Popular Posts

Tuesday, May 15, 2018

ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ

እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ ማቴዎስ 12፡36
ዝም ብሎ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ሰው የንግግርን ሃይል በቅጡ ያልተረዳ ሰው ነው፡፡  
ንግግር ታላቅ ሃይል ያለው ነገር ነው፡፡ የንግግር ቃል ያፈርሳልም ይገነባልም፡፡
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ። ምሳሌ 18፡21
የንግግር ቃል ይባርካል ይረግማል፡፡
በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። ያዕቆብ 3፡9-10
ሰው በንግግር ሰውን ያንፃል ፣ ይገነባል ፣ ያሻግራልና ይፈውሳል፡፡ መልካም ቃል ይፈውሳል ጤንነትን ይሰጣል፡፡  
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ኤፌሶን 4፡29
ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል። ምሳሌ 15፡4
ሰው ደግሞ በንግግር ሰውን ያፈርሳል ያጠፋል የፍጥረትን ሩጫ ያቃጥላል፡፡  
እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፤ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል። እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፤ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው። ምሳሌ 12፡17-18
አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። ያእቆብ 3፡6
እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ ማቴዎስ 1236
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #አንደበት #ምላስ #አፍ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፀጋ #እሳት #መልካምቀኖች #ህይወት #በረከት #መርገም #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment