Popular Posts

Saturday, August 5, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 8

 

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ። እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 23፡25-28

የፈሪሳዊነት ትምህርት እግዚአብሔር ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ የሚለውን ትእዛዝ በስራ እና በትምህርት መቃወም ነው፡፡

ልባችሁን እንጂ፣ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ፣ ቍጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ፣ ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገሥ ነውና። ትንቢተ ኢዩኤል 2:13

ፈሪሳዊነት እግዚአብሔር ፊትን አያይም ልብን ያያል የሚለውን የእግዚአብሔርን መርህ መቃወም ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16፡7

ፈሪሳዊነት ልብ ከእግዚአብሔር በጣም ርቆ በውጭ ስርአት ብቻ ማምለክ ነው፡፡

ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ። የማቴዎስ ወንጌል 15፡8-9

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ጻፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን


No comments:

Post a Comment