እንግዲህ
ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና። ማቴዎስ 7፡12
የእግዚአብሄር
ትእዛዞች ከባዶች አይደሉም፡፡ የእግዚአብሄርን ትእዛዞች ማድረግ ከፈለግን ማድረግ እንችላለን፡፡ ማድረግ የማንችላቸው የእግዚአብሄር
ትእዛዞች የሉም፡፡ እግዚአብሄር ካዘዘ ማድርገ እንችላለን ማለት ነው፡፡
ትእዛዛቱን
ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 1ኛ ዮሐንስ 5፡3
የእግዚአብሄር
ትእዛዞች ውስብስብና ለመረዳት አስቸጋሪ አይደሉም፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ለመረዳት እና እግዚአብሄርን ለማስደሰት አራት አመት
ስነመለኮት መማር የለብንም፡፡
ማንም
ሰው የእግዚአብሄርን ትእዛዝ መረዳት ይችላል፡፡
ለምሳሌ
‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ ማቴዎስ 22:39 የሚለውን ትእዛዝ ለመረዳት ሰው ብዙ ቦታ መውጣት መውረድ የለብንም፡፡ ባልንጀራህን
እንደራስህ አድርገህ ውደደ የሚለውን ትእዛዝ ለመረዳት ሰው ራሱን እንደ እንደሚወድ መመለከት በቂው ነው፡፡ ሰው ራሱን አይጠላም፡፡
ሰው ለራሱ ክብር አለው፡፡ ሰው ራሱን ይወዳል፡፡
ትእዛዙ
ታዲያ ለራስህ ክብር እንዳለህ ለሌላው ክብር ይኑርህ ነው፡፡ ትእዛዙ ለራስህ ፍቅር እንዳለህ ለሌላው ፍቅር ይኑርህ ነው፡፡
ሰው
እንዲያከብርህ እንደምትፈልገው ሁሉ ሰውን አክብር፡፡ ሰው እንዳይንቅህ እንድምትፈልገው ሁሉ ሰውን አትናቅ፡፡ ሰው እንዲሰማህ እንደምትፈልገው
ሁሉ ሰውን ስማ፡፡ ሰው እንዲያዋርድህ እንደማትፈልገው ሁሉ ሰውን አታዋርድ፡፡ ሰው እንዲያማህ እንደማትፈልገው ሁሉ ሰውን አትማ፡፡
ሰው በችግርህ እንዲረዳህ እንደምትፈልግ ሰውን በችግሩ እርዳ፡፡ ሰው እስከድካምህ እንዲቀበልህ እንደምትፈልግ ሰውን እስከድካሙ ተቀበል፡፡
ሰው ሊያደርግልህ የምትፈልገውን ለሰው አድርግ፡፡
ሰዎችም
ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው። ሉቃስ 6፡31
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ፍቅር #መውደድ #የህግፍፃሜ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ዲዛይን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ራስንመውደድ #መንፈስቅዱስ #ራስንማክበር #ልብ #መሪ
No comments:
Post a Comment