በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ። ሕዝቅኤል 28፡17
ሰይጣን እግዚአብሄር ላይ በማመፅ ከመውደቁ በፊት በእግዚአብሄር ጥበብ ነበር የሚኖረው፡፡ ሰይጣን ከክብሩ ሲወድቅ ግን
የሰይጣን ጥበብ ረከሰ፡፡
ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚታለሉት ጥበበኛ የሆኑ እየመሰላቸው ነው፡፡ ጥበበሦች የሆኑ ሲመስላቸው የማያስተውሉ ይሆናሉ፡፡
ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ ሮሜ 1፡22
ሰዎች ጥበብ አለን ይላሉ ነገር ግን ያላቸው ጥበብ ምን አይነት ጥበብ እንደሆነ አያስተውሉም፡፡ ሰዎች በጥበብ እየኖሩ
ይመስላቸዋል ነገር ግን ያላቸውን የጥበብ አይነት ለይተው አያውቁትም፡፡
ሰዎች በአግዚአብሄር ጥበብ እየኖሩ እየመሰላቸው በሰይጣን ጥበብ ይኖራሉ፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ጥበብ ሁሉ እውነተኛ ጥበብ እንዳይደለ ያስተምራል፡፡ ጥበብ ሁሉ ንፁህ ጥበብ እንዳይደለ መፅሃፍ ቅዱስ
ያስተምራል፡፡ ንፁህ ጥበብ እንዳለ ሁሉ የረከሰ ጥብብ እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ ያስተምረናል፡፡
ሰይጣን ጥበብ አለው፡፡ ነገር ግን የሰይጣን ጥበብና የእግዚአብሄር ጥበብ አንድ አይደሉም፡፡ የሰይጣን ጥበብ የረከሰ
ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥብብ ቅዱስ ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የየዋህነት ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የተንኮል
ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የይቅርታ ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የመራርነት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የፍቅር
ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የቅንአት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የአንደነት ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የአድመኝነትና
የመከፋፈል ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የሰላም ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የጥል ጥበብ ነው፡፡
ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡13-17
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #መራራ #ቅንዓትና #አድመኛነት #ንጽሕት #በኋላም #ታራቂ #ገር #እሺባይ
#ጥርጥር #ግብዝነት ##አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment