Popular Posts

Thursday, May 31, 2018

ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ

እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡10-11
ሰዎች በህይወት ብዙ ግቦች ይኖራቸዋል፡፡ ሰዎች እነዚህን ግቦች ለመምታት ይደክማሉ ይወጣሉ ይወርዳሉ፡፡ ሰዎች የህይወት አላማ ለማሳካት ብዙ ነገሮችን ይተዋሉ፡፡ ሰዎች የህይወት አላማቸውን ለማሳካት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡
ሰዎች በምድር ላይ ስኬታማ የሚያደርጋቸውን እውቀት ለማግኘት ቀን ከሌሊት ይደክማሉ፡፡ ሰዎች አካባቢያቸውን ለመረዳት መፅሃፍትን ያነባሉ፡፡ ሰዎች የህይወት ክህሎት ለማግኘት አዋቂ ሰዎችን ይሰማሉ፡፡ ሰዎች በህይወት ስኬታማ የሚያደርጋቸውን እውቀት ለማግኘት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡ ሰዎች የህይወትን ተግዳሮት ተቋቁመው ለማለፍ ያስችላል የሚባልን እውቀት ከማግኘት ወደኋላ ላለመቅረት የሚቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡  
ሰዎች ስለሰዎች ባህሪ ለማወቅ እና በሚገባ ከሰዎች ጋር ለመኖር የሚያስችላቸውን የሰውን አያያዝ ጥበብ ለማወቅ እውቀትን ይመረምራሉ፡፡ ሰዎች በንግዳቸው የተሳካላቸው ለመሆን ንግዳቸውን እንዴት እንደሚያስተዳድሩት ሌት ተቀን ያስባሉ፡፡ ሰዎች በገንዘብ ነፃነት ውስጥ ለመግባት የገንዘብ አያያዝ ችሎታቸውን ለማጎልበት እውቀትን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች ትዳራቸውን በትክክል ለመስራት በትጋት መጽሃፍትን ያነባሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ እውቀቶች የሚያስፈልጉ ናቸው፡፡ ይህ እውቀት ግን ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ እውቀት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ እውቀቶች ግን ወደዚህ እውቀት የሚደርሱ እውቀቶች አይደሉም፡፡
ሃዋሪያው ኢየሱስንና ትንሳኤውን ሃይል ማወቅ ከሁሉ የሚበልጥ እውቀት ይለዋል፡፡  
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ፊልጵስዩስ 3፡8
ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ እውቀት አለ፡፡ የሃዋሪያው ጳውሎስ የህይወት ግቡ ከሁሉ የሚበልጠውን እውቀት ኢየሱስን ማወቅ ነበር፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ ሰዎች የሚያከብሩዋቸውንና ዋጋ የሚሰጡዋቸውን ነገሮች ሁሉ እንደምናምንቴ የሚቆጥረው ኢየሱስንና የትንሳኤውን ሃይል ለማወቅ ነው፡፡
ሃዋርያው ይህን ኢየሱስንና የትንሳኤውን ሃይል ለማወቅ በብዙ ነገሮች ውስጥ ለማለፍ ዝግጁ ነበር፡፡ ሃዋሪያው ኦየሱስንና የትንሳኤውን ሃይል ለማወቅ የማይከፍለው ነገር የለም፡፡  
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#የሚበልጥ #እውቀት #ጥበብ #ነፍስ #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፀጋ #መልካም #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አእምሮ #ሰላም #ማስተዋል #ልጅ

No comments:

Post a Comment