Popular Posts

Saturday, May 26, 2018

ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል

እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው። ሉቃስ 19፡46
ኢየሱስ ስለ እግዚአብሄር ቤት የተናገረው ንግግር ልቤን ይነካኛል፡፡ ስለእግዚአብሄር ቤት ስናስብ ብዙ ነገር እናስባለን፡፡
ስለእግዚአብሄር ቤት ስናስብ ስለእግዚአብሄር ቃል ትምህርት እናስባለን፡፡ ትክክል ነው የእግዚአብሄር ቤት የእግዚአብሄር ህዝብ የእግዚአብሄርን ቃል የሚማርበት ህብረት ነው፡፡   
በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር። የሐዋርያት ሥራ 2፡42
ስለእግዚአብሄር ቤት ስናስብ የእግዚአብሄር ህዝብ እግዚአብሄርን የሚያመልክበት ቦታም እንደሆነ እናስባለን፡፡ የእግዚአብሄር ቤት የእግዚአብሄር ህዝብ ጌታውን እግዚአብሄርን የሚያመልክበትና የሚያመስግንበት ለእግዚአብሄር የሚዘምርበት ህብረት ነው፡፡
በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ ኤፌሶን 5፡19
ስለእግዚአብሄር ቤት ስናስብ የእግዚአብሄር ቤት የመንፈቅ ቅዱስ ስጦታዎችን የምንለማመድበት ቤት እንደሆነ እናስባለን፡፡ እውነትም ነው ስንሰበሰብ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ይሰራሉ፡፡
በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ ሁሉ ለማነጽ ይሁን። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡26
ኢየሱስ ስለ ቤቱ ሲናገር ቤቴ የፀሎት ቤት የጸሎት ቤት ይሆናል ነው ያለው፡፡ የእግዚአብሄር ቤት ህብረት የፀሎት ህብረት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቤት ህብረት ሰዎች ፀልየው ከእግዚአብሄር የሚቀበሉበት ህብረት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስትያን ህብረት ሰዎች እግዚአብሄርን በህብረት ፈልገው የሚያገኙበት ህብረት ነው፡፡
ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። ማቴዎስ 18፡19-20
የማይፀልይ ክርስትያን ደካማ ክርስትያን እንደመሆኑ መጠን የማትፀልይ ቤተክርስትያን ደካማ ቤተክርስትያን ነች፡፡ የማይፀልይ ክርስትያን የእግዚአብሄር ሃይል እንደሚያጥረው ሁሉ የማትፀልይ ቤተክርስተያን የእግዚአብሄርን ሃይል በሰው ክንድ የምትለውጥ ቤተክርስተያን ነች፡፡ የማይፀልይ ክርስትያን እንደሚፍገመገም ሁሉ የማትፀልይ ቤተክርስትያን የማትፀጸና ቤተክርስትያን ነች፡፡
የእግዚአብሄር ቤተክርስትያን ካለማቋረጥ የእግዚአብሄር እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ህብረት ነች፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስትያን በእግዚአብሄር ሃይል ብቻ የሚታመኑ ሰዎች ስብስብ ነች፡፡   
እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አጥብቆ #ፀሎት #ልመና #ቤቴ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሃይለ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና

No comments:

Post a Comment