Popular Posts

Follow by Email

Friday, May 18, 2018

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ

ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ቆላስይስ 2፡20-21
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚል ትእዛዝ ለእኛ በክርስቶስ አምነን ለዳንን አይገባንም፡፡ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚል ትእዛዝ ለእኛ የማይመጥንበትን ምክነቢያቶች እንመልከት
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ አለማዊ ስርአት ነው
በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጣቸው አይኖርም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄርን ፍቅር አልተረዱም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄር ፍቅር አይመራቸውም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች መንፈሳቸው ሙት ነው፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች በእግዚአብሄር መንፈስ ህያው አልሆኑም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄር ቃል በውስጣቸው የለም፡፡ ስለዚህ አትያዝ ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ትእዛዝ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ ኤፌሶ 2፡1
በአለም ያሉ ሰዎች የሚመሩት አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ስርአት ብቻ ነው፡፡ ሌላ የሚያሸንፍ መንፈስ በውስጣቸው ስለሌለ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ትእዛዝ ብቻ ነው በአለም ያሉትን ሰዎች የሚያሸንፋቸው፡፡ ለእኛ ግን መንፈሳችን ህያው ስለሆነ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ትእዛዝ አያስፈልገንም፡፡ እኛ በኢየሱስ ስለምንኖር ቃሎቹም በውስጣችን ስለሚኖር እግዚአብሄር በመንፈሱ አማካኝነት ይመራናል፡፡  
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የመጀመሪያ ትምህርት ነው
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የመጀመሪያ ትምህርት ነው፡፡ ልጅ መጀመሪያ የነገሮችን ጉዳትና ጥቅም በራሱ ስለማይረዳ ትእዛዘ ይሰጠዋል፡፡ ልጅ በራሱ አነሳሽነት ነገሮችን ለማድርግ ብቃቱን ስላዳበረ ትእዛዝ በትእዛዝ ይሰጠዋል፡፡ ልጅ እራሱ አውቆ ነገሮችን ስለማይሰራ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ተብሎ ይታዘዛል፡፡
ጎልማሳ ሰው ግን ይህ አያስፈልገውም፡፡ የነገሮችን ጥቅምና ጉዳት ስለሚያመዛዘን በራሱ ይወስናል፡፡ በተመሳይ መልኩ በክርስትና የምንመራው በህጉ መንፈስ እንጂ በህጉ ፊደል አይደለም፡፡ ህጉን ተረድተን በገባነ መንገድ እንተረጉመዋለን እንጂ ሰዎች ይህን አድርጉ ይህን አታድርጉ እያሉ እንደህፃን ልጅ እንዲመሩን እንጠብቅም፡፡  ቃሉን ሰምተን የታዘዘው ትእዛዝ ለምን እንደታዘዘ ተረድተን እናደርገዋለን እንጂ በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችን ይህን አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚለን ሌላ ሰው እንጠብቅም፡፡  
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሰው ስርአት ነው
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሰው ስርአት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት አንድ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት ፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት እግዚአብሄርን እና ባልንጀራህን ውደድ ነው፡፡ ትእዛዛት ሁሉ በሁለቱ ትእዛዛት ይጠቃለላሉ፡፡
እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። ሮሜ 12፡8-10
የትእዛዛት ሁሉ አላማ እኛ በፍቅር እንድንኖር መርዳት ነው፡፡
የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡5
ከፍቅር ህግ በላይ የሚጨምር ግን ህጉን ይሽረዋል፡፡
ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። ማርቆስ 7፡13
ለእኛ ግን የእግዚአብሄር ምንፈስ በእናንት ውስጥ ይኖራል እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ነው የምንባለው፡፡
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡20-27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አትያዝ #አትቅመስ #አትንካ #አለማዊ #ስርአት #መጀመሪያ #ፅድቅ ሰላም #መንፈስቅዱስ #ደስታ #መብል #መጠጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አለም #ድምፅ #ቅባት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መሪ

No comments:

Post a Comment