Popular Posts

Monday, May 7, 2018

ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል

የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና። ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል። 2 ቆሮንቶስ 410-12
ወደጌታ የመጣነው ጌታን የሚከተሉ ሰዎች በእሰቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ ስላገለገሉን ነው፡፡ በጌታ የበረታነው ለእግዚአብሄር መንግስት ዋጋ የሚከፍሉ ሰዎች በመከራ ውስጥ እያለፉ ጌታን ስላሳዩን ነው፡፡
እነርሱ በተለያየ መልኩ ሲሰደዱና በመከራ ሲያልፉ የክርስቶስ ሞት በእነርሱ ይሰራ ነበር፡፡ ክርስቶስ እንደሞተ ያገለገሉን አገልጋዮች በሞት ውስጥ ያልፉ ነበር፡፡
የኢየሱስ ህይወት በአገልግሎታቸው ይገለጥ ዘንድ በስጋቸው መከራን ይቀበሉ ነበር፡፡ የኢየሱስን ህይወት እንዲያካፍሉን በመከራ ውስጥ ያልፉ ነበር፡፡
ስለዚህ ሞቱ እኛን ባገለገሉን ላይ ይሰራ ነበር ህይወቱ በእኛ ይሰራ ነበር፡፡ እነርሱ ሞቱን ሲካፈሉ እኛ ህይወቱን ተካፈልን፡፡
አሁን ደግሞ እኛ የምናገለግላቸው ሰዎች የክርስቶስን ህይወትን ይካፈሉ ዘንድ የክርስቶስ ሞት በእኛ ይሰራል፡፡ እኛ ከክርስቶስ ሞት ጋር ስንካፈልና በመከራ ውስጥ ስናልፍ የሚሰሙን ሰዎች የክርስቶስን ህይወት ይካፈላሉ፡፡
እኛ በተለያየ መልኩ ስንሰደድና በመከራ ውስጥ ስናልፍ የሚሰሙን ሰዎች የክርስቶስን ህይወት ይካፈላሉ፡፡ እኛ ስንጨፈለቅ እነርሱ ጭማቂን ይጠጣሉ፡፡ እኛ አገልጋዮቹ ስንሰደድና በመከራ ውስጥ ስናልፍ የክርስቶስ ሞት በእኛ ይሰራል የክርስቶስ ህይወት ደግሞ በምናገለግላቸው ላይ ይሰራል፡፡ ክርስቶስ እንደሞተ በሞት ውስጥ እናልፋለን፡፡ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ የምናገለግላቸው አገልግሎታችን ህይወቱን ይካፈላሉ፡፡   
ስለዚህ አሁን ሞቱ በእኛ ይሰራል ህይወቱ እኛ በምናገለግላቸው ላይ ይሰራል፡፡
የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና። ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል። 2 ቆሮንቶስ 410-12
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #መከራ #ፈተና #ሞት #ህይወት #ስጋ #መፅናት #መታገስ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment