Popular Posts

Wednesday, May 9, 2018

ዕረፉ

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙር 46፡10
እንደ እረፍት ጣፋጭ ነገር የለም፡፡ ሰው ሲያርፍ ብቻ ነው ፍሬያማ የሚሆነው፡፡ ሰው ሲያርፍ ብቻ ነው በሙሉ ሃይሉ መልካምን ነገር ማድረግ የሚችለው፡፡ ፡፡ መስራትና ነገሮችን መለወጥ የሚችለው፡፡ ሰው ሲያርፍ ብቻ ነው  የሚሳካለት፡፡
ሰው ካላረፈ ጉልበቱን ያባክናል፡፡ ሰው ካላረፈ
ሰው የሚርፈው ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው የእግዚአብሄርን ሃይል ሲረዳ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው የእግዚአብሄርን ሁሉን ቻይነት ሲያውቅ ነው፡፡
ሰው የሚያርፈው የእግዚአብሄርን የፍቅር አላማ ሲረዳ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄር በሰው ላይ ያለው አላማ ፍቅር መሆኑን ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄር ለእያንዳንዱ ሰው የሚያስበው ልዩ ሃሳብ እንዳለው ሲያውቅ ነው፡፡
ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄር አብሮት እንዳለ ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄር እየመራው እንደሆነ ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው የእግዚአብሄር እርዳታ አብሮት እንዳለ ሲያውቅ ነው፡፡
ሰው የሚያርፍው እግዚአብሄር በበጥበብ በሃይልና በፍቅር ምድርን እንደሚያስተዳደር ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው የምድር ቁልፉ አግዚአብሄር ጋር እንዳለ ሲረዳ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው የነገሮች ቁልፍ ማንም ሰው ጋር እንደሌለ ሲረዳ ነው፡፡
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ኤርሚያስ 9፡24
ሰው የሚያርፈው ክብር ከእግዚአብሄር እንጂ ከሌላ ቦታ እንደማይመጣ ሲረዳ ነው፡፡
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤መዝሙር 75፡6
ሰው የሚያርፈው ከፍ ካለው ማንኛውም ነገር በላይ እጅግ ከፍ ያለው እግዚአብሄር እንደሚመለከት ሲረዳ ነው፡፡
አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ። ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አታድንቅ። መክብብ 5፡7-8
ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙር 4610

#ክርስቶስ #ጌታ #እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #እውቀት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment