Popular Posts

Tuesday, May 8, 2018

ብትበደሉ አይሻልምን?

እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡7-8
እግዚአብሄር በትክክል ይፈርዳል፡፡ እንደ እግዚአብሄር በፅድቅ የሚፈርድ ማንም የለም፡፡
እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡2
ከእግዚአብሄር በላይ የምናውቅ አይምሰለን፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ፃዲቅ እንደሆንን አይሰማን፡፡ ከእግዚአብሄር የተሻለ እንደምንፈርድ አይምሰለምን፡፡
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3
እግዚአብሄር ስራን ይመዝናል፡፡ እግዚአብሄር የተበደለን እንዴት እንደሚክስ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር በዚህ የተበደለን በዚያ እንዴት እንደሚክስ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ፃዲቅ ፈራጅ ነው፡፡
እኛ ብንበደል ችግር የለውም፡፡ የእኛ ነገር በእግዚአብሄር እጅ ውስጥ ነው፡፡ እርሱ እንዴት እንደሚፈታው ያውቃል፡፡ እርሱ የተበደለን እንዴት እንደሚክስ ያውቃል፡፡ እርሱ የወደቀን እንዴት እንደሚያነሳ ያውቃል፡፡ እርሱ የተዋረደን እንዴት እንደሚያከብር ያውቃል፡፡
ሰው በደለም አልበደለም የሚያመጣው ነገር የለም፡፡ ጉዳዬ የምንለው እግዚአብሄር ነው፡፡ ቁልፉ ያለው በእግዚአብሄር እጅ ነው፡፡ ሰው በደለንም አልበደለንም በአጠቃላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡  
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርሚያስ 9፡24
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ የተዋረደ ወንድም በውርደቱ ይመካ የሚለው፡፡
የተዋረደ ወንድም ግን በከፋታው ባላጠጋም በውርደቱ ይመካ እንደ ሥር ያልፋልና። ያዕቆብ 1÷9-10
ማድረግ የሌለብን አንድ ነገር ሌላውን አለመበደል ነው፡፡ የሚበድል ሰው ግን እግዚአብሄር አብሮት አይሆንም፡፡ የሚበድል ሰው እግዚአብሄር ቢቀጣው እንጂ አይደግፈውም፡፡ የሚበድል ሰው ከእግዚአብሄር ተስፋ አያደርግም፡፡ የሚበድል ሰው በእግዚአብሄር ፊት ድፍረቱ የለውም፡፡ የሚበድል ሰው ቶሎ ካልተመለሰ ከእግዚአብሄር እየራቀ ይሄዳል፡፡ የሚበድል ሰው እግዚአብሄር እንዲክሰው አይጠብቅም፡፡  
የተበደለ ሰው እግዚአብሄር አብሮት ይቆማል፡፡ የተበደለ ሰው እግዚአብሄር ይክሰዋል፡፡
እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡7-8
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ  #ጌታ #እግዚአብሔር #ብትበደሉ #ካሳ #ይቅርታ #ምህረት #ፍርድ #ጠላት #ዲያቢሎስ #ስፍራ #ኢየሱስ #ጥላቻ #ትእቢት #መራርነት #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment