Popular Posts

Sunday, May 20, 2018

በእንጀራ ብቻ አይኖርም


ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡3-4
ፈታኙ ሰይጣን ኢየሱስን የፈተነው ኢየሱስ በምድራዊ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር ሰው የሚኖርበትን የእግዚአብሄርን ቃል እንዲረሳ ነው፡፡
የሰይጣን አላማ አይናችንን ከመንፈሳዊው ነገር ላይ አንስተን በስጋዊው ነገር ላይ ብቻ እንድናተኩር ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በምድራዊ ነገር ሁሉ ባተሌ ሆነን መንፈሳዊ ነገርን በመርሳት ህይወታችንን ማባከን ነው፡፡ የሰይጣን አላማ አይናችንን ቁሳቁስ ላይ በማድረግ ከተጠራንበት ከፍ ካለው መንፈሳዊ አላማ ማስተጓጎል ነው፡፡
የሰይጣን አላማው ለስጋችን የሚያስፈልገው ነገር ላይ ብቻ አተኩረን መንፈሳዊውን ምግብ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳናስታውስ በዚያም ፍሬ ቢስ እንድንሆን ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ለስጋችን የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እያደረግን ለመንፈሳችን የሚሆነውን ነገር እንዳናደርግ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በስጋ እየኖረን በመንፈስ እንድንሞት ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በስጋ ሰብተን በመንፈስ አንድንጫጭ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በስጋ እየኖርን መንፈሳችንን በህይወት የሚያኖረውን በእግዚአብሄር ቃል እንዳንኖር ነው፡፡
ሰይጣን የሚፈልገው በስጋ ነገር ባተሌ ሆነን በመንፈስ ነገር እንድንከስር ነው፡፡ ሰይጣን የሚፈትነው ስለሚበላና ስለሚጠጣ እየተጨነቅን የእግዚአብሄርን መንግስት ፅድቁንም እንዳንፈልግ ነው፡፡  
እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 4፡31-33
ሰይጣን የሚፈልገው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት የእግዚአብሄር ቃል የሚገባውን ስፍራ በህይወታችን እንዳይኖረውና ሙሉ ፍሬ አንዳያፈራ ማድረግ ነው፡፡
በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። ሉቃስ 8፡14
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ስኬት #ክንውን #ቃል #መንፈስ #ስጋ #እንጀራ #የእግዚአብሔርቃል ##ማሰላሰል #አእምሮ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment