ሰዎች ለራሳቸውም ለሌላውም መልካምን ይመኛሉ፡፡ ምኞት በህይወታችን እንዲሆንልን የምንፈልገው ነገር ነው፡፡ ምኞት በህይወታችን እንዳናጣው የምንፈልገው ነገር ነው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ስለምኞት ምን ይላል? በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ምኞቶችን መረዳት ስለምኞት መልካም ግንዛቤ እንዲኖረን ያስችላል፡፡ ሃዋሪያው በህይወቱ ስላለው ምኞት እንዲሆንለት ስለሚፈልገው በህይወቱ ሊያጣው ስለማይፈልግ ምኞት ይናገራል፡፡
እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡10-11
ደህንነት ነፃ ነው፡፡ ደህንነት ኢየሱስ በመስቅል ላይ የሰራልንን ስራ ለእኔ ነው ብለን መቀበል ብቻ ነው፡፡
ማንኛውንም የእግዚአብሄርን ነገር ለማግኘት የምናደርገው አንድ ነገር አለ፡፡ በተለይ ደግሞ ለማደግና በክርስቶስ ለመለወጥ የምንከፍላቸው ዋጋዎች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ለማግኘት የምንተወው ነገር አለ፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ ይህንን ምኞት ለማግኘት የሚተዋቸውን ነገሮች ይዘረዝራል፡፡ ሃዋሪያው እንዲሆኑለት ስለሚፈልገው ነገሮች ስለምኞቱ ሰዎች የሚያከብሩዋቸውን ነገሮች ሁሉ ይንቃል፡፡ በህይወቱ መድረስ ስለሚፈልገው ቦታ ስለምኞቱ ዋጋ ያላቸውን ክብር ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደጉድፍ ይቆጥራል፡፡ ምኞቱ ለማግኘት በሁሉም ይጎዳል፡፡
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ ፊልጵስዩስ 3፡8-9
ሃዋሪያው እነዚህን በሰዎች ዘንድ የከበሩትን ነገሮች ሁሉ እንደጉድፍ የሚቆጥረው እነዚህን ምኞቶቹን ለማግኘት ነው፡፡ ሃዋሪያው ይህንን ለማግኘት በሁሉ ይጎዳል፡፡ ሃዋሪያው ስለምኞቱ መሳካት ሰዎች የሚያከብሩዋቸውን ነገሮች ሁሉ ይንቃል፡፡
እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡10-11
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ክርስቶስ #ጌታ #እውቀት #የትንሳኤሃይል #እምነት #ምኞት #መከራ #ትንሳኤ #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ሞት #መመለስ #ሃይል #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment