Popular Posts

Monday, May 28, 2018

የሚሰክረው ልጅ እናት ታሪክ

ኬኔት ሃገን የተባሉ የእግዚአብሄር ሰው በአንዱ ስብከታቸው ላይ ስለ አንድ ሴት ታሪክ ያናገራሉ፡፡
በየቤተክትርስትያን እየተጋበዝኩ በማገለግልበት ጊዜ ከስብከት በኋላ አንድ ሴት መጥታ ለልጄ ፀልይለት ብላ ጠየቀችኝ፡፡ ልጅዋ ስላለበት ሁኔታም ስረታስረዳኝ ህይወቱ በጣም የተበላሸ ነው ፣ በጣም ይሰክራል ፣ ከምሽቱ 8 ሰአት ነው ወደቤት የሚመጣው ብላ ነገረችኝ፡፡
እኔም ታሪክዋን ከሰማሁ በኋላ ለልጅዋ እንደማልፀልይለት ነገርኳት፡፡ ያንን ያልኩት ስላላዘንኩ ሳይሆን የእርስዋን ትኩረት ለማግኘት ስለፈለኩ ነበር ይላሉ የእግዚአብሄር ሰው ኬኔት ሃገን፡፡
እንዴት ስትለኝ አልፀልይለትም ነገር ግን አንቺ ሂጂና ለልጅሽ ፍቅርን አሳዪው ብዬ መክርኳት፡፡
ከቆየ በኋላ አንድ ቀን ያቺ ሴት ወደእኔ መጥታ ታሳውሰኛለህ ወይ ብላ ጠየቀቺኝ፡፡ አይ አላስታውስሽም እልኳት፡፡ በጣም ለሚሰክረው ልጄ እንዲለወጥ እንድትፀልይልኝን የጠየቅኩህ ሴት ነኝ ብላ አስታወሰቺኝ፡፡
ፍቅርን አሳዩው ባልከኝ መሰረት አትስከር ብዬ መጨቃጨቄን ትቼ የእናትነት ሃላፊነቴን ብቻ መወጣት ጀመርኩ፡፡ እናት ለልጅ የምታደርግለትን ነገር ሁሉ አደርግለት ጀመር፡፡ እንደ ቤተሰቡ ካህን እንዲህ አድርግ እንዲህ አታድርግ የሚለውን ጭቅጭቅ ትቼ በራሴ ሃላፊነት ላይ ማተኮር ጀምረኩ፡፡
አንድ ሌሊት እንዲሁ ሰክሮ መጥቶ በነጋታው እሁድ ነበርና ቤተክትርስትያን ውሰጂኝ አለ፡፡ እኔም አይ ትላንትና አምሽተህ ነው የገባኸው ደክሞሃል እረፍ ብለው ሊቀበልኝ አልቻለም፡፡ እኔ ጌታን መቀበል እፈልጋለሁ ብሎ ጌታን ተቀበለ በማለት የፍቅር ህይወት የተበላሸ ህይወት የነበረውን ልጅዋን እንዴት እንደለወጠ መሰከረችልኝ በማለት ይመሰክራሉ፡፡  
የሰው የፍቅር ህይወት ከምንም ንግግር በላይ ሃይል አለው፡፡ ፍቅርን ስናሳየው ሰው ይማረካል፡፡ ፍቅር የማይገባው ፍቅር የማይማርከው ሰው የለም፡፡
ምንም አያውቅም የምንለው ምንም አይረዳም የምንለው ሰው ፍቅርን ያውቀዋል፡፡ በክፉ የተያዘው አለም ፍቅርን ይለያል፡፡
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሃንስ 13፡35
ይህ ቃል ከዚህ የእግዚአብሄር ቃል ጋር ይስማማል፡፡
እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። 1 ጴጥሮስ 3፡1-2
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ምስክርነት #ኑሮ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #የህይወትምስክርነት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment