Popular Posts

Follow by Email

Thursday, June 1, 2017

የግንኙነት መለኪያ - ምስጋና

ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡23
ምስጋና እግዚአብሄር ስለደረገልን መልካምነት ምላሽ ከመስጠት ያልፋል፡፡ ምስጋና ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን የግንኙነት ደረጃ ያሳያል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኘነት ጤንነት ማወቅ ከፈለግን ምስጋናችንን መለካት ይጠይቃል፡፡
ምስጋና የሚሰዋ እርሱ ያከብረኛል ይላል፡፡ ምስጋና እግዚአብሄርን ማክበራችን ያሳያል ማለት ነው፡፡ ምስጋና ለእግዚአብሄር የመጀመሪያውን ስፍራ መሰጠታችንን ያሳያል፡፡ ምስጋና የተፈጠርንለትን አላማ እየፈፀምንም መሆናችንን ያሳያል፡፡
ምስጋና ስለ ትህትናችን ይናገራል
ምስጋና የልባችንን ትህትና ይገልጣል፡፡ ትሁት የሆነ ሰው እግዚአብሄር ላይ ለማጉረምረም ምክኒያት አያገኝም፡፡ ትሁት የሆነ ሰው እግዚአብሄር ከእኔ በላይ ያውቃል ይላል፡፡ ትሁት ሰው እኔ የማላውቀው ነገር አለ ይላል፡፡ ትሁት ሰው እግዚአብሄር የሚሰጠው አያንስበትም ይበቃዋል፡፡ ትሁት ሰው እግዚአብሄር የሚሰጠው ጥቂት ነገርን እንኳን እንደሚገባው አይቆጥረውም፡፡  ትሁት ሰው እያንዳንዱን መልካምነት አቅልሎ አያየውም፡፡
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡7
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያዕቆብ 1፡16-17
ምስጋና እግዚአብሄርን ስለመፍራታችን ይናገራል
ምስጋና እግዚአብሄርን እንደምንፈራው ያሳያል፡፡ ምስጋና ለእግዚአብሄር ያለንን ፍርሃትና አክብሮት ያሳያል፡፡ ለእግዚአብሄር የተለየ ክብር ያለው ሰው በእግዚአብሄር ፊት ምስጋናን እንጂ ማጉረምረም ሊያወጣ አይችልም፡፡
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14-15
ምስጋና በእምነት መኖራችነንን ያሳያል፡፡ ምስጋና የምንመላለሰው በማየት ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ያሳያል፡፡ እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ ካመንን እግዚአብሄርን ለማመስገን እንችላል፡፡
ምስጋናችን በእግዚአብሄር ደስታ መርካታችንንና አለምን መናቃችንን ያሳያል
ሰው ሃጢያት የሚሰራው የእግዚአብሄር ደስታ ወይም እቅርቦት አልበቃ ብሎት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ደስ የተሰኘ ሰው ግን ሃጢያትን ይንቃል፡፡ ከሃጢያት መራቃችን በእግዚአብሄር መርካታችንንና የሚያመሰግን ልብ እንዳለን ያሳያል፡፡
አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን። ዕብራውያን 13፡5-6
ምስጋና እግዚአብሄርን ማወቃችንን ያሳያል
ምስጋና የእግዚአብሄን አሰራር መረዳታችንን ያሳያል፡፡ የእግዚአብሄርን አሰራር ያልተረዳ ሰው ሁል ጊዜ ጥያቄ አለው ሁል ጊዜ ያጉረመርማል፡፡ ምስጋና የሚሰጥ ሰው ግን የእግዚአብሄርን አሰራር የተረዳ ሰው ነው፡፡
 በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡18
ምስጋና በእግዚአብሄር ላይ መደገፋችንን ይመሰክራል
ምስጋና በማናውቅው ነገር እንኳን በእግዚአብሄር ላይ መደገፋችንን ያሳያል፡፡ የጠበቅነው ነገር ሳይሆን ያልጠበቅነው ነገር ሲሆን በእውቀታችን ላይ ሳይሆን በእግዚአብሄር ላይ ተደግፈን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

No comments:

Post a Comment