ደግሞ
እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። የማቴዎስ ወንጌል 18፡19-20
ኢየሱስ
በመካከላችን እንዲገኝ የሚያደርገው መጮኻችን አይደለም፡፡ ኢየሱስ በመካከላችን እንዲገኝ የሚያደርገው መለመናችንና ማልቀሳችን አይደለም፡፡
ኢየሱስ
በህዝቡ መካከልና መገኘት አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡ እኛ በመካላችን እንዲገኝና እንዲሰራ ከምንፈልገው በላይ ኢየሱስ በመካካላችን
ተገኝቶ አብሮ በሃይል መስራት ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስ በመካከላችን የሚገኘው እርሱ እንዲገኝ የሚያደርገውን ነገሮችን ስናደርግ ነው፡፡
ኢየሱስ
በመካላችን እንዲገኝ የሚያድርገውን ሁለት ነገሮች እንመልካት፡፡
1.
በአንድ ልብ መሆን
ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር
በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። የማቴዎስ ወንጌል 18፡19
በአንድ ሃሳብ መሆን ኢየሱስ በማካከላችን እንዲገኝ
ያደርገዋል፡፡ አንዱ አንድ ሌላው ሌላ አላማ ካለው ኢየሱስ የተደበላለቀን ነገር ሊሰራ አይገኝም፡፡
በሃዋሪያት ላይ የእግዚአብሄር መንፈስ ከመውረዱ
በፊት በአንድ ሃሳብ ይፀልዩ ነበር፡፡
በዓለ
ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥
ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። የሐዋርያት ሥራ 2፡1-2
ሃዋሪያው ስለዚህ ነው ደስታዬን ፈፅሙልኝ በአንድ
ሃሳብ ተስማሙ እያለ የሚናገረው፡፡
በክርስቶስም
አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ
አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡1-2
2.
የመሰብሰብ አላማ
ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ
በመካከላቸው እሆናለሁና። የማቴዎስ ወንጌል 18፡20
ኢየሱስ በመካከላችን እንዲገኝ መሰብሰባችን
አላማ ያስፈልገዋል፡፡ እንደው ለመሰብሰብ የሆነ መሰብሰብ ኢየሱስ እንዲገኝ አያደርገውም፡፡ ኢየሱስ እንዲገኝ የሚያደርገው መሰብሰብ
በስሙ የሚደረግ መሰብሰብ ብቻ ነው፡፡
በኢየሱስ ስም መሰብሰብ ማለት ደግሞ ስብሰባው
ሲጀመር በኢየሱስ ስም ፕሮግራማንን እንጀምራለን ማለት አይደለም፡፡ በስሙ መሰብሰብ በኢየሱስ ስም ብሎ ከመናገር ያልፋል፡፡
በኢየሱስ ስም መሰብሰብ ማለት ኢየሱስን ወክሎ
መሰብሰብ ማለት ነው፡፡ የኢየሱስ አላማ የእግዚአብሄርንም መንግስት ማስፋፋት እንደሆነ ሁሉ በኢየሱስ ስም መሰብሰብ ለእግዚአብሄር
መንግስት ጥቅምና መስፋት እንሰበሰባለን ማለት ነው፡፡ በኢየሱስ ስም መሰብሰብ ማለት ቤተክርስትያን በምድር ላይ ያለችበትን አላማ
ለማስፈፀም እንሰበሰባለን ማለት ነው፡፡ በኢየሱስ ስም መሰብሰብ ማለት እኛ የኢየሱስ ተከታዮች ደቀመዛሙርት በምድር ላይ ያለንን
የእግዚአብሄርን መንግስት እና ፅድቁን የመፈለግ አላማ ለማስፈፀም እንሰበሰባለን ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ
በመካከል እንዲገኝ የሚያደርገውን የልብ አንድነትና የእግዚአብሄር መንግስት አላማ ከተሟላ ኢየሱስ እራሱ ይገኛል፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ልጅነት #መገኘት #ህልውና #ቃል #ህልዎት #አንድነት #በስሜ #በኢየሱስስም #ፅድቅ #የጌታመንፈስ #አብሮነት #ክብር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ምስክርነት #አማርኛ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነፃነት #ሞገስ #እርፍት #እርካታ #አርነት #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #ፌስቡክ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment