Popular Posts

Saturday, May 5, 2018

ፍጻሜዬን አስታውቀኝ

አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ። መዝሙር 39፡4
ይህ የእግዚአብሄር ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡ ይህ በምድር ላይ ያለው ጊዜ አጭር መሆኑን የተረዳ ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡ ይህ በምድር ላይ ሊሰራ ያለው ስራ ሸክም በውስጡ የሚጮህበት ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡
ሰው በምድር ላይ የሚኖረው አንድ ጊዜ ነው፡፡ ሰው በምድር ላይ የሚኖረው በጣም ለአጭር ጊዜ ነው፡፡ ሰው በምድር ላይ ሚሊየን ቀን አይኖርም፡፡ ሰው በምድር ላይ 120 አመት ቢኖር 43830 ቀናት ነው በምድር ላይ የሚኖረው፡፡ ይህ አጭር የምድር ኑሮ በሚገባ ብንጠቀምበትም ባንጠቀምበትም ማለፉ አይቀርም፡፡ በምደ ያለው ህይወታችን በፍሬያማነት ብንጠቀምበትም ባንጠቀምበትም ወደኋላ ማጠንጠን እንችልም፡፡ ሚያዚያ 26 2010 ተመልሶ አይመጣም፡፡   
በህይወታችን መድረስ የምንፈልገውን ብዙ ነገሮችን ስናስብ ብዙ ጊዜ በምድር ላይ ያለው ህይወታችን ውስን መሆኑን እንረሳለን፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ከመካከላችን ሲጠራ የምንደነግጠው፡፡ ሞት ሁልጊዜ አዲስ የሚሆንብን በተለያዩ ነገሮች ባተሌ ስለሆንንና በምድር ላይ ያለን ኑሮ አጭር መሆኑን ስለምንረሳ ነው፡፡
መዝሙረኛው እንዲህ እያለ ነው፡፡ ዘመኔ አጭር መሆኑን ከረሳሁ ዘመኔን በአግባቡ መጠቀም አልችልም፡፡ ዘመኔ አጭር መሆኑን ከረሳሁ በከንቱ የማባክነው ጊዜ ይበዛል፡፡ ዘመኔ አጭር መሆኑን ካላወቅኩ መልሼ የማላገኘው በስንፍና የማሳልፈው ጊዜ ይበዛል፡፡ ዘመኔ አጭር መሆኑን ካላስብኩ ቅድሚያ በጥሪዬ ላይ ብቻ አላተኩርም፡፡ ዘመኔ አጭር መሆኑን ካላወቅኩ ቅደሚያ በሚሰጠው ላይ ብቻ ለማተኮርና ቅድሚያ ለመስጠት አላስብም አላቅድም፡፡ ዘመኔ አጭር መሆኑን ካላወቅኩ በእቅድና በጥንቃቄ አልኖርም፡
መዝሙረኛው እያለ ያለው በምድር ዘላለም እንደማልኖር ካወቅኩ ጊዜዬን በአግባቡ እጠቀምበታለሁ፡፡ በምድር ላይ ያለው ዘመኔ አጭር እንደሆነ ካወቅኩ ቅድሚያ በሚሰጠው ነገር ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፡ በምድር ላይ ያለው ኑሮዬ ውስን መሆኑን ካወቅኩ የማባክነው ጊዜ አይኖርም፡፡ በምድር ላይ ያለው ጊዜዬ አጭር መሆኑን ከተረዳሁ ውስን የሆነው ጊዜዬን በህይወት አላማዬ ላይ ብቻ አጠፋለሁ፡፡ በምድር ላይ ያለው ጊዜዬ አጭር መሆኑን ከተረዳሁ ያለኝን ጊዜ በጥበብ ለመጠቀም እወስናለሁ፡፡
ይህ የሁላችንም የልብ ጩኸት ሊሆን ይገባል፡፡ እግዚአበሄ በዚህ ቀን ነው የምተጠራው ላይለን ይችላል፡፡ ነገር ግን አጭር መሆኑን እንዳንረሳና ካላግባብ እንዳንዝናና ይፈልጋል፡፡
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ። መዝሙር 394
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ዘመን #ፍፃሜ #አጭር #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment