Popular Posts

Friday, May 25, 2018

የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ

ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። ማቴዎስ 4፡1-3
ሰይጣን አላማው አልተለወጠም፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊርድ ሊያጠፋ እንጂ ስለሌላ አይመጣም፡፡ ሰይጣን እኛንም የሚፈትነን ኢየሱስን በፈተነበትን ፈተና ነው፡፡ ኢየሱስ ተርቦ ባየ ጊዜ ሰይጣን የኢየሱስን የእግዚአብሄር ልጅነት ዝቅ ዝቅ የሚያደርግበት እድል ያገኘ መሰለው፡፡ ኢየሱስ ተርቦ ሲያየው ሰይጣን የእግዚአብሄር ልጅነቱን ሊያስክደው የሚችልበት በቂ ምክኒያት ያገኘ መሰለው፡፡ ኢየሱስ ተርቦ ያገኘው ሰይጣን የመንፈሳዊነትን ትኩረት ሊያስለውጠው ፈለገ፡፡
ኢየሱስ የእግዚአብሄር ቃልን የተሞላ ስለነበረ ለሰይጣን ፈተና በቂን መልስ መለሰ፡፡ አሁንም የእግዚአብሄር ቃል ካለን ከፈተና እናመልጣለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ከሌለን ግን በሰይጣን ማታለል እንወድቃለን፡፡
የሰይጣን ፈተና ኢየሱስ ከደረሰበት ነገርና ካለበት የህይወት ሁኔታ አንፃር አይ ተሳሰቼ ነው የእግዚአብሄር ልጅ አይደለሁም ብሎ እንዲክድ ማድረግ ነበር፡፡ አሁንም ሰይጣን እኛን የሚፈትነን እንደዚሁ ነው፡፡
ሰይጣን የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ብሎ ኢየሱስን እንደፈተነው እኛንም ሰይጣን የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ለምን ውድ መኪና አትነዳም? የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ለምን በመከራ ውስጥ ታልፋለህ? የእግዚአብሄር ልጅህ ከሆንክ ለምን ትደክማለህ? የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ለምን ሰው ይጠላሃል? የእግዚአብሄ ልጅ ከሆንክ ለምን ትልቅ ቤት ውስጥ አትኖርም? የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንል ለምን በገንዘብ ሚሊየነር አልሆንክም? የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ለምን ዝነኛ አትሆንም? የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ለምን በከፍታና በዝቅታ ውስጥ ታልፋለህ? ነው የሚለን፡፡
ጥያቄው እነዚህ ከሌሉህ የእግዚአብሄር ልጅ አይደለህም የሚል መልእክትን የያዘ ነው፡፡ ጥያቄው ሰው የሚኖረው በዝናና በሃብት ነው የሚል መልእክት ያዘለ ነው፡፡ ጥያቄው ሰዎች በምድር ላይ የሚሮጡላቸው ነገሮች ከሌለህ ዋጋ የለህም የሚል መልእክት ያለው ነው፡፡   
ኢየሱስ የሰይጣንን ጥያቄ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በማለት በሚገባ መልሶታል፡፡
ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ ነው እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም፡፡ ሰዎች በምድር ላይ የሚፈልጓቸው ዝና ፣ ክብርና ሃብት ሰውን ሊያኖሩ የሚበቁ አይደሉም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረ ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ክብር የተፈጠረ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት እንዲያደርግ በመልኩና በአምሳሉ የተፈጠረ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን እየሰማና እየታተዘ እንዲኖር የተፈጠረ ነው፡፡
ሰው የሚኖረው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡  ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሄር ጋር በሚያደርገው ህብረት ነው፡፡ ሰው የሚኖረው ሰው የሚኖረው በእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የሚኖረው እግዚአብሄርን በመስማትና በመታዘዝ ነው፡፡
የሰይጣን አላማ ሰው የሚኖረው በምን እንደሆነ በመዋሸትና የሰውን ትኩረት በማስለወጥ ነው፡ሸ የሰይጣን አላማ ሰው እነዚህ ነገሮች ከሌሉኝ ብሎ ራሱን እንዲንቅና እንዲያንቋሽሽ ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ሰው ድንጋዩን ዳቦ ባለማድረጉ እውነትም የእግዚአብሄር ልጅ አይደለሁም ማለት ነው እንዲል ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ሰው የሚኖርበትን የእግዚአብሄርን ቃል በቂ እንዳይደለ ማጣጣል ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ሰው በእርሱ ብቻ የማይኖርበትን ሃብት ክብርና ዝና ላይ ብቻ እንዲያተኩትር ማሳሳት ነው፡፡ የሰጣን አላማ ክቡር የሆነው ሰው መኖር የማይችለበት ነገር ላይ አተኩሮ የሚኖርበትን ነገር እንዲተው ትኩረቱን ማዛባት ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #በክርስቶስ #መልክ #አምሳል #የእግዚአብሄርልጅ #ወዳጅ #የንጉስልጅ #ልጅነት ##መንፈስ #ነፍስ  #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን #ዳግመኛመወለድ

No comments:

Post a Comment