Popular Posts

Follow by Email

Monday, May 28, 2018

ከአፌ የሚወጣ ቃሌ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል

ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም። ኢሳያስ 55፡10-11
እግዚአብሄር በየጊዜው ይናገራል፡፡ እግዚአሄር የተናገረውን ደግሞ ያደርጋል፡፡ ሃይል የእግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥ መዝሙር 62፡11
እግዚአብሄር የሚናገረው ነገር ሁሉ በጊዜው ባይመስልም ይፈፀማል፡፡
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እናገራለሁ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል፥ ደግሞም አይዘገይም፤ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ሕዝቅኤል 12፡25
ሰዎች ሲፈሩ ይዋሻሉ፡፡ ወይም ሰዎች ሰውን በከንቱ ለማበረታታት ይዋሻሉ፡፡ እግዚአብሄር ግን የሚፈራው የለም፡፡ እግዚአብሄር ካለ ይሆናል፡፡ ሰዎች ለሰዎች ይዋሻሉ፡፡ እግዚአብሄር ግን አይዋሽም፡፡ ጌታ እውነተኛ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለመናገር ብቻ ብሎ የሚናገር አምላክ አይደለም፡፡ ወይም እግዚአብሄር በስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሮ አይፀፀትም፡፡   
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን? ዘኍልቍ 23፡19
እግዚአብሄር ተናገረ ማለት ሆነ ማለት ነው፡፡
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም። መዝሙር 33፡9
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #ታላቅ #ድንቅ #ልዩ #ግሩም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

No comments:

Post a Comment