Popular Posts

Saturday, May 12, 2018

እናት ልጅዋን እንደምታጽናና

እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፥ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል። እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ። ኢሳያስ 66፡12-13
እግዚአብሄር ርህሩህ ነው፡፡ እግዚአብሄር አዛኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያፅናናል፡፡ እግዚአብሄር ልብን ይደግፋል፡፡ እግዚአብሄር ሲያፅናና የማይጽናና ሰው የለም፡፡
እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። መዝሙር 149፡8-9
ሃዘን ከባድ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍጥረታችንን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ከማንኛውም ሃዘን እንዴት እንደሚያፅናናን ያውቃል፡፡
ስለዚህ ነው ሃና እግዚአብሄር ስራን መዝኖ ያዘነን እንዴት እንደሚክስ ትናገራለች፡፡
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3
ሃዋሪያው ጳውሎስ እግዚአብሄርን የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ ይለዋል፡፡
የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና። 2ኛ ቆሮንቶስ 1፡3-5
በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ብሎ ኢየሱስ እንደተናገረ እግዚአብሄር በውስጣችን እንዲኖር የላከው መንፈስ ቅዱስ እንደ እናት አፅናኝ ነው፡፡
አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ 14፡26
እግዚአብሄር ሲያበረታ ተመልሶ የሚበረታ የማይመስለው ሰው እንደገና ይበረታል፡፡ እግዚአብሄር እንደ እናት ይንከባከባል፡፡ እግዚአብሄር ሰላምን ይመልሳል፡፡ እግዚአብሄር እንደገና ደስ ያሰኛል፡፡ እግዚአብሄር ሲያፅናና ሰው እንዴት ተፅናሁ ብሎ እስከሚያስብ ድረስ ይፅናናል፡፡
አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ፊልጵስዩስ 4፡7
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ሴት #እናትነት #ጌታ #መፅናናት #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ  #ቃል #ደግነት #ቸርነት #አልረሳሽም #እግዚአብሔርንመምሰል #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #የእናቶችቀን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment