ክርስቶስ
ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡5
ክርስቶስ አዳኝ ነው፡፡ ክርስቶስ ጌታ ነው፡፡
ክርስቶስ ሊያድነን ወደምድር የመጣ ነው፡፡ ክርስቶስ አዳኝ ነው፡፡
እኛ በእርሱ ዳንን እንጂ አዳኝ አይደለንም፡፡
ከእርሱ በቀር እኛ በጎነት የለንም፡፡ እኛ ምንም በጎነት ቢታይብን ምንጩ ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡
እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙር 16፡2
ክርስቶስ በምደር ላይ ያለነው የኢየሰስ ስንም
ልንሸከም ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው ኢየሱስ ከፍ አድርገን ልናሳይ ነው፡፡
ክርስቶስ ከፍ ብሎ እንዲታይ እኛ ዘቅ እንላለን፡፡
ክርስቶስን እንዳንሸፍን ራሳችንን እናዋርዳለን፡፡
ሰዎች ከሆነው በላይ እንደሆንን እንዳያስቡ በነገር
ሁሉ እንጠነቀቃለን፡፡
ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡6
ሰዎች በህይወታችን ስለተገለጠው ፀጋ ሲያነሱ እኛ
ደግሞ ሰጪውን እግዚአብሄርን እናነሳለን፡፡ ሰዎች ስለአገልግሎታችን ሲያመሰግኑን እኛ ደግሞ የዚህን ሁሉ ምንጭ ጌታን እናመሰግናለን፡፡
ሰው ራሱን ከሰበከ በምድር ላይ ሊጠቀም ይችላል
ነገር ግን በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋውን በምድር ተቀብሎዋልና በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ የለውም፡፡
ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። ማቴዎስ 6፡1-2
ክርስቶስን እንዲወክል ተልኮ ራስን እንደመስበክ
መሳሳት የለም፡፡ ክርስቶስን ሊሰብክ ተልኮ ራስን እንደመስበክ ኪሳራ የለም፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20
የእኛ
የስኬታችን መጨረሻ ሰዎችን ከጌታ ጋር ማገናኘት ነው፡፡ የመጨረሻው ስኬታችን በሰዎች ውስጥ ክርስቶስን መሳል ነው፡፡
በዓይናችሁ
ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ገላትያ 3፡1
ለህይወት
ሙሉ መፍትሄ ያለው ክርስቶስ በሰዎች ልብ ውስጥ ሲሳል ብቻ ነው የምናርፈው፡፡
ልጆቼ
ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል። ገላትያ 4፡19
ክርስቶስ
በሰዎች ውስጥ መሳሉ የክርስትና ህይወት ግባችን ነው፡፡ ክርስቶስ ነው መፍትሄ ያለው፡፡ ስለዚህ ነው ክርስቶስን እንጂ ራሳችንን
የማንሰብከው፡፡
በመካከላችሁ
ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡2
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት
#ወንጌል #ስብከት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment