ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች አናዝንም አንጨነቅም፡፡
በዚህ አጋጣሚ በህይወታችን
ስላለ ተስፋ ለሌሎች በየዋህነትና በፍርሃት እንመሰክራለን፡፡
በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ
ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ
ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡15
ሰዎች እንደዚህ ጊዜ ለፀሎት ክፍት የሚሆኑበት ጊዜ ላይኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ የተጨነቁ ሰዎች ስናገኝ ለእነርሱ መፀለይ ልባቸውን ወደክርስቶስ
መምራት እንዲሁም ጌታን ክርስቶስን የህይወታችንው
ጌታ እንዲያደደርጉት መምራት ይጠይቃል፡፡
9. ለፈውስ መፀለይ
አንደኛው የሚያምኑትን ከሚከተላቸው
ምልክቶች አንዱ በበሽታ ላይ ያላቸው ሃይል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የታመመ ሰው ስናገኝ ለዚያ ሰው መፀለይ ይጠብቅብናል፡፡
እንደዚህ አይነት አጋጣሚ በሃይል በእኛ የሚሰራውን የእግዚአብሄርን
ክብር የምንለማመድበት መልካሚ አጋጣሚ ነው፡፡
ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። የማርቆስ ወንጌል 16፡17-18
እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም
ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር። የማርቆስ ወንጌል 16፡20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
AbiY Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Subscribe to:
Posts (Atom)









