Popular Posts

Friday, May 18, 2018

ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ሮሜ 14፡17
የእግዚአብሄር መንግስት የቁሳቁስ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የሚበላና የሚጠጣ ጉዳይ አይደለም፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት ከፍ ያለ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የመንፈስ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የእግዚአብሄርና የልጆቹ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የነገስታት ቤተሰብ መንግስት ነው፡፡
ለእግዚአብሄር መንግስት በሚበላና በሚጠጣ መጋጨት አይመጥነውም፡፡
የእግዚአብሄር መንግስ አትቅመስ አትንካ በሚል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚተዳር መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ስርአት በስርአት የሆነበት መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በስርአት ብዛት ሰዎችን የሚቆጣጠሩበት መንግስት አይደለም፡፡
ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ቆላስይስ 2፡20-21
የእግዚአብሄር መንግስት ልጆቹ በመንፈሱ የሚመሩበት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሰው ከውጭ በስርአትና በህግ ሰውን የሚቆጣጠርበት መንግስት ሳይሆን የእግዚአብሄር መንፈስ እያንዳንዱን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራበት መንግስት ነው፡፡
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡27
የእግዚአብሄር መንግስት ሰው በፍቅር በፈቃዱ ለእግዚአብሄር የሚገዛበት የፍቅር መንግስት ነው፡፡  
የእግዚአብሄ መንግስት ፅድቅ ነው
የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ፊት ትክክል መሆን መፈለግ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ፊት ትክክለኛ አቋም መያዝ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ለእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ብቻ ለመኖር መፈለግ ነው፡፡ የእግዚአብሄ መንግስት ኢየሱስን ፈፅሞ መከተል ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት የሰላም መንግስት ነው
የእግዚአብሄር መንግስት የእረፍት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ላይ የመደገፍ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የፉክክርና የረብሻ መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ረጋ ብለን እግዚአብሄርን እየሰማን የምንኖርበበት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄ መንገስት በረብሻ ጊዜ እንኳን አእምሮን የሚያልፍ ሰላም የምንለማመድበት መንግስት ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት በመንፈስ ቅዱስ የሆነ የደስታ መንግስት ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት የቁሳቁስ ደስታ መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የእርስ በእርስ ፉክክር መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በገንዘብ የመመካት መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በኑሮ የመመካት መንግስት አይደለም፡፡
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሃንስ 2፡15-16
የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ደስ የመሰኘት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ብቻ የመመካት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሁልጊዜ በጌታ ደስ የምንሰኝበት የደስታ መንግስት ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፅድቅ #ሰላም #መንፈስቅዱስ #ደስታ #መብል #መጠጥ ##ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አለም #ሃጢያት #ድምፅ #ቅባት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የህይወትፍሬ #መናገር #ቅባት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment