Popular Posts

Friday, May 11, 2018

የእናትህንም ሕግ

ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል። ምሳሌ 6፡20
ሰው ሞኝነቱ በግልፅ የሚታወቅው እናቱን ሲንቅ ነው፡፡
ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል። ምሳሌ 15፡20
እናቱን የማይንቅና የሚሰማ ሰው ጥበበኛ ነው፡፡ በእናቱ የተጠራቀመ ጥበብ የሚጠቀም ሰው ጥበበኛ ነው፡፡ እናቱ የማታውቅ የማይመስለው ሰው ጥበበኛ ነው፡፡ በእናቱ ርህራሄ ተጠቃሚ የማይሆን ሰው ሞኝ ሰው ነው፡፡
እናት ስትናገር ከርህራሄ ትናገራለች፡፡ እናት ስትናገር ከጥንቃቄ ትናገራለች፡፡ እናት ስትናገር ከሸክም ትናገራለች፡፡ የእናቱም ምክር የበቀላሉ የሚያሳልፍ ሰው ታላቅ ሃብትን ያሳልፋል፡፡
እናቶች የሚሰራበትንና የማይሰራበትን መንገድ በተግባር ኖረው አይተውታል፡፡ እናቶች ልጆች ለሚጓጉለት ነገር ሁሉ አይጓጉም፡፡ እናቶች ከልጆች ያለፈን ነገር ያያሉ፡፡
እናቱን የማይንቅና የሚታዘዝ ሰው መልካም ይሆንለታል ዘመኑም ይረዝማል፡፡
ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። ኤፌሶን 6፡13
እናቶች ልጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን ወጣቶችን እናቶች በተለያየ መንገድ ያሰለጥናሉ፡፡ እናትነት በተፈጥሮ ልጅ ላይ ብቻ አይወሰንም፡፡ እናትነት ርህራሄ ቸርነት ምህረትን ለሌላው ማድረግ ነው፡፡ እናትነት እንክብካቤ ነው፡፡ እናትነት አዘኔታ ነው፡፡ እናትነት መርዳት መደገፍ ነው፡፡ እናትነት መምከር ማስተማር በርህራሄ መምራት ነው፡፡    
እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው። ቲቶ 2፡3-5
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር #ሴት #እናትነት #ጌታ #መከተል #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ  #ቃል #ደግነት #ቸርነት #እግዚአብሔርንመምሰል #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment