እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20
ንስሃ የመፅሃፍ ቅዱስ ዋና አስተምሮ ነው፡፡
ንስሃ የክርስትና ዋና ትምህርት ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ ትምህርትም ነው፡፡ ሰው የንስሃ
ትምህርት ካልገባው እስከሚገባው መማር አለበት እንጂ ወደ ሌሎች ትምህርቶች ፈጥኖ ማለፉ ዋጋ የለውም፡፡ ሰው ንስሃ ካልገባው ክርስትና
አይገባውም፡፡
ዴሪክ ፕሪንስ የተባሉት በብዙ የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የሚጠቀሱት ታዋቂው የመፅሃፍ
ቅዱስ አስተማሪ ስለንስሃ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ በቤተክርስትያን ውስጥ አጅግ አስቸጋሪ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች እንደሆኑ ፣
በቤተክርስትያን የማያድጉ እና የማይለወጡ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች እንደሆኑ እና በቤተክርስትያን ፍሬን የማያፈሩ ሰዎች ንስሃ
ያልገቡ ሰዎች እንደሆኑ ተናግረው፡፡
በክርስትና በቆየሁበት ዘመን ይህንን ተመልክቻለሁ አባባላቸው እውነት እንደሆነ እኔም
እመሰክራለሁ፡፡
ክርስቲያን መስሎ ነገር ግን ንስሃ የማይገባ ሰው እግዚአብሔርን ለማሞኘት አንደሚሞክር
ሰው ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ
ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ
#ንስሃ #አእምሮንማደስ
#አሳብንመቀየር
#መንገድንመቀየር #በረከት #ቤተክርስቲያን
#መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ክርስትና
No comments:
Post a Comment