I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸ...
-
Faith is an Adventure Faith is an exciting adventure. The faith walk is a real and worthwhile adventure. There is nothing more adventuro...
-
It is very wise to seize any opportunity set-aside to give thanks to the Lord. But thanks-giving isn’t a once a year activity to be ...
-
የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ...
-
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡1-10 ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል። ...
-
Who is the real Jesus? Two thousand years ago a man set foot on our planet who claimed to be from a place beyond space and time. Althoug...
-
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። ...
-
እግዚአብሔርን ሰውን ሲፈጥረው ከሰው ጋር በደንብ መነጋገር እንዲችል በመልኩና በአምሳሉ ነው የፈጠረው፡፡ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ ለፈጠረው ለሰው ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔርና የሰው ግንኙነት በሃጢያት ምክኒያት...
-
የእግዚአብሄር መንግስት የመንፈስ መንግስት ነው፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምናደርገውን ማንኛውንም ነገር የምናደርገው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም፡፡ ለክርስትና ህይወት እምነት ወሳኝ ነው፡...
-
ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡8 በእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንኖረው በእግዚአብሄር ህግ በእግዚአብሄር ቅድመ ሁኔ...
Showing posts with label Letting go makes you wealthier. by CJ Jackson. Show all posts
Showing posts with label Letting go makes you wealthier. by CJ Jackson. Show all posts
Sunday, June 21, 2020
ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 3፡12-13 ፣ 8፡5

Sunday, April 26, 2020
በምድር ያለነው
በተለያየ ጊዜ በህይወታችን የተለያዩ ተግዳሮቶች
ይመጣሉ፡፡ ታዲያ ይህን አልፈው ይሆን ብለን የምናስብበት ውጥረት በህይወታችን ይመጣል፡፡ እንደዚህ አይነት ውጥረት በህይወታችን
ሲገጥመን "በምድር ላይ ያለሁት ለምንድነው?" ብለን ይህን ጥያቄ ከልባችን እንጠይቃለን፡፡
በምድር ላይ ያለሁት ለምንድነው? የሚለው ጥያቄ
ሁል ጊዜ መጠየቅና በትክክል መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡
እውነት ግን በምድር ላይ ያለነው ለምንድነው?
የማንሞተው ለምንድነው ? ወይም መሞት የማንፈልገው
ለምንድነው ?
በምድር ላይ ያለነው ስላልሞትን ነው ? ወይስ
በምድር ላይ ስለመኖራችን ሌላ አለማ አለ?
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው አስቦና አቅዶና በአላማ
ነው፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27
ወደምድር ከመምጣታችን በፊት ወደምድር የመጣንበት
ልዩ አላማ ነበር፡፡
ማንም ሰው በድንገት ውይም በአጋጣሚ በምድር ላይ
የተወለደ ሰው የለም፡፡ ሰው በምድር ላይ የመወለዱ ምልክት ከመወለዱ በፊት የተወለደበት ልዩ አላማ የመኖሩ ምልክት ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና
ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11
እኛ በምድር ላይ ለመኖር ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር
በምድር ላይ እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ በምድር ላይ ለመኖር ካለን ፍላጎት በላይ በምድር ላይ እንድንኖር የተፈለገበት የእግዚአብሄር
አላማ ይበልጣል፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር
ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን
እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ኢሳያስ 46፡10
ይህን በህይወታችን ላይ ያለውን የእግዚአብሄርን
አላማ ስንረዳ እናርፋለን፡፡
እግዚአብሄር እንዴት እንደሚወደን ስንረዳ እና
በህይወት ለመኖራችን ልዩ አላማ እንዳለው ስንረዳ ከፍርሃት ነፃ እንወጣለን፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር
አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18-19
ፍርሃት የእግዚአብሄርን ፍቅር የመረዳታችንን ደረጃ
ያመለክታል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያለውን የፍቅር አላማ በተረዳን መጠን ፍርሃት ከህይወታችን ቦታ እያጣ ይሄዳል፡፡
የእግዚአብሄርን ፍቅር በተረዳን መጠን ከፍርሃት
ነፃ እንወጣለን፡፡ እግዚአብሄር እንዴት በፍቅር እንደሚያየን በህይወታች ላይ ያለውን የእግዚአብሄርን የፍቅር አላማ እየተረዳን ስንመጣ
በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር እንንቀሳቀሳለን፡፡
የእግዚአብሄርን የፍቅር አለማ ስንረዳ የሚያንቃቅሰን
ፍርሃት ሳይሆን ፍቅር ብቻ ይሆናል፡፡
በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡4
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ
#እይታ #አላማ
#ተስፋ #ፍፃሜ
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ተስፋ #ፍፃሜ
#የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Tuesday, June 28, 2016
ፈጣን ባለጠግነት
እግዚአብሄር በልጆቹ ብልፅግና መሳካትና መከናወን ደስ ይለዋል፡፡ እግዚአብሄር ይባርካል፡፡ እግዚአብሄር በማንም መባረክና ማግኘት ላይ ተቃውሞ የለውም፡፡ እንዲያውም መፅሃፍ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንድንመካ ያስተምረናል፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡17
የሰው ታማኝነት የሚታየው በአንድ ቀንና በአንድ ወር አይደለም፡፡ የሰው ታማኝነት የሚታየው በጊዜያት ውስጥ ነው፡፡ የታመነ ሰው በመታመን በቀጠለ መጠን ጥቂት በጥቂት እየጨመረ እየተባረከና እየበዛ ይሄዳል፡፡
እግዚአብሄር የራሱ እርምጃና ፍጥነት አለው፡፡ነገር ግን እግዚአብሄር በአንዴ አያሳድግም፡፡
ባለጠጋ ለመሆን መቸኮል ግን ችግር ነው፡፡ ፈጣኑ ባለጠግነት የእግዚአብሄር እጅ የለበትም፡፡ ፈጣኑ ባለጠግነት በፍፁም በንፅህና የሚመጣ አይደለም፡፡ ፈጣኑ ባለጠግነትና ከእግዚአብሄር ውጭ የሚመጣ ነው፡፡
ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኩል ወይ ያጭበረብራል ወይ ይሰርቃል ወይ ይገድላል፡፡ ባለጠጋም ለመሆን ቸኩሎም ንፁህም መሆን አይቻልም፡፡ ባለጠጋ ለመሆን ቸኩሎም የእግዚአብሄርን በረከትንም ጠብቆም አይሆንም፡፡
ሰው ባለጠጋ ለመሆን ከቸኮለ የእግዚአብሄርን እርምጃ አልታገሰም ፡ እግዚአብሄርን በትግስት አልጠበቀም እንዲሁም የእግዚአብሄርን የበረከት መንገድ ትቶታል ማለት ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚሰጠው ሃብት መሰረት ያለው ነው ሃዘንንም ከእርሱ ጋር አይጨምርም፡፡
የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም። ምሳሌ 10፡22
በችኮላ የምትከማች ሃብት ግን የእግዚአብሄር እጅና ድጋፍ ስለሌለባት መሰረት እንደሌላት ቤት ነች፡፡ ተግንብታ ስታልቅ ከስርዋ ትናዳለች፡፡
በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11

Wednesday, April 25, 2012
Letting go makes you wealthier. by CJ Jackson
Letting go makes you wealthier. by CJ Jackson
Wealth is never measured by what you have, but by what you can give away. You are rich with money when you can afford to donate. You are rich with love when you can give love freely. You are rich with God when you can behold your enemy with compassion.
"Its better to give than to recieve because the principle is the more you give the same meausre will be met back to you"
Luke 6:38Mark 4:24,25
Letting go makes you wealthier!
For more posts click the link below
More posts

Subscribe to:
Posts (Atom)