Popular Posts

Follow by Email

Thursday, May 31, 2018

በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ

ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10
የእስራኤል ህዝብ በእግዚአብሄር መሪነት ደስተኛ አልነበሩም፡፡ የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄር እንደዚህ አድርጎ ሊይዘን አይገባም ነበር የሚል ጥያቄ ነበራቸው፡፡ የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄር ከዚህ በላይ ሊያደርግልን ይገባል የሚል ቅሬታ ነበራቸው፡፡ የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄ ጠላቶቻችንን እንደዚህ ነበር ማድረግ የነበረበት የሚል የተለየ ሃሳብ አላቸው፡፡ የእስራኤልክ ህዝብ እግዚአብሄር እንደሚገባን አልተንከባከበንም የሚል ጥያቄ ነበራቸው፡፡ ሰው የሚያንጎራጉረው በመሪው ላይ ጥያቄ ሲኖረው ነው፡፡  
ሰው በሚስቴ በባሌ ደስተኛ እይደለሁም ሲል አልገረምም፡፡ ሰው በፍፁሙ በእግዚአብሄር መሪነት ላይ ጥያቄ ካለው ሚስት በባልዋ መሪነት ላይ ጥያቄ ባይኖራት ይገርማል እንጂ የማይገባት ነገር ስላለ አያስገርምም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መሪነት ላይ አቃቂር የሚያወጣ ሰው በሰው መሪነት ላይ አቃቂር ቢያወጣ አያስገርምም፡፡ ሁላችንም በምናውቃቸው ሰዎች መሪነት ላይ አቃቂር ማውጣት እንችላለን፡፡  
የሚያንጎራጉር ሰው በህይወቱ ለሰይጣን በር እየከፈተ ይሄዳል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን መንፈስ እያሳዘነ ይሄዳል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው እደከመ መቋቋም እያቃተው ይሄዳል፡፡ ስለዚህጅ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ አታንጎራጉሩ የሚለው፡፡
ማንጎራጎር ተስፋ መቁረጥ ነው
ማንጎራጎር ተስፋን አለማየት ነው፡፡ ማንጎራጎር ጨለማ ነው፡፡ ማንጎራጎር ተስፋ ቢስነት ነው፡፡
እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፥ በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ። መዝሙር 71፡14
ማንጎራጎር እግዚአብሄር እውነተኛ ዳኛ መሆኑን መርሳት ነው
ማንጎራጎር እግዚአብሄር በወቅቱ እንደማየፈርድ መጠራጠር ነው፡፡ ማንጎራጎር አግዚአብሄር ለመፍረድ የሆነ ነገር እንደጎደለው ማሰብ ነው፡፡  
ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? ያዕቆብ 4፡12
ማንጎራጎር እግዚአብሄርን አለማመስገን ነው
የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄር ምስጋና ያነሰበት ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን መልካምነት ያልተረዳ ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን አሰራር የማያውቅ ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን እርምጃ ያልተረዳ ሰው ነው፡፡  
በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡17-18
ማንጎራጎር በእግዚአብሄር ደስ አለመሰኘት ነው
በእግዚአብሄር ደስ የተሰኘ ሰው ጥያቄውን ዋጥ ያደርገዋል እንጂ ለማንጎራጎር አፉን ለመክፈት አይደፍርም፡፡
ማንጎራጎር በሰው ቁጣ የእግዚአብሄርን ፅድቅ የመስራት ከንቱ ሙከራ ነው፡፡
ማንጎራጎር በእግዚአብሄር መታመን አይደለም፡፡ ማንጎራጎር በራስ ችሎታ መታመን ነው፡፡ ማንጎራጎር የስጋ ክንፍ ነው፡፡  
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። ያእቆብ 1፡19-20
ማንጎራጎር የእግዚአብሄርን መሪነት ጥያቄ ውስጥ መክተት ነው
ምድርን እና ሞላዋን ለራሱ ክብር የፈጠረና እያስተዳደር ያለ ባለቤት እያለ የሚያንጎራጉር ሰው እግዚአብሄር መምራት በትክክል አልቻለም እያለ ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው መሪነቱን ከእግዚአብሄር ተቀብሎ በተሻለ ለማምራት እየተፈተነ ነው፡፡
ማንጎራጎር ባለን ነገር ላይ ሳይሆን በጎደለን ነገር ላይ ማተኮር ነው
እግዚአብሄር በህይወታችን ያደረጋቸው ከቁጥር የበዙ ታእምራቶች እያሉ አልሆነልኝም በምንለው ነገር ላይ ማተኮር ማጉረምረምን ያመጣል፡፡
የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል። ኢዮብ 9፡10
ማንጎራጎር እኔ አውቃለሁ ባይነት ነው
የሚያንጎራጉር ሰው ከእርግዚአብሄር በላይ እንደሚያውቅ የተሰማው ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው እግዚአብሄርን ሊመክርው የሚዳዳው ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው በእግዚአብሄር ያልተረዳውነ አንድ ነገር ያገኘ የመሰለው ሰው ነው፡፡
ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡2
በፊቱ ሙግቴን አዘጋጅ ነበር፥ አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር። የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደ ሆነ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር። ኢዮብ 23፡4-5
ማንጎራጎር ትእቢት ነው
ማንጎራጎር ሰው ከሚገባው በላይ በትእቢት ማሰብ ነው፡፡   
ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡1
ማንጎራጎር እግዚአብሄርን አለመፍራት ነው፡፡
እግዚአብሄርን በትክክል የማያውቀው ሰው ይዳፈረዋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚዳፈር ሰው ለማንጎራጎር ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ላለማንጎራጎር የሚጠይቀውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው። ሰቆቃው ኤርምያስ  3፥29
ተስፋ የሆነው እንደ ሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።  ሰቆቃው ኤርምያስ 3፥26
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡27-28
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #አታንጎራጉሩ #አታጉረምርሙ #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ

እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡10-11
ሰዎች በህይወት ብዙ ግቦች ይኖራቸዋል፡፡ ሰዎች እነዚህን ግቦች ለመምታት ይደክማሉ ይወጣሉ ይወርዳሉ፡፡ ሰዎች የህይወት አላማ ለማሳካት ብዙ ነገሮችን ይተዋሉ፡፡ ሰዎች የህይወት አላማቸውን ለማሳካት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡
ሰዎች በምድር ላይ ስኬታማ የሚያደርጋቸውን እውቀት ለማግኘት ቀን ከሌሊት ይደክማሉ፡፡ ሰዎች አካባቢያቸውን ለመረዳት መፅሃፍትን ያነባሉ፡፡ ሰዎች የህይወት ክህሎት ለማግኘት አዋቂ ሰዎችን ይሰማሉ፡፡ ሰዎች በህይወት ስኬታማ የሚያደርጋቸውን እውቀት ለማግኘት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡ ሰዎች የህይወትን ተግዳሮት ተቋቁመው ለማለፍ ያስችላል የሚባልን እውቀት ከማግኘት ወደኋላ ላለመቅረት የሚቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡  
ሰዎች ስለሰዎች ባህሪ ለማወቅ እና በሚገባ ከሰዎች ጋር ለመኖር የሚያስችላቸውን የሰውን አያያዝ ጥበብ ለማወቅ እውቀትን ይመረምራሉ፡፡ ሰዎች በንግዳቸው የተሳካላቸው ለመሆን ንግዳቸውን እንዴት እንደሚያስተዳድሩት ሌት ተቀን ያስባሉ፡፡ ሰዎች በገንዘብ ነፃነት ውስጥ ለመግባት የገንዘብ አያያዝ ችሎታቸውን ለማጎልበት እውቀትን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች ትዳራቸውን በትክክል ለመስራት በትጋት መጽሃፍትን ያነባሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ እውቀቶች የሚያስፈልጉ ናቸው፡፡ ይህ እውቀት ግን ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ እውቀት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ እውቀቶች ግን ወደዚህ እውቀት የሚደርሱ እውቀቶች አይደሉም፡፡
ሃዋሪያው ኢየሱስንና ትንሳኤውን ሃይል ማወቅ ከሁሉ የሚበልጥ እውቀት ይለዋል፡፡  
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ፊልጵስዩስ 3፡8
ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ እውቀት አለ፡፡ የሃዋሪያው ጳውሎስ የህይወት ግቡ ከሁሉ የሚበልጠውን እውቀት ኢየሱስን ማወቅ ነበር፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ ሰዎች የሚያከብሩዋቸውንና ዋጋ የሚሰጡዋቸውን ነገሮች ሁሉ እንደምናምንቴ የሚቆጥረው ኢየሱስንና የትንሳኤውን ሃይል ለማወቅ ነው፡፡
ሃዋርያው ይህን ኢየሱስንና የትንሳኤውን ሃይል ለማወቅ በብዙ ነገሮች ውስጥ ለማለፍ ዝግጁ ነበር፡፡ ሃዋሪያው ኦየሱስንና የትንሳኤውን ሃይል ለማወቅ የማይከፍለው ነገር የለም፡፡  
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#የሚበልጥ #እውቀት #ጥበብ #ነፍስ #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፀጋ #መልካም #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አእምሮ #ሰላም #ማስተዋል #ልጅ

Wednesday, May 30, 2018

የእምነት ማጣት አስራ አንዱ ምልክቶች

የእግዚአብሄር መንግስት የመንፈስ መንግስት ነው፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምናደርገውን ማንኛውንም ነገር የምናደርገው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም፡፡ ለክርስትና ህይወት እምነት ወሳኝ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚሰራው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚጠቀመው እምነት ያለውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር ለመስራት እምነት ያለውን ሰው ይፈልጋል፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን  ማስደሰት አይቻለም፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ጊዜ ምንም ታላቅ ሃይል ቢኖረውም ሰዎችን ለመርዳት ቢፈልግም እምነት ላልነበራቸው ሰዎች ምንም ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡
በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም። ማቴዎስ 13፡58
እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ ስለ ምን ትፈራላችሁ? ማቴዎስ 8:26
ኢየሱስም መልሶ፦ የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ማቴዎስ 17፡17
ሰው እግዚአብሄርን አላምንም ብሎ ላይናገር ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን የማያምን ሰው ስራው ይናገራል፡፡ እምነት ያለው ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች እንዳሉ ሁሉ የማያምን ሰው የሚያሳያቸው ምልከቶች አሉ፡፡
1.      የማያምን ሰው ጠማማ ነው
የማያምን ሰው ቅን ሊሆን አይችልም፡፡ የማያምን ሰው የዋህ ሊሆን አይችልም፡፡ የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን መንገድ ስለማይከተል የራሱን የጠማማነትን መንገድ ይከተላል፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ማቴዎስ 17፡17
2.     የማያምን ሰው ኩራተኛ ሰው ነው
የሚያምን ሰው የሚታወቀው በትህትናው ሲሆን የማያምን ሰው የሚታወቀው በትእቢቱ ነው፡፡ የማያምን ሰው በእግዚአብሄር ሳይሆን በራሱ ይተማመናል፡፡ የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ላይ ይደገፋል፡፡
እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4
3.     የማያምን ሰው ፈሪ ነው
የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ይደፍራል የማያምን ሰው ግን ፍርሃት አለበት፡፡ በእግዚአብሄር የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ልቡ ስለሚጠበቅ ያርፋል፡፡ የማያምን ሰው ግን ልቡ በምንም ላይ ስለማያርፍ ይፈራል፡፡ የማያምን ሰው የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ የሚያደርገው ከፍቅር ድፍረት ሳይሆን ከፍርሃት ነው፡፡ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ ስለ ምን ትፈራላችሁ? ማቴዎስ 8:26
4.     የማያምን ሰው ፍቅር ይጎድለዋል
የሚያምን ሰው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሄርን ስለሚያምን በፍቅር ለመኖር አይፈራም፡፡ የማምን ሰው ግን የእግዚአብሄርን ፍቅር ስለማያምን እና ስለማይቀበል ራሱም በፍቅር ለመኖር ራሱን አይሰጥም፡፡ የማምን ሰው ከፍቅር ይልቅ ሌላ የራሱን መንገድ ይፈልጋል፡፡
እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡13
5.     የማያምን ሰው በምድር ጥበብ ይመላለሳል
ከእግዚአብሄር የሆነው ንፅህ ጥበብ የሚገኘው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄርን የማያምን ሰው ይህን ንፁህ ጥበብ በምድራዊ ተንኮል ይለውጠዋል፡፡
ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ያዕቆብ 3፡14-16
6.     የማያምን ሰው ይቸኩላል
የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ጊዜ ይተማመናል፡፡ የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን እርምጃ ይታገሳል፡፡ የማያምን ሰው ግን የእግዚአብሄርን ጊዜ ስለማያምነው ይቸኩላል፡፡
በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11
የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።ምሳሌ 28፡20
7.     የማያምን ሰው ከሰው ጋር ይጣላል፡፡
የማያምን ሰው በረከቱን የያዘው ሰው ስለሚመስለው ከሰው ጋር ይጣላል፡፡ የማያምን ሰው ከሰው ስለሚጠብቅ በሰው ይሰናከላል፡፡ የመያምን ሰው መንፈሳዊውን አለም በእምነት ስለማያይ የጦር እቃው ስጋዊ ብቻ ነው፡፡ የሚያምን ሰው ግን ከእግዚአብሄር ስለሚጠብቅ በሰው አይሰናከልም፡፡ የሚያምን ሰው ከሰው ባሻገር መንፈሳዊውን አለም ስለሚያይ የጦር መሳሪያው ስጋዊ አይደለም፡፡  
በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡1-3
በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ 2 ቆሮንቶስ 10፡3-4
8.     የማያምን ሰው በጥበቡ በሃይሉና በብልጥግናው ይመካል
የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ይመካል፡፡ የማያምን ሰው ግን የእግዚአብሄር ሃብት የእኔ ሃብት ነው ስለማይል መሰብሰብ ማከማቸት ይፈልጋል፡፡ የሚያምን ሰው እግዚአብሄር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ የለም ስለሚል ማግበስበስ አያስፈልገውም፡፡ የማያምን ሰው ግን እረኛውን ስለማያምን እረኛ የሚያደርገው ጥበቡን ሃይሉንና ባለጠግነቱን ነው፡፡ የሚያምን ሰው የነገሮች ሁሉ ቁልፍ እግዚአብሄር ጋር እንጂ ጥበብ ፣ ሃይልና ባለጠግነት ጋር እንዳይደለ ያውቃል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርሚያስ 9፡23-24
9.     የማያምን ሰው ይጨነቃል
የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቅን ሲፈልግ እግዚአብሄር በምድር የሚያስፈልገው እንደሚያሟላለት ስለሚያምን አይጨነቅም፡፡ እግዚአብሄርን የማያምን ሰው ግን ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ በመጨነቅ እግዚአብሄር ይጨመርላችኋል ያለውን በመፈልግ ህይወቱን ያባክናል፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31፣33
10.    የማያምን ሰው ያጉረመርማል
የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር መልካምነት ስለሚተማመን ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ደስ ይለዋል፡፡ የማያምን ሰው ደስታው በሁኔታዎች ብቻ ስለሆነ ያጉረመርማል፡፡ የሚያምን ሰው እግዚአብሄርን መልካምነት ስለሚያይ በእግዚአብሄር ላይ ጥያቄ የለውም፡፡
ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10
11.     የማያምን ሰው ይመኛል
የሚያምን ሰው ምንም እንዳልጎደለው ራሱን ያማጥናል፡፡ የሚያምን ሰው ጉድለቱን በሚሸፍን ድካምን በሚሞላ የእግዚአብሄር ፀጋ ስለሚተማመን አይመኝም፡፡ የማያምን ሰው ግን ሁሌ እግዚአብሄር ያልሰጠውን ነገር ይመኛል፡፡ የሚያምን ሰው ራሱን በሁኔታዎች ሁሉ ራሱን ያማጥናል፡፡
ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጭንቀት #ፍርሃት #ፍቅር #ተንኮል #ጠማማነት #ኩራት #ቅን #እምነት #ተንኮል #ምኞት #ሰላም #ኢየሱስ #ጌታ #ሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በእምነቱ በሕይወት

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4
መፅሃፍ ቅዱስ በእምነት ስለሚኖር ሰውና በእምነት ስለማይኖር ሰው እያነፃፀረ ያስተምራል፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ወይ በእምነት ነው የሚኖሩት ወይም ደግሞ በእምነት አይደለም የሚኖሩት፡፡
በእምንት ስለመኖር ጥቅም ሲናገር በህይወት ያኖራል ይላል፡፡ በህይወት መኖር ማለት በሁሉ ነገር ህያው መሆን ማለት እንጂ በስጋ አለመሞት ማለት ብቻ አይደለም፡፡
ለምሳሌ ኢየሱስ ያለው ህይወት አለው ሲል የዘላለም ህይወትን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ህይወትን ስለማጣጣም ይናገራል፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ በእርሱ የማያምን ህይወትን አያይም ሲል በስጋ ይሞታል ማለት ሳይሆን የእግዚአብሄርን ህይወት አላማ ይስተዋል ማለት ነው፡፡ ህይወትን አያይም ማለት እግዚአብሄር በህይወት ውስጥ ያስቀመጠውን በረከት አያገኘውም ማለት ነው፡፡ ህይወትን አያይም ማለት የህይወትን እውነተኛ መልክና ጣእም አያገኘውም ማለት ነው፡፡
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በደስታ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖሩ ሰዎች ለመደሰት የሆነ ነገር አይጠብቁም፡፡ በእምነት የሚኖሩ ሰዎች እነርሱን ለማስደሰት ጌታ ብቻውን በቂ ነው፡፡ በእምነት የሚኖሩ ሰዎች ለመደሰት ሌላ ሌላ ነገር መጨመር የለባቸውም፡፡
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡4
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከጭንቀት በላይ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖር ሰው ለእርሱ የሚያስብለት እንዳለ ስለሚያምን ጭንቀት ከህይወቱ ይሞታል፡፡
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡7
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በሃይል ይኖራል ማለት ነው፡፡
ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ዕብራውያን 11፡11
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በሃይል ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖረ ሰው እግዚአብሄር እንዲሰራው የሰጠውን ስራ ለመስራት ምንም ሃይል አይጎድልበትም፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።2 ጴጥሮስ 1፡2-3
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ስኬት ይኖራል ማለት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ በእግዚአብሄ ቃል እምነት የሚኖር ሰው በስራው ሁሉ ፍሬያማ ይሆናል፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡2-3
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል ማለት ነው፡፡  
ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል” ዮሐንስ 10፡1
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከጠላት ጥቃት በላይ ይኖራል ማለት ነው፡፡
በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡8-9
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በክንውን ደስታ ይኖራል ማለት ነው፡፡
እኔም መልሼ፦። የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት መታሰቢያም የላችሁም አልኋቸው። ነህምያ 2፡20
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በነፃነት ይኖራል ማለት ነው፡፡
በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃነት አወጣን እንግዲህ ፀንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ! ገላትያ 5:1
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከሁኔታዎች በላይ ይኖራል ማለት ነው፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በእርካታ ይኖራል ማለት ነው፡፡
ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡11-12
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በድፍረት ይኖራል ማለት ነው፡፡
ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም። ዕብራውያን 10፡38-39
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በፍሬያማነት ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖር ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በየዋህነት በማድረግ ፍሬን ያፈራል፡፡
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዮሃንስ 15፡15
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከመቋጠር ይወጣል ፣ ረጋ ብሎ በስፋት ካለስጋት ይኖራል ማለት ነው፡፡
ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ። መዝሙር 18፡19
አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። መዝሙር 18፡36
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ አያፍርም አይዋረድም በእረፍት ይኖራል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም። ኢሳያስ 28፡16
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በአሸናፊነት ይኖራል ማለት ነው፡፡
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1 ዮሐንስ 5፡4
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ስፋት #እርካታ #ፍሬያማነት #ክንውን #አሸናፊነት #በጎነት #ቅን #እምነት #ፅድቅ #ደስታ #ሰላም #ኢየሱስ #ጌታ #ሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ