I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ኢየሱስ በስጋ ወደምድር ከመምጣቱ በፊት ብሉይ ኪዳን ' የጉብኝት ባህል ' እና በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተደረገው አዲስ ኪዳን ግሞ ' የ መ ኖር ባህል ' ተብሎ ...
-
ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ኦሪት ዘጸአት 12:2 እውነተኛው አዲስ አመት የሚባለው ቃሉን ሰምተን ነጻ የምንወጣበትን ጊዜ ነው። እውነተኛው ዘመን መለወጫ የሚባለው ቃሉን ሰምተን በቃሉ ...
-
የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ነገር የመስራት እና የመለወጥ አቅም አለው። ያዕቆብ 5:16 … የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሀይል በፀሎታችን አይወሰንም። እግዚአብሔር ከምንለምነው ...
-
እግዚአብሄር - አባት የሁልጊዜ ነው፡፡ አባት ስሜቱን ዋጥ ያደርጋል፡፡ አባት ተለዋዋጭ ስሜቱን አይከተልም፡፡ አባት በመርህ ይመራል፡፡ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በ...
-
በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል። 1ኛዮሐንስ 3:19-20
-
If you had it to do over again, you’d marry me for love Love and Let Live Love and Let Live By Dale Carnegie How To Win Friends And I...
-
Name it claim it Take it! “So Jesus answered and said to them, “Have faith in God. For assuredly, I say to you, whoever says to this mount...
-
When I was in high school I was taught a Biology theory called the survival of the fittest. Here is the Wikipedia definition of Survival...
-
የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16 ወንጌል በሃጢያታቸው ምክኒያት ለዘላለም ከእ...
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
Sunday, August 28, 2022
Saturday, August 27, 2022
ሲሾም ያልበላ
እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ አምላክ ነው:: በቅንነት ህዝብን እንዲያስተዳድርና እንዲፈርድ እግዚአብሔር የስልጣንእድልን ይሰጣል::
ሰው እግዚአብሄር የሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ የብዙዎችን ህይወት ሊለውጥ ይችላል::
አንዳንድ ሰው ግን ከሚከፈለው በላይ መኖር ሲመኝ እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን እንዲባርክበት የስጠውንስልጣን አላግባብ በመጠቀም ህዝብን ያስጨንቃል የማይገባውን ገንዘብ ይነጥቃል::
ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። ዘፅአት28:8
ጉቦኝነት የየዋህነት ተቃራኒ ተንኮለኝነት ነው::
በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች። መዝሙር 26:10
ጉቦኝነት በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም ብለን እንዳንፀልይ በእግዚአብሔር ፊት ያለንን ድፍረት ይመታል::
ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ። በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውምመማለጃ ተሞልታለች።እኔ ግን በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም። መዝሙር 26:9-11
ህይወቱን ለማስተካከል ጉቦ የሚቀበል ሰው ተታሏል:: በህይወት የማይታውከው ደሞዜ ይበቃኛል ብሎ ጉቦየማይቀበል ሰው ነው::
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።መዝሙር 15:5
ጉቦ የሚቀበል ሰው ቀለል ያለ ህይወቱን እላግባብ ያወሳስባል::
ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፤ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል። ምሳሌ 18:27
ጉቦ ልብን ያቆሽሻል:: ጉቦ በንፁህ ልብ እግዚአብሔርን እንዳናይ ያደርጋል::
ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል፤ ጉቦም ልቡን ያጠፋዋል። መክብብ 7:7
ሰውን ለመርዳት ጉቦን የሚቀበል ሰው የለም:: ሰው ጉቦ ሲቀበል ጉቦ የሚቀበለውን ሰው ይጎዳል:: ሰው ጉቦሲቀበል የባለመብቱን ፍትህ ያጣምማል::
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። አሞፅ 5:12
ሰው ጉቦ ሲቀበል ለማይገባው ሰው ይፈቅድለታል ይሚገባውን በመከልከል የባለመብቱን ፍትህ ያጣምማል::
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃልያጣምማልና ጉቦ አትቀበል። ዘዳግም 16:19
ጉቦ ፍትህን ያሸጣል::
ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል። ምሳሌ 17:23
ሰው ጉቦ ሲቀበል የማይገባውን ሰው አላግባብ ይጠቅማል:: ሀገር በህግ ሳይሆን በጥቅማ ጥቅም እንድትመራያደርጋል::
ሰው በቅንነት ከመፍረድ ይልቅ ጉቦ ሲቀበል ሰው በሰውነቱ እንዳይከበር ጉልበተኛ በጉልበቱ ተመክቶ የፈለገውንእንዲያደር ያደርጋል::
አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፥ ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ፤ ለድሀ አደጉአይፈርዱም፥ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም። ኢሳያስ 1:23
ጉቦ ሁሉም ሰው ሰርቶ እንዳያድግ እና እንዳይለወጥ በተቃራኒው ሌቦችና አጭበርባሪዎች በነፃነት እንዲዘርፉያደርጋል:: ህዝብ ሁሉ እንዲደኸይ ጥቂቶች ብቻ ሃብቱን አላግባብ እንዲያካብቱ ያደርጋል::
ልጆቹም በመንገዱ አልሄዱም፥ ነገር ግን ረብ ለማግኘት ፈቀቅ አሉ፥ ጉቦም እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።1ኛ ሳሙኤል 8:3
የንጹሑን ሰው ነፍስ ለመግደል ጉቦ የሚቀበል ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ዘዳግም 27:25
እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ክእንግዲህ ወዲህም አንገተደንዳና አትሁኑ። ዘዳግም 10:17
በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው! ኢሳያስ 5:23
ጉቦ የሚቀበል ሰው አገሬን እወዳለው የሚለው ውሸቱን ነው:: ጉቦ ቤተሰብን ብሎም እገርን ያፈርሳል::
ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል፤ መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል። ምሳሌ 29:4
ጉቦ የሚቀበል ሰው እግዚአብሔር ቤቴን እግዚአብሔር ይጠብቀዋል የሚለውን ድፍረቱን ያጣል::
የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥
የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች። ኢዮብ 15:34
እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፤ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ። ሚክያስ 7:3
የገንዘብ ፍቅር ያለበት ጉቦ የሚቀበል ኢየሱስ መሞቱን እንኳን ይክዳል::
ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው። እኛ ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለንእናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸውአደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል። ማቴዎስ 28:12-15
ጉቦ የሚቀበል እግዚአብሔር በነፃ የሰጠውን ቸርችሮ የሚበላበት ሰው እግዚአብሔርን አያምንም::
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፤ ከዚህምጋር። እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔርይታመናሉ። ሚክያስ 3:11
ጉቦ የሚቀበል እግዚአብሔር በህዝብ እንዲያገለግል የሰጠውን ስልጣን አላግባብ የሚጠቀም ሰውእግዚአብሔርን የረሳ ነው::
በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ጉቦን ተቀበሉ፤ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ከባልንጀሮችሽም በቅሚያየስስትን ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ህዝቅኤል 22:12
እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሰው::
በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁንየሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፥ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።ኢሳያስ 33:15
ያን ጊዜም ደግሞ እንዲፈታው ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ አደረገ፤ ስለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ እያስመጣያነጋግረው ነበር። ሐዋርያት 24:26
ጉቦ የሰጠህ ሰው አንተ ትልቅ ቦታ ላይ ሆነህ በገንዘብ ስለገዛህ በልቡ ይንቅሀል ሳይወድ ስለዘረፍከው ደግሞበልቡ ይረግምሀል:: ሰው ሲረግምህ መንገድህ አይቀናም::
በጉቦ የተቀበልከው ጥቅም ላብህ ስላይደለ ያንተ አይደለምና በወጉ አትጠቀምበት:: በንፅህና ስላላገኘህው ኮሽባለ ቁጥር ትደነግጣለህ ኑሮህ የቆቅ ኑሮ ይሆናል::
ጉቦ አእምሮን ስለሚያበላሽ ከምትጠቀምበት በላይ ስለምትሰበስብ በጉቦ ያገኘኸውን ገንዘብ ለመደበቅ ስትጥርበመሃል ሌላው ይበላዋል::
በእጆችህ በመድከም ቀስ በቅስ የተከማቸ ሃብት ስላይደ ለአያያዙን ስለማታውቅበት እንደጠላት ገንዘብትበትነዋለህ::
ከደሃ አስጨንቀህ መቀበልህን እንጂ ራስህ እንደምትጠቀምበት እርግጠኛ መሆን አትችልም:: ከድሀ ኪስአውጥተህ ለማንም እንዳይሆን በክንቱ ትበትነዋለህ::
ለራሱ ጥቅም ለመጨመር ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለባለጠጋም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል። ምሳሌ22:16
ሲሾም ያልበላ በሰላም ይኖራል::
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

