I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
Live soberly and be vigilant, for the devil, who is not your partner, prowls around like a roaring lion looking for someone to devour. Re...
-
የህይወት ስኬት የሚመጣው ለእግዚአብሄር ቃል የመጀመሪያውን ስፍራ በመስጠትና በቃሉ ከባቢ ውስጥ ለመኖር በመወሰን ነው፡፡ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ...
-
የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16 ወንጌል በሃጢያታቸው ምክኒያት ለዘላለም ከእ...
-
A group of alumni, highly established in their careers, got together to visit their old university professor. Conversation soon turned in...
-
ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢታንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር። ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድም...
-
ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23 ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ያለን ቦታ እንዴት ልዩ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን ክብር እንዴት ድንቅ ነው፡...
-
We are created to be free moral beings. Man thinks before he decided to do something. He only does what he decided to do. For as he ...
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
-
ክርስትና ስር ነቀል የህይወት ለውጥ ነው፡፡ ክርስትና ጌታን መከተል ነው፡፡ ክርስትና ጌታ በቃሉ ያዘዘንን መፈፀም ነው፡፡ ጌታ በቃሉ የከለከለውን አለማድረግ ነው፡፡ ከሰሞኑ ዘፈን ሃጢያት ነው? አይደለም? የሚሉ ክር...
Tuesday, June 29, 2021
Tuesday, June 22, 2021
ለፀፀት እንቢ እንበል!
ፀፀት አንድ ሰው በሠራው ነገር ወይም አንድን ነገር ባለማድረጉ የሚሰማው የሐዘን ወይም የቁጭት ስሜት ነው፡፡
ህይወት በውሳኔ የተሞላ ነው፡፡ በህይወታችን በየደቂቃውና
በየሰከንዱ ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር በመለየት ሂደት ብዙ ውሳኔዎችን እንወስናለናን፡፡ በህይወታችን ትንሽ ከሚባለው ነገር ጀምሮ
ትልቅ እስከሚባለው ውሳኔ ድረስ አማራጮችን አመዛዝነን ውሳኔዎችን እንወስናለን፡፡
በየቀኑና በየደቂቃው አንድን ነገር ለማድረግ ወይም
ላለማድረግ መወሰን ተፈጥሮአዊ ግዴታ ነው፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ በወሰንን በዚያው ቅፅበት ሌላውን አማራጭ ላለማድረግ እየወሰንን
ነው፡፡ አንድን ነገር ላለማድረግ በወሰንን ቅፅበት ሌላውን አማራጭ ለማድረግህ እየወሰንን ነው፡፡
ውሳኔ ስንወስን ያለንን እውቀት ፣ ማስተዋል እና
ጥበብ ሁሉ ተጠቅመን እንወስናለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የምንወስነው ላለንበት ጊዜ እና ላለንበት ሁኔታ የተሻለውንና ትክክል የሆነውን
ውሳኔ ነው፡፡ ለነበርንበት ሁኔታ ከዚያ ከወሰነው ውሳኔ በላይ ልንወስን እንችልም ነበር፡፡
ታዲያ ችግሩ የሚመጣው የህይወት ተግዳሮት ሲደርስብን
አንድ ቀን የወሰንነውን ውሳኔ መጠራጠር ስንጀምር ነው፡፡
ልጆች ሆነን አደጋ ስለ ደረሰበት ልጅ ወላጆቻችን
ሲያወሩ እንሰማ ነበር፡፡ ታዲያ ልጁ አደጋ ሳይደርስበት በፊት የጠየቀው ጥያቄ ፣ የፈለገው ፍላጎት እና የለመንው ልመና ሁሉ ለፀፀት
ምክኒያት ሆኖ ሲቀርብ እንሰማ ነበር፡፡ ልጁ ሱቅ ከመላኩ በፊት እማዬ ርቦኛል ብሎ እናቱ ምሳ አልደረሰም ስትመጣ ትበላለህ ብላው
ከሄደ ምነው በሰጠሁትና በበላ ኖሮ ብላ ትፀፀታለች፡፡
ደግም እንፀፀት ካልን የማይፀፅት ነገር የለም፡፡
ለፀፀት ፊት ከሰጠነው በቁማችን ሊውጠን የሚችል ክፉ ሃይል ያለው ነገር ነው፡፡
የሰውን ህይወት ለመስረቅ ለማረድና ለማጥጭፋት
ፀፀተን የሚጠቀመው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን እኛን ለማሰቃየት ብዙ የህይወትን ተግዳሮት ያለፍንባቸውን ውሳኔዎች አይጠቀምባቸውም፡፡
በህይወታችን የወሰናቸውን አያሌ ውሳኔዎች እኛን ፀፀት ውስጥ ለመክተት ብዙ ጊዜ አይመቹትም፡፡
ነገር ግን የሰይጣን ብቸኛ አላማ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ስለሆነ እንደ አጋጣሚ
ከውሳኔያችን በኋላ የተፈጠረውን ነገር ግን ከውሳኔያችን ጋር ምንም የማይገናኘውን ሁኔታ እያስታወሰ ሊያሰቃየን ይሞክራል፡፡ የሰይጣን
አላማ እኛን ዝቅ ዝቅ ማድረግህ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ እኛን በፀፀት ሽባ እድርጎ ዛሬን እና ነገን ለእግዚአብሄር እንዳንኖር ማድረግ
ነው፡፡
እግዚአብሄር ይመራናል ያስጠንነቅናል እንጂ በፀፀት አያሰቃየንም፡፡
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን
ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10
አብዛኛውን ጊዜ የምንንፀፀትበት ነገር እግዚአብሄር የሌለበት ነገር ነው፡፡ የእግዚአብሄር
መንፈስ ወቀሳ የሚያበረታታ ፣ የተሻልን ሰዎች እንድንሆን የሚያደርግ እና የተሻለ አድርጎ የሚያስነሳ እና ተስፋ የሚሰጥ እንጂ ባለፈው
ህይወታችን ውስጥ በፀፀት በመኖር ዛሬን እና ወደፊታችንን እንድናባክነው የሚያደርግ አይደለም፡፡
ለፀፀት እንቢ እንበል!
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ፀፀት #መካድ #መታለል #ታማኝነት #ክህደት #ንስሃ #ሃዘን #መመለስ #መሰደድ #ሃዋሪያዊ #መውደቅ #አለመመረጥ #ተቀባይነትማጣት #ዋጋአሰጣጥ #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አምልኮ #እምነት #መከተል
Wednesday, June 9, 2021
መተቸት በጣም ቀላል ነው ፡፡ ሰዎች ሲተቹ እሰማለሁ እናም ስለ መሪዎቻችን እንደማይጸልዩ አውቃለሁ; ስለ ሌሎች በምንጸልይበት ጊዜ እነሱን ለመንቀፍ በጣም ተስማሚ አይደለንምና ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ግን ፖለቲካን ከክርስቶስ በፊት ማስቀደም የለብንም ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከመጠን በላይ በፖለቲካ አስተሳሰብ ውስጥ በመያዛቸው የተነሳ ጥሩ መንፈሳዊ ሰዎች መሆን አይችሉም ፡፡ ኬኔዝ ኢ ሀጊን የሚማልዱ ክርስትያኖች It's so easy to criticize. I hear people criticize and I know they are not praying for our leaders; for when we pray for others we are not so apt to criticize them. As Christians, however, we are not to put politics before Christ. Some people are so politically minded they are no good spiritually. Kenneth E Hagin The Interceding Christians
መተቸት
በጣም ቀላል ነው ፡፡ ሰዎች ሲተቹ እሰማለሁ እናም ስለ መሪዎቻችን እንደማይጸልዩ አውቃለሁ; ስለ ሌሎች በምንጸልይበት ጊዜ እነሱን ለመንቀፍ በጣም ተስማሚ አይደለንምና ፡፡
እኛ
ክርስቲያኖች ግን ፖለቲካን ከክርስቶስ በፊት ማስቀደም የለብንም ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከመጠን በላይ በፖለቲካ አስተሳሰብ ውስጥ በመያዛቸው የተነሳ ጥሩ መንፈሳዊ ሰዎች መሆን አይችሉም ፡፡ ኬኔዝ ኢ ሀጊን የሚማልዱ ክርስትያኖች
It's
so easy to criticize. I hear people criticize and I know they are not praying
for our leaders; for when we pray for others we are not so apt to criticize
them.






