አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡8-11
ሰዎች በዘመናቸው ብዙ ነገሮችን እንዲሆንላቸው ይመኛሉ፡፡ ሰዎች በህይወታቸው ጥሩ መልበስን ፣ጥሩ መብላትን ፣ ጥሩ ቤት ውስጥ መኖርን ይመኛሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ታዋቂ ለመሆን ይመኛሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ሃያል ለመሆን ይመኛሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ መልካም ምኞቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ምኞቶች በራሳቸው ምንክ ክፋት የሌላቸው ተፈጥሮአዊ ምኞቶች ናቸው፡፡ እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ምኞቶች ጊዜያዊና አሁን ኖረው ሌላ ጊዜ የማይኖሩ ተለዋዋጭ ምኞቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ምኞቶች ምድራዊ ምኞቶች ናቸው፡፡
ሃዋሪያው በእውነት ከሁሉ ስለሚበልጥ ምኞት ይናገራል፡፡ ይህ ምኞት ከሁሉ ምኞቶች ይበልጣል፡፡ ይህም ምኞት ከሁሉ ምኞቶች ይልቃል ይከብራል፡፡ ይህ ምኞት ከሁሉ ምኞቶች እጅግ የከበረ ዋጋ አለው፡፡
ሌሎች ምድራዊ ምኞቶች ማንም ሰው ሊያገኛቸው የሚችላቸው ምኞቶች ናቸው፡፡ ሌሎቹ ምኞቶች እግዚአብሄርን የማያውቅ ሰው እንኳን የሚደርስባቸው ምኞቶች ናቸው፡፡
ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡32
ሌሎች ሁሉ ምኞቶች ሰው ያን ያህል ዋጋ ሳይከፍል ሊያገኛቸው የሚችላቸው ምኞቶች ናቸው፡፡ ሌሎቹ ምኞቶች በእውነት መንገድ ሊመጡ ቢችሉም እንኳን በስስትና በክፋትም መንገድ ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ሌሎች ምኞቶች በእውነት ባልሆነ መንገድ ሊመጡ የሚችሉ ተራ ምኞቶች ናቸው፡፡
ይህ የከበረ ምኞት ግን በሌላ በምንም ነገር አይመጣም፡፡ ሃዋሪያው የሚመኘው ምኞት ግን በሰው ብልጠት አይመጣም፡፡ ይህ ምኞት በሰው ጥበብ አይመጣም፡፡
ይህ ጥበብ የሚመጣው በእውነት ዋጋ በመክፈል ነው፡፡ ይህ ምኞት የሚመጣው ነገሮችን በመተው ነው፡፡ ይህ ምኞት የሚመጣው ነውረኛ ረብ በመናቅ ነው፡፡
ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡9
ይህ ምኞት የሚመጣው ብዙ ሰዎች የሚያከብሩዋቸውን ነገሮችን እንደጉድፍ በመቁጠር ነው፡፡ ይህን ምኞት የሚገኘው በመተው እና በመጎዳት ነው፡፡ ይህ ምኞት ክርስቶስንና የትንሳኤውን ሃይል የማወቅ ምኞት ነው፡፡
ይህ እውቀት የክርስትና ህይወታችንን ፍሬያማ ያደርጋል፡፡
እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1፡8
ይህ ምኞት በክርስቶስ እውቀት የማደግ ምኞት ነው፡፡ ይህን እውቀት ለማግኘት የማንተወው ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ይህን እውቀት ለማግኘት የማንንቀው ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ይህንን እውቀት ለማግኘት የማንጎዳወ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡18
ይህ ምኞት ክርስቶስ በልባችን በእምነት እንዲኖር የመጠማት ምኞት ነው፡፡
በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ ኤፌሶን 3፡16-17
ይህ ምኞት ክርስቶስን በጥልቀት የማወቅ ምኞት ነው፡፡
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡8-11
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ክርስቶስ #ጌታ #እውቀት #የትንሳኤሃይል #እምነት #ምኞት #መከራ #ትንሳኤ #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ሞት #መመለስ #ሃይል #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment