Popular Posts

Monday, May 14, 2018

የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን

አለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርግ ሰው ግን አያልፍም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እንደማያልፍ ሁሉ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ለዘላም ይኖራል፡፡
ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሃንስ 2፡17
ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ ስጋ ለባሽ ሰው ሁሉ ሳር ነው፡፡ የስጋ ለባሽ ክብር አሁን ታይቶ በኋላ እንደሚጠወልግ እንደምድረበዳ አበባ ነው፡፡ ሳር ጊዜያዊ እንደሆነና እንደሚደርቅ አበባም እንደሚረግፍ የሰው ክብር ይጠፋል፡፡ የአምላክ ቃል ፀንታ እንደምትኖር የእግዚአብሄርን ቃል የሚያደረገ ሰው ግን ለዘላም ይኖራል፡፡   
ጩኽ የሚል ሰው ቃል፤ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። ኢሳያስ 406-8
ሰው ከእግዚአብሄር ቃል ዳግመኛ ካለተወለደ በስተቀር ሰው እንደ ሳር ነው ክብሩም እንደሳር አበባ ነው፡፡ ሰው ለዘላለም ከሚኖረው ከእግዚአብር ቃል ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር ሳሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፡፡ የጌታ ቃል ለዘላለም እንደሚኖር ከእግዚአብሄ የተወለደ ሰው ለዘላለም ይኖራል፡፡
ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡23-25
ሰማይና ምድር ለዘላለም አይኖሩም፡፡ ሰማይና ምድር እንኳን ያልፋሉ፡፡ የእግዚአብሄር ቃልና ቃሉን የሚጠብቁ ሰዎች ግን አያልፉም ለዘላለም ይኖራሉ፡፡
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ማቴዎስ 24፡35
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እንፍዋለት  #ሕይወታችሁ #ዘላለም #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment