Popular Posts

Friday, January 31, 2020

ሁሉን እንድንችል የሚፈልግ እግዚአብሔር



እግዚአብሄር ቸር ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በልግስና በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሳይሰስት ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ ኦሪት ዘፍጥረት 126-27
እግዚአብሄር የዘላለም ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር የዘላለም ገዢ ነው፡፡
እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። መዝሙረ ዳዊት 472
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር እንደ እርሱ አድርጎ ምድርን እንዲገዛና እንዲያስተዳድር ነው፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። ኦሪት ዘፍጥረት 126-27
እግዚአብሄር ሁሉን ይችላል፡፡
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። የሉቃስ ወንጌል 137
ለእግዚአብሄር የሚያቅተው ነገር የለም፡፡
እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን? ትንቢተ ኤርምያስ 3227
እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው ስለአንድ ነገር የእግዚአብሄር አላማ በመረዳት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው ስላለንበርት ሁኔታ የእግዚአብሄር ፈቃድ በመረዳት ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 1017
የእግፍዚአበሄር ቃል በመስማት እምነትን ላገኘ ሰው የሚሳነው ነገር የለም፡፡
ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ቢሰማ የማይቻለው ነገር አይኖርም፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡
ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። የማርቆስ ወንጌል 923
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ስንፈፅም ምንም ነገር ፊታችን እንዲቆም እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን በቃሉ ስንሰማ በህይወታችን የእግዚአብሄርን አላማ ከመፈፀም ምንም አያቆመንም፡፡ እግዚአብሄር የማይችለው ነገር እንደሌለ ሁሉ እግዚአብሄርን ስናምን የሚሳነን ነገር አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር በእምነት የማንችለው ነገር እንዳይኖር ይፈልጋል፡፡ 
እግዚአብሄር የፈጠረን እርሱ አላማውን ለማስፈፀም የሚከለክለው የሚያግደው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የእግዚአብሄር ፈቃድ በምድር ላይ እንድናስፈፅም በእምነት የሚሳነን ነገር እንዳይኖር አድርጎ ነው፡፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ስንፈፅም በህይወት በዘመናችን ሁሉ በፊታችን የሚቆም ነገር እንዳይኖር አድርጎ አሸናፊ አድርጎ ፈጥሮናል፡፡
በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 15
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakum Dinsa 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መስማት #የእግዚአብሄርቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Thursday, January 30, 2020

ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ብልሃት



ሰማይንና ምድርን የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡
ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም አጽንቶአታልና። መዝሙረ ዳዊት 24፡1-2
የምድር ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8
ምድርን እያስተዳደረ ያለው የምድር ገዢው እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። መዝሙረ ዳዊት 47፡2
እግዚአብሄር የምድር ፈራጅ ነው፡፡
ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል። የሐዋርያት ሥራ 17፡31
ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ለአላማው ነው፡፡
ታዲያ ለሰው ከምድር ባለቤት ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት መኖር እንዳለበት ከማወቅ የበለጠ የሚያስፈልገው እውቀት የለም፡፡ ለሰው መጀመሪያ የሚያስፈልገው እውቀት ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት በሰላም እንደሚኖር የሚያሳውቀው እግዚአብሄርን የመፍራት ጥበብ ነው፡፡   
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 9፡10
ሰው ምንም እውቀት ቢኖረው ከምድር አስተዳዳሪ ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት መኖር እንዳለበት ካላወቀ ያለው ሌሎች አውቀቶች ሁሉ ዋጋ የላቸውም፡፡ ሰው ምንም እውቀት ቢኖረው ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር ካላወቀ ገና ምንም አያውቅም፡፡
በምድር በሰላም እና በስኬት ለመኖር ዝቅተኛው መመዘኛ እግዚአብሄርን እንደ እግዚአብሄርነቱ ማክበር ወይም እግዚአብሄርን የመፍራት እጥበብ ነው፡፡
ለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡21-22
ከምድር ባለቤት ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር ሳያውቅ በሰላም እኖራለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡
ከምድር ገዢ ጋር በትህትና ሳይሄዱ ይሳካልኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8
ሰው በምድር ላይ ያሉትን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሞ ማለፍ የሚችለው እግዚአብሄርን እንዴት እንደሚፈራው ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡
እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። ኦሪት ዘዳግም 6፡21
እግዚአብሄር ከሰው እጅግ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ብዙ የሚያልፋቸው ነገሮች አሉ ነገር ግን እርሱን በመፍራት ላይ ግን አይደራደርም፡፡ እግዚአብሄር ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ባይጠብቅም  እርሱን መፍራትን ግን ከሰው ይጠብቃል፡፡
የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ መጽሐፈ ምሳሌ 9፡10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Saturday, January 18, 2020

የአንድነት ዋጋ



መተባበርና አንድነት የከበረ ነገር ነው፡፡ አንድነት ትልቅ ዋጋ ያለው ሃብት ነው፡፡ ሰው በአንድነት የሚያደርጋቸው ነገሮች  በተናጥል ከሚያደርጋቸው ነገሮች በላይ ፍሬያማ ያደርጉታል፡፡
በአንድነት ውስጥ የታመቀ ትልቅ ጉልበት አለ፡፡ ሰው ሲተባበር እና በአንድ ላይ ሲሰራ በተናጥል ከሚያመጣው ውጤት በላይ የተሻለ ውጤት ያመጣል፡፡ ሰው ፣ በቤተሰብ ፣ በቤተክርስትያን ፣ በስራና በአገር ደረጃ በተናጥል ከሚሰራው ስራ ይልቅ ተባብሮ የሚሰራው ስራ ብዙ ጥቅምን ብዙ ነው፡
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም አሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። ኦሪት ዘሌዋውያን 26፡8
አንድነት ግን ቀላል አይደለም፡፡ አንድነት ይበልጥ ፍሬያማ እንደሚያደርግ ሁሉ አንድነት ይበልጥ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
ሰው ብዙን ጊዜ ከአንድነት ይልቅ መለያየትን የሚመረጥው በአንድነት ውስጥ ያለውን እምቅ ሃይል በቅጡ ስለማይረዳና አንድነት የሚጠይቀውን ዋጋ መክፈል ስለማይፈልግ ነው፡፡ ብዙ ሰው በአንድንት ያለውን ዋጋ ከመክፈል ይልው በስንፍና በተናጥል ያነሰ ነገርን ማግኘትን ይመርጣል፡፡ ሰው ለአንድነት ዋጋ መክፈል ሳይፈልግ ሲቀር በውስጡ ያለውን የአንድነትን እምቅ ጉልበት ያባክነዋል፡፡
ማንም ሃያል ሰው በጋራ ከሚሰራ ስራ በላይ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ማንም ጠቢብ ሰው ብቻውን ምንም ያህል ቢጥር በጋራ ቢሰራ እንደሚያመጣው ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ በአንድነት ብቻ ውስጥ የሚገኝ በተናጥል ውስጥ የሚየገኝ ለአንድነት ብቻ የተለየ ታላቅ ሃይል አለ፡፡
አንድነት ከተናጥልነት በላይ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ነገር ግን አንድነት ከተናጥል በላይ እጅግ ብዙ ፍሬ እንድናፈራ ያደርገናል፡፡
አንድነት ማለት ተመሳሳይነት ማለት አይደለም፡፡ አንድነት ማለት የተለያዩ ሰዎች ለአንድ የጋራ አላማ መስራት ማለት ነው፡፡ እውነት ነው እኛን ከማይመስል ሰው ጋር ከመስራት ይልቅ ከእኛ ተመሳሳይ ሰው ጋር መስራት ይቀላል፡፡ ነገር ግን እኛን ከማይመስል ሰው ጋር ለጋራ አላማ መስራት ይበልጥ ፍሬያማ ያስደርጋል፡፡  
አንድነት ትህትናን ይጠይቃል፡፡ አንድነት የማይመስለንን ሰው መቀበል ይጠይቃል፡፡ አንድነት ከእኛ በተለየ ሰው ማመን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ከእኛ የተለየን ሰው ለጋራ አላማ መታገስን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ዋጋ ይከፍላል፡፡ አንድነት ዋጋን ይከፍላል፡፡
አንድነት ሌላውን መረዳትና ሌላውን ማመንን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ራስ ወዳድ አለመሆን ሌላውን ማስቀደምን ይጠይቃል፡፡ አንድነት እኛን የማይመስልን ሰው መታገስ ይጠይቃል፡፡ አንድነት የእኔ  አሳብ ብቻ ይሰማ አለማለትን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ትህትናን ለጋራ አላማ በሌሎች ሃሳብ መስማማትን ይጠይቃል፡  
በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡1-2
አንድነት የሰነፎች እና የቸልተኞች አይደለም፡፡ አንድነት ትጋትን ይጠይቃል፡፡
በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡2-3
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #መዳን #እምነት #አንድነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ህብረት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ትግስት #መሪ

ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል። መዝሙረ ዳዊት 75፡6-7


Thursday, January 16, 2020

WAR ROOM | Elizabeth Jordan sends the devil out of her house



Elizabeth Jordan : I don't know where you are, Devil, but I know you can hear me. You have played with my mind and had your way long enough! No more! You are done! Jesus is the Lord of this house, and that means there's no place for you here anymore! So take your lies, your schemes, and your accusations and get out in Jesus' name! You can't have my marriage, you can't have my daughter and you sure can't have my man! This house is under new management and that means you are out! And another thing, I am so sick of you stealing my joy, but that's changing too. My joy doesn't come from my friends, it doesn't come from my job, it even doesn't come from my husband. My joy is found in Jesus, and just in case you forgot, he has already defeated you, so go back to Hell where you belong and leave my family alone! From War room Christian movie.

Monday, January 13, 2020

የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡6-8


የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡6-8