ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። ምሳሌ 16፡18
ሰው ጥፋትን ቢያጠፋም ተስፋ አለው፡፡ ሰው ቢስትም የሚማር ልብ እስካለው ድረስ ይመለሳል፡፡ ሰው መንገድን ቢስት እስከሰማ ድረስ ይድናል፡፡
ትእቢተኛ ሰው ግን ሰውን የማይሰማ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ከእርሱ ውጭ አዋቂ እንደሌለ የሚያስብ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ካለእርሱ መንገድ ሌላው መንገድ ሁሉ የተሳሳተ የሚመስለው ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ራሱን ያለአግባብ የሰቀለ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ካለ እኔ ሰው የለም የሚል ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ማንንም የማይሰማ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ሁሉን የሚያውቅ የሚመስለው ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው የሚማር ልብ የሌለው ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ከሁሉም በላይ እውቀት ያለው የሚመስለው ሰው ነው፡፡
ደሃ እርዳታ ይገባዋል፡፡ ያዘነ መፅናናትን ይረዳል፡፡ ትእቢተኛ ግን የሚረዳው አንድን ነገር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን የሚገናኘው በሚረዳበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡ ትእቢተኛ የሚረዳው ተቃውሞን ብቻ ነው፡፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ይቃወማል፡፡
እግዚአብሄር የተቸገረን ይረዳል፡፡ እግዚአብሄር የወደቀን ያነሳል፡፡ እግዚአብሄር ያዘንን ያፅናናል፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ግን የሚያሻሽልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ግን ይቃወመዋል፡፡
ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። ያዕቆብ መልእክት 4፡6
ትእቢተኛ ከእግዚአብሄር ተቃውሞ ውጭ ለማንም እድልን አይሰጥም፡፡ ትእቢተኛን ማንም አይመክረውም፡፡ ትእቢተኛን ማንም አያስተምረውም፡፡ ትእቢተኛ ሁለኩንም ዝቅ አድርጎ ነው የሚያየው፡፡ ትእቢተኛ ሊሰማው የሚገባው ምንም ሰው የለም፡፡ ትእቢተኛን ማንም አይመልሰውም፡፡ ትእቢተኛ ከእግዚአብሄር ተቃውሞ ውጭ ተስፋ የለውም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ሌላ ምንም ማድረግ ስለማይችል ይቃወመዋል፡፡ ትእቢተኛ ማነንም ስለማይሰማ እግዚአብሄር በትእቢተኛ ፊት ይቆማል፡፡
እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
ትእቢተኛ ከሁሉ በላይ ራሱን አዋቂ ስለሚያደርግ ትእቢተኛ ከማንም ሊማር አይችልም፡፡ ትእቢተኛ የሚማረው በመስማት አይደለም፡፡ ትእቢተኛ የሚማረው በጥፋት ብቻ ነው፡፡ ሌላ የሚመለስበት ምንም መንገድ ስለሌለው ትእቢተኛ የሚመለሰው በውድቀት ብቻ ነው፡፡
ከትእቢት በኋላ ጥፋት ተከትላ እንደምትመጣ እርግጥ ነው፡፡ ኩሩ መንፈስን ካየህ ውድቀት ተከትላ እንድምትመጣ መጠበቅ ትችላለህ፡፡
ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። ምሳሌ 16፡18
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ጥፋት #ውድቀት #ኩሩ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment