የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። ምሳሌ 4:18
በጌታ ኢየሱስ አምኖ ጌታን የሚከተል ሰው ሁሉ ተስፋው ብሩህ ነው፡፡ ጌታን የሚከተል ሰው ሁሉ እየተነሳ ያለ ኮከብ ነው፡፡ ጌታን ለመከተል የወሰነ ሰው ሁሉ መጨረሻው የሚያምር ነው፡፡
እርግጥ ነው ክርስትያን በብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ውስጥ ያልፋል፡፡ በነገሮች ወስጥ ሁሉ ግን ክርስትያን እያደገ ፣ እያሸነፈና እየለመለመ ይሄዳል፡፡
ክርስትያን የሚያልፍባቸውን አስቸጋሪ ነገሮችን ልዩ የሚያደርጋቸው እግዚአብሄር አብሮት ስላለ ነው፡፡ አስቸጋሪውን ነገር እግዚአብሄር አብሮት ይጋፈጠዋል፡፡ እግዚአብሄር እንዴት እንደሚያልፈው ጥበብን ይሰጠዋል፡፡
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡5
ጌታን የሚከተል ሰው በራሱ ሲደክም እግዚአብሄር ያስችለዋል፡፡ እግዚአብሄር በድካሙ እየገባ በፀጋው ሃይል ያስችለዋል፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9
በክርስቶስ የመስቀል ስራ የፀደቀ ሰው መንገዱ እንደንጋት ብርሀን ነው፡፡ የንጋት ብርሃን ከትንሽ ወገግታ ብርሃን አንስቶ እየደመቀ እየደመቀ እንደሚሄድ ሁሉ የክርስትያን መንገስ እንደዚያው ነው፡፡
የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20
የክርስትያን ሙሉ የህይወት ለውጥ ድንገተኛ አይደለም፡፡ የክርስትያን መንገድ የሚሄደው ቀስ በቀስ እየጨመረ ይበልጥ እየበራ ነው፡፡ የእግዚአብሄር አስተዳደግ በፍጥነት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር አስተዳደግ በሂደት ነው፡፡
በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11
ጌታን የሚከተል ሰው ፍፃሜው ያማረ ነው፡፡
የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። ምሳሌ 4:18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ጻድቃን #የታመነ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥቂትበጥቂት #ሙሉቀን #እየተጨመረ #በረከት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment