Popular Posts

Wednesday, October 30, 2024

የአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊነት ምርጫ

የአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊነት ምርጫ የአሜሪካዊያንንም ይሁን ይነስም ይብዛም በአጠቃላይ የአለምን ህዝብ ትኩረት የሳበ ርእስ ነው። 
እንደ ክርስትያን በፖለቲካ ምርጫ መሳተፍ ምንም የማይወጣበት ትክክል ነገር ቢሆንም በሪፐብሊካንም ይሁን በዲሞክራት ላይ ያን ያህን ልባችንን መጣል እና ተስፋ ማድረግ እንደማይገባ ማስታወስ አለብን። 
ፖለቲከኞች በፖለቲካ ፖሊሲ ወይም መመሪያቸው የሚለያዩ ቢሆኑም ሪፐብሊካንም ይሁን ዲሞክራት ቢያሸንፍ እንደው ያን ያህል ስር ነቀል ልዩነት የሚያመጣ ነገር ያመጣል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው። 
እንደ ክርስትያን በምርጫ ካርዳችን ከምናመጣው ልዩነት በላይ ማንም ይሁን ማን ለተመርጠው እና በስልጣን ላይ ላለው መንግስት  እለት ተእለት ለነገስታት እና ለመኳንንት መጸለይ ይበልጥ በዘላቂነት ልዩነት ያመጣል። 
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡1-2
እኛ ራሳችን ፖለቲከኞች ብንሆን እንኳን በምርጫ ቅስቀሳም ቢሆን በምርጫ ካርዳችን ከምናመጣው ልዩነት ይልቅ በጸሎታችን የምናመጣው ልዩነት እጅግ ይበልጣል። ሪፕብሊካን ይሁን ዲሞክራት ከሁሉም በላይ የእናንተን ልመናና ጸሎት ምልጃ ይፈልጋል። 
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ምርጫ #ጸሎት #ምልጃ #ምስጋና #ልመና #ክርስትያን #ፖለቲካ 


 

በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን

 https://youtu.be/VhF0pSsp14I

በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን

Tuesday, October 29, 2024

ሀሎዊን ክፍል 2

 

ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያየ መልኩ ይከበራል፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚከብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባቸውም ባይገባቸውም መንፈሳዊ እንደምታ የለውም ማለት ግን አይቻልም። 

 ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ እንጂ ስለሌላ አይመጣም የተባለው ጠላት ዲያቢሎስ ባገኘው አጋጣሚ የሰዎችን ህይወት ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል።  

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፣10 

 

ሰይጣን በእግዚአብሄር ይፈጠር የእግዚአብሄር መላክ የነበር ሳጥናኤል ነበር። ሳጥናኤል ሰይጣን የሆነው እና እርሱን ከተከተሉት የወደቁት መላእክት ጋር ከእግዚአብሄር ፊት ወደ ምድር የተጣለው በትእቢት እንደ እግዚአብሄር ሊሆን ስለፈለገ ነበር።  

 

መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል። የይሁዳ መልእክት 1:6 

 

ሰይጣን ዲያብሎስ የእሳት ባህር ቅጣት ተዘጋጅቶልታል።  

 

እስክዚያ ግን የቻለውን ያህል ሰው አታልሎ ብዙ ሰዎችን ወደ እሳት ባህር መሄድ ይፈልጋል። የእሳት ባህር ለሰው ያልተዘጋጀ ቢሆንም እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ ያዘጋጀውን ከሃጢያት የመዳኛ መንገድ ያልተቀበሉ ሁሉ ለሰይጣን እና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው የእሳት ባህር ይጣላሉ። 

 

እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ ያዘጋጀውን ከሃጢያት የመዳኛ መንገድ የተቀብሉ ብቻ ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም አይለያዩም ለሰይጣን እና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው የእሳት ባህር አይጣሉ። 

 

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። የማቴዎስ ወንጌል 25:11 

 

 አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa  

#ሰይጣን #ሀሎዊን #ሃሎዊን #ጠላት #ዲያቢሎስ #አቢይዋቁማ #ኢየሱስጌታ #ኢየሱስ