I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ኢየሱስ በስጋ ወደምድር ከመምጣቱ በፊት ብሉይ ኪዳን ' የጉብኝት ባህል ' እና በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተደረገው አዲስ ኪዳን ግሞ ' የ መ ኖር ባህል ' ተብሎ ...
-
Video Transcript: In the far east they have something that’s call the Chinese bamboo tree. The Chinese bamboo tree takes five years to ...
-
ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ኦሪት ዘጸአት 12:2 እውነተኛው አዲስ አመት የሚባለው ቃሉን ሰምተን ነጻ የምንወጣበትን ጊዜ ነው። እውነተኛው ዘመን መለወጫ የሚባለው ቃሉን ሰምተን በቃሉ ...
-
የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ነገር የመስራት እና የመለወጥ አቅም አለው። ያዕቆብ 5:16 … የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሀይል በፀሎታችን አይወሰንም። እግዚአብሔር ከምንለምነው ...
-
እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2 የጥንቱን ...
-
በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል። 1ኛዮሐንስ 3:19-20
-
የምንሞትለት እንጂ የምንገድልለት አምላክም ሆነ ሀይማኖት የለንም! አምላክ ሀያል ነው የእኛ እርዳታ አይፈልግም። እንዲገድሉለት የሰውን እርዳታ የሚፈልግ ሀይማኖት እውነተኛ ሀይማኖት አይደለም። የሰውን እርዳታ የሚፈልግ...
-
የእግዚአብሄር ስራ የሚሰራው በመንፈስ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት እውነተኛ አገልግሎት ለማገልገል መቀጣጠሉና ግለቱ ወሳኝ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ነገር ቢኖረው ነገር ግን ምንም መነሳሳትና መቀጣጠል ከ...
-
በምድር ላይ ህዝብን የሚያስተዳድርና የሚገዛ መንግስት እንዳለ ሁሉ በመካከላችን የእግዚአብሄር መንግስት አለ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በአይን የማይታይ በስፍራ የማይወሰን መንግስት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ንጉ...
-
Name it claim it Take it! “So Jesus answered and said to them, “Have faith in God. For assuredly, I say to you, whoever says to this mount...
Thursday, November 7, 2024
Wednesday, November 6, 2024
ያላችሁም ይብቃችሁ! አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ወደ ዕብራውያን 13:5 ሰዎች ጥፋት የሚያጠፉት አሁን ጥፋት ላጥፋ ብለው አቅደው አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ጥፋት የሚያጠፉት በሀሳባቸው ተታለው ነው። ሰዎች ሁሌ የተሻለ የበለጠ ነገር ይፈልጋሉ። ደግሞም ብዙ ጊዜ የሌላቸው ነገር ሁሉ የተሻለ የበለጠ ነገር ይመስላቸዋል። ታዲያ ሰዎች በተለይ የተሻለ ደስታን ፈልገው የተሳሳተ እርምጃ በመውሰዳቸው ምክንያት የማይወጡበት ሱስ ውስጥ ይገባሉ። ያለኝ ደስታ አይበቃኝም ብለው በትእቢት በማሰብ ደስታን በተሳሳተ ቦታ ሲፈልጉት የማይወጡት እስራት ውስጥ ወድቀው ራሳቸውን ያገኛሉ። ከነበራቸው ደስታ በላይ ያስፈልጋቸው እንዳልነበር እና የናቁት ደስታ ይበቃቸው እንደነበረ የሚረዱት ከረፈደ በኋላ ነው። እመኑኝ አሁን ከናቃችሁት የደስታ ደረጃ በላይ ያስፈልጋችሁ እንዳልነበረ የምትረዱት አሁን ያላችሁን ደስታ በንቀት ያጣችሁት ቀን ነው። አሁን እናንተ ያላችሁም ደስታ ይብቃችሁ። አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa #ፀሎት #ፈቃዱ #መልስ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
ያላችሁም ይብቃችሁ!
አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህምብሎአልና፤ ወደ ዕብራውያን 13:5
ሰዎች ጥፋት የሚያጠፉት አሁን ጥፋት ላጥፋ ብለው አቅደው አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ጥፋትየሚያጠፉት በሀሳባቸው ተታለው ነው።
ሰዎች ሁሌ የተሻለ የበለጠ ነገር ይፈልጋሉ። ደግሞም ብዙ ጊዜ የሌላቸው ነገር ሁሉ የተሻለ የበለጠ ነገርይመስላቸዋል።
ታዲያ ሰዎች በተለይ የተሻለ ደስታን ፈልገው የተሳሳተ እርምጃ በመውሰዳቸው ምክንያት የማይወጡበት ሱስውስጥ ይገባሉ። ያለኝ ደስታ አይበቃኝም ብለው በትእቢት በማሰብ ደስታን በተሳሳተ ቦታ ሲፈልጉት የማይወጡትእስራት ውስጥ ወድቀው ራሳቸውን ያገኛሉ።
ከነበራቸው ደስታ በላይ ያስፈልጋቸው እንዳልነበር እና የናቁት ደስታ ይበቃቸው እንደነበረ የሚረዱት ከረፈደ በኋላነው።
እመኑኝ አሁን ከናቃችሁት የደስታ ደረጃ በላይ ያስፈልጋችሁ እንዳልነበረ የምትረዱት አሁን ያላችሁን ደስታበንቀት ያጣችሁት ቀን ነው።
አሁን እናንተ ያላችሁም ደስታ ይብቃችሁ።
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ፀሎት #ፈቃዱ #መልስ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል#እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር#ፅናት #ትግስት #መሪ

