እምነትና
በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡19
እምነት ታላቅ የክርስትና ሃይል ነው፡፡ ለሚያምን
ሁሉ ይቻለዋል፡፡ እምነት እጅግ ታላቅ ሃየለን ይሰጠናል፡፡ እምነት የማያስችለን ነገር የለም፡፡
ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23
ነገር
ግን ሃይል ካልመቆጣጠሪያው መንገድ አደገኛ እንደሆነ ሁሉ እምነት ካለመቆጣጠሪያ መሳሪያው ብቻውን አደገኛ ነው፡፡ እምነትና በጎ
ህሊና ይኑርህ የሚለው ለዚህም ነው፡፡
ምክኒያቱም
እምነት እንደ መርከብ ግዙፍና ብዙ ስራዎችን ሊሰራ የሚችል ነገር ነው፡፡ በጎ ህሊና ደግሞ ያንን ታላቅ መርከብ ሊቆጣጠር የሚችልና
ወደሚፈለግበት ቦታ ሊያደርስ የሚችል መሪው ነው፡፡
ታላቅ
መርከብ መሪ ባይኖረው እጅግ አደገኛ እንደሆነ ሁሉ እምነት ያለበጎ ህሊና አደገኛ ነው፡፡
በታላቅ
እምነቱ የታወቀው ሃዋሪያው ጳውሎስ በእምነቱ ብቻ ሳይሆን በህሊናውም ንፅህና ይታወቅ ነበር፡፡ ሃዋሪያው እምነቱን በእምነቱ መልካም
ገድልን መጋደል ብቻ ሳይሆን ህሊናውን ንጹህ ለማድረግ ይተጋ ነበር፡፡
ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡3
የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡5
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል
#መናገር #ህሊና #ተጋድሎ #ንፅህና #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment