Popular Posts

Friday, May 4, 2018

የፀሎት መሰረት

በፀሎት ውስጥ እጅግ ታላቅ ሃይል አለ፡፡ ለእግዚአብሄር የኖሩና እግዚአብሄርን ያገለገሉ ሰዎች ሁሉ በፀሎታቸው ይታወቃሉ፡፡ የፀሎት ሰዎች የሃይል ሰዎች ናቸው፡፡ የፀሎት ሰዎች የእምነት ሰዎች ናቸው፡፡ የፀሎት ሰዎች ፍሬያማ ሰዎች ናቸው፡፡ ካለ ፀሎት የእግዚአብሄርን ፈቃድ በሚገባ መፈፀም የማይታሰብ ነገር ነው፡፡
ፀሎት ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ የምናደርግው ነገር ነው፡፡ ፀሎት የምናስበውን ሃሳብ ተናግረን የምንሄድበት ነገር አይደለም፡፡ ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን መስማት ለእግዚአብሄር መናገር ነው፡፡
የፀሎት ዋናው ክፍል እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ የፀሎት መሰረቱ እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ ፀሎት የሚጀመረው ለእግዚአብሄር ከመናገር አይደለም፡፡ ፀሎት የሚጀመረው እግዚአብሄርን ከመስማት ነው፡፡
ፀሎትይ ወደአእምሮዋችን የሚመጣውን ነገር ተናግሮ መነሳት አይደለም፡፡ ፀሎት የሚጀመረው በእግዚአብሄር ፊት ከመቆየት ነው፡፡ ጸሎት የሚጀመረው እግዚአብሄርን ከመጠበቅ ነው፡፡
ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። መዝሙር 40፡31
የፀሎት ዋናው ጉዳይ ለእግዚአብሄር ንግግር ቅድሚያ መስጠት ነው፡፡ የፀሎት ዋናው ክፍል ለማናገር ሳይሆን ለመስማት መቅረብ ነው፡፡  
ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፤ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን። መክብብ 5፡1-2
በፀሎታችን ፍሬያማ የምንሆነው በእግዚአብሄር ላይ በተደገፍን መጠን ብቻ ነው፡፡
በፀሎት ለመናገር የሚያስቸኩለን ነገር የለም፡፡ የሚያስፈልጋችሁን እርሱ ያውቃል ብሎናል፡፡
አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡7-8
ፀሎት በእረፍት መሆን አለበት፡፡ ፀሎት በፀጥታና በመታመን መሆን አለበት፡፡  
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡ ኢሳያስ 30፡15
የፀሎት ዋናው ክፍል በእግዚአብሄር ፊት ማረፍ ነው፡፡ የፀሎት ዋናው ክፍል እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ የፀሎት መሰረት እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡
ከእግዚአብሄር መንፈስ ውጭ በራሳችን እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅም፡፡ በፀሎታችን መንፈሱን መጠበቅና መስማት ያስፈልገናል፡፡
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ሮሜ 8፡26-27
በፀሎታችን የእግዚአብሄርን መንፈስ ሰምተን የምንፀልየው ፀሎት መሬት አይወድቅም፡፡ የፀሎት ዋናው እና በጣም አስፈላጊው ክፍል የእግዚአብሄርን መንፈስ መጠበቅና መስማት ነው፡፡ መንፈሱን ሰምተን የምንፀልየው ነገር ሁሉ አንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ስለሆነ ሁሉም ይመለሳል፡፡ መጠበቅ መታገስ የሚጠይቀው መንፈሱን መስማት እና መከተል እንጂ ለእግዚአብሄር መናገር አይደለም፡፡ አንድ ጊዜ የመንፈስን ሃሳብ ካወቅን የሚመለስ ፀሎትን መፀለይ ይቀላል፡፡  
መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10-12
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #ይማልዳል #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል   

2 comments: