እግዚአብሄር ቸር አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር
የማንንም እድገት አይጠላም፡፡ እግዚአብሄር የማንንም ደስታ አይቃወምም፡፡ እግዚአብሄር የነጻነት አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር በእኛ
ላይ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡
እግዚአብሄር የህግን ብዛት ዘርዝሮ ሰዎችን አሳስሮ
የሚያስቀምጥ የስጋት አምላክ አይደለም፡፡
የእግዚአብሄር ትእዛዞች ከባዶች አይደሉም፡፡
ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።
1ኛ ዮሐንስ 5፡3
ሰው በነፃነት እንዲሰራ ፣ እንዲያድግና እንዲለወጥ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሄር እጅግ ረቂቅ ከመሆኑ የተነሳ እግዚአብሄርን ለማስደሰት በስነመለኮት
ዲግሪ ማግኘት ፣ ብዙ መፅሃፎችን ማንበብና ብዙ የምርምር ስራዎችን መስራት አይጠይቅም፡፡ እግዚአብሄርን ማስደሰት ሊደረስበት የማይቻል
ውስብስብ ነገር አይደለም፡፡
ሰው እግዚአብሄር የሚፈልገውን ይህን አንድ ነገር ካደረገ ባለው እውቀት ተጠቅሞ
እግዚአብሄርን ማስደሰት ይችላል፡፡
እግዚአብሄር አንድ የሚጠይቀው ነገር ግን አለ፡፡ ሰው ሌላ ምንም ነገር ባያደርግ
ይህንን ነገር ግን እንዲያደርግ እግዚአብሄር ይጠብቃል፡፡
የትእዛዛት መደምደሚያ ይህ ነው፡፡ የትእዛዛት ሁሉ አላመ ሰው እግዚአብሄን በመፍራተ
እንዲኖር ነው፡፡ የሰው ሃላፊነቱ ሁሉ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት ትእዛዙን መጠበቅ፡፡
የነገሩን
ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መክብብ 12፡13-14
ምክኒያቱም
እግዚአብሄር የሰውን ስራ ሁሉ ወደፍርድ ያመጣዋል፡፡ እግዚአብሄር የተሰወረውን መልካምም ይሁን ክፉ ስራ ወደፍርድ ያመጣዋል፡፡
ሰው
እግዚአብሄርን በመፍራት እስካደረገው ድረስ በነጻነት መኖር መስራት መውጣትና መግባት ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #ክፉ #መልካም #ፍርድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#እምነት
#ቃል #ማደስ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment