Popular Posts

Monday, June 29, 2020

የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። መዝሙረ ዳዊት 2:2


ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፤ መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 3፡18


እግዚአብሔር ትልቅ ዘማሪት ህሊና ካሳሁን



እግዚአብሔር
ትልቅ (Egziabhier
Teleq) - ህሊና ካሳሁን

ችግር
ምንድን ነው ከሙላትህ ፊት ሲቆም
ጭንቀት
ምንድን ነው ከሰላምህ ፊት ሲቆም
ድካም
ምንድን ነው ከጉልበትህ ፊት ሲቆም
ማጣት
ምንድን ነው ከዙፋንህ ፊት ሲቆም

ይሟሟሉ
ይቀልጣሉ መገኘትህን ሲረዱ
የከበዱት
ዙፋን ስጡኝ ያሉ
ለቀው
ሄዱ እያፈሩ (x)

እግዚአብሔር
ትልቅ (x)

ከተራራው
በላይ ትልቅ
ከከበደው
በላይ ትልቅ
ከነገሩኝ
በላይ ትልቅ
ከችግሩ
በላይ ትልቅ

መንፈስ
ቅዱስ ትልቅ (x)

ከጨነቀኝ
በላይ ትልቅ
ከነገሩኝ
በላይ ትልቅ
ከሰበክነው
በላይ ትልቅ
ካመለኩት
በላይ ትልቅ

የሰልፉ
አለቃ ብቻህን ምትገዛ
ምድርን
ፍጥረትን በቃልህ ያጸናህ (x)
ዕድሜ
ማይወጣልህ ኃይልህ አይለካ
ምሽግ
መጠለያ ክንድህ የበረታ (x)

ገብተህ
በእኔ ጓዳ (x)
ኧረ
ለምን ልፍራ

መንፈስ
ቅዱስ ትልቅ ()

ከጨነቀኝ
በላይ ትልቅ
ከነገሩኝ
በላይ ትልቅ
ከሰበክነው
በላይ ትልቅ
ካመለኩት
በላይ ትልቅ

Sunday, June 28, 2020

ብዙ ጊዜ እንደምናስበው እጅግ በጣም አስፈላጊ አይደለንም በአእምሮዋችን ከምናስበው በላይ ግን ተወደናል



የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ አስፈላጊነታችን አጠያያቂ አይደለም፡፡
ነገር ግን ብዙ ጊዜ አስፈላጊነታችንን ከመጠን በላይ እናጋንነዋለን፡፡ ብዙ ነገሮች ካለእኛ መሰራት እንደማይችሉ በከንቱ እናስባለን፡፡
በህይወታችን ሁሉንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው በጣም ውስን ነገር ነው፡፡ ማድረግ የምንችለውን ውስኑን ነገር በትክክል ከሰራነው ስኬታማ ነን፡፡
እኔ ካለ እግዚአብሄር ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ እግዚአብሄር ግን ካለእኔ ሁሉን ሊያደርግ ይችላል ብሎ ትሁት መሆን ይጠቅማል፡፡ በእኛ መጠቀም ሲፈልግ ይጠቀማል እንጂ እኛን ላይጠቀም ሌላውን ሊጠቀም ይችላል፡፡   
አንገስ ቡከን የሚባል የእግዚአብሄር ሰው ሲናገር ራሳችንን በጣም ከማጋነናችን የተነሳ ስንሞት መልከአ ምድር ሁሉ የሚለወጥ ይመስለናል፡፡ እኛ ስለሞትን የሚለወጥ መንም መልከአ ምድር አይኖርም፡፡ ለብዙ ሺዎች አመታት ምድር ቀጥላለች እኛም ስንሞት ምድር እንዳለች ትቀጥላለች፡፡
ውስን እንደሆነን በመረዳት ራሳችንን ትሁት ማድረግ እና እጅግ አስፈላጊ በሆነው በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ በምድር ላይ ባለን ቆይታ ውጤታማ እንድንሆን ያስችለናል፡፡
ግንድ ሳንሆን ቅርንጫፍ እንደሆንን ስንረዳ ከእግዚአብሀጌር ጋር በሰላም እንኖራለን፡፡
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡5
አካል ሳንሆን የአካል ብልቶች እንደሆንን ስንረዳ ውጤታማነታእችን ይበዛል፡፡
አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡12
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24
ውስን እንደሆንን በትክክል ስንረዳ ማሰብ ከሚገባን አልፈን በትእቢት እንዳናስብ ይጠብቀናል፡፡
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡3
ውስን እንደሆንን ስንረዳ ሌላውን በትህትና ከእኛ እንደሚሻል አድርገን መቁጠር እና ማድነቅ እንጀምራለን፡፡  
ውስን እንደሆንን ስንረዳ በሁለንተናችን እኛ እግዚአብሄር ለእኛ እንደሚያስፈልገን በትህትና ማየት እንጀምራለን፡፡
እንደምናስበው ከሚገባው በላይ በጣም አስፈላጊ አለመሆናችን ብቻ ሳይሆን ከምናስበው በላይ ተወደናል፡፡
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፍቅር ተረድተን አንጨርሰውም፡፡
ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡8
በእኛ ላይ ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡
በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡4
ጠላቶች ሳለን ወደደን፡፡
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡8
ሃጢያተኞች ሳለን አንድ ልጁን እስኪሰጠን ድረስ ወዶናል፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። የዮሐንስ ወንጌል 3፡16
እራሱ ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር ተወደናል፡፡
ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡18-19
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #ትህትና #መዋረድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ከቅዱሳንሁሉጋር #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

"ውስጤ ስሰማው ሳደምጠው ሁሉ ሰላም ሰላም ነው ውጭውን አይቶ ልቤ እንዳይሰጋ እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ" ከተከስተ ጌትነት


ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6


አቤቱ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ ትንቢተ ኢሳይያስ 26:12


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 1፡7











Saturday, June 27, 2020

ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። የሐዋርያት ሥራ 20:24


የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ የያዕቆብ መልእክት 5:14


የስምዖንም አማት በብርቱ ንዳድ ታማ ነበር ስለ እርስዋም ለመኑት። በአጠገብዋም ቆሞ ንዳዱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ያንጊዜውንም ተነሥታ አገለገለቻቸው። የሉቃስ ወንጌል 4:38-39


Don't Quit by John Greenleaf

Don't Quit
by John Greenleaf Whittier
When things go wrong as they sometimes will,
When the road you're trudging seems all up hill,
When the funds are low and the debts are high
And you want to smile, but you have to sigh,
When care is pressing you down a bit,
Rest if you must, but don't you quit.
Life is strange with its twists and turns
As every one of us sometimes learns
And many a failure comes about
When he might have won had he stuck it out;
Don't give up though the pace seems slow—
You may succeed with another blow.
Success is failure turned inside out—
The silver tint of the clouds of doubt,
And you never can tell just how close you are,
It may be near when it seems so far;
So stick to the fight when you're hardest hit—
It's when things seem worst that you must not quit.
This poem is in the public domain

Friday, June 26, 2020

የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። ትንቢተ ኢሳይያስ 58:8


በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:25


አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ። ኦሪት ዘጸአት 23፡25-26


ለምን ? ለምን ?




ሰው የተፈጠረው ሁሉንም እንዲያውቅ ሳይሆን በማያውቀው ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር እንዲታመን ነው፡፡
ሰው ግን ብዙ ጊዜ በሚያውቀው ላይ ከመትጋት እና በማያውቀው ነገር ሁሉ ላይ ሁሉን በሚያውቀው በእግዚአብሄር ከመታመን ይልቅ የሚያውቅውን ትቶ የማያውቀውን ለማወቅ ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው፥ እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፤ እነርሱ ግን ብዙ ብልሃትን ፈለጉ። መጽሐፈ መክብብ 7፡29
አዳምና ሔዋን በሚያውቁት ሁሉ ከመኖርና በማያውቁት ሁሉ በየዋህነት በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ይልቅ የማያውቁትን ለማወቅ ለምን የሚል የማይመለስ አጓጉል ጥያቄ መጠየቅ በመጀመራቸው ከህይወት መንገድ ወደቁ፡፡
ሰው የተፈጠረው በቀላሉ የሚያውቀውን እየተገበረ የማያውቀውን ሁሉን በሚያውቀው በእግዚአብሄር ላይ እየተደገፈ እንዲኖር ነው፡፡
ኢዮብ ህይወቱ ላይ በደረሰው ነገር ለምን የሚል ጥያቄ ይዞ ተነሳ፡፡ እግዚአብሄ ግን ያሆነው ነገር ለምን እንደሆነ ከመመለስ ይልቅ የእዮብን መረዳት ነው የፈተነው፡፡
እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦ ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው? እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር። መጽሐፈ ኢዮብ 38፡1-4
ብዙ ጊዜ ለምን የሚል ጥያቄ እግዚአብሄርን የምንጠይቀው ቢመልስልንና ምክኒያቱን ቢነግረን የምንረዳ ስለሚመስለን ነው፡፡
እግዚአብሄር ለምን የሚለውን ጥያቄ የማይመልስልን ፍጥረቱ ስለሆንን ሁሎዩንም እንደማንረዳ አበጥሮ ስለሚያቀን ነው፡፡ እግዚአብሄር ለምን የሚለውን ጥያቄ የማይመልስልን የእግዚአብሄርን አሰራር ሁሉ መረዳት ከቻልን እኛ ራሳችን እግዚአብሄ ሆንን ማለት ነው፡፡
የሚያስፈልጉን የተገለጡ ነገሮች አሉ፡፡ እግዚአብሄር የማይነግረን ነገሮች ደግሞ አሉ፡፡
ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ኦሪት ዘዳግም 29፡29
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #መታመን #መደገፍ #እምነት #ለምን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። የማቴዎስ ወንጌል 8፡16-17 ወደ ዕብራውያን 13፡8


Tuesday, June 23, 2020

በምድራዊ እውቀት የማይደረስበት መንፈሳዊ ክልል



ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። የሉቃስ ወንጌል 13፡16

በህይወታችን ላይ የሚነጣጠሩ ብዙ ጥቃቶች ከምናስበው በላይ መንፈሳዊ ናቸው፡፡

ለምሳሌ የጤና መታወክ ሲደርስብን ቶሎ የሚመጣልን የሳይንሱ እውቀትና የሳይንሱ መፍትሄ ነው፡፡ ብዙ ነገር ሲደርስብን ቁሳዊ እናደርገዋለን፡፡ ብዙ ነገር ሲደርስብን በህክምና እውቀት ብቻ ልንተረጉመው እንፈተናለን፡፡

የበላሁት ምግብ ነው ወይም ቫይረስ ነው ብለን እንደሰው ልማድ ብቻ ጥቃቱን ልንዋጋው እንፈልጋለን፡፡ እንደሰው ልማድ ተዋግተን ከተሳካልን እሰየው፡፡ የሰይጣን ስራ ለማፍረስ ያለንን ነገር ሁሉ እምነታችን እና እውቀታችንን ሁሉ እንጠቀማለን፡፡

እንደሰው ልማድ ብቻ ከመዋጋት ያለፈ ነገር የሚጠይቅ ብዙ የዲያቢሎስ ጥቃት አለ፡፡  

የሰው ልጆች ጥቃት በቀጥታ ባይሆንም ቢያንስ በተዘዋዋሪ ከሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን ሌላ ራእይ የለውም፡፡ ራእዩ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቻ ነው፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

አንዳንዴ ሰይጣን በመንፈሱ በቀጥታ ባያጠቃንም ማድረግ ያለብንን ነገር በቸልተኝነት እንዳናደርግ በአእምሮዋችንም ቢሆን ያጠቃናል፡፡ ወይም የእግዚአብሄርን አላማ በምድር ላይ እንዳንፈፅም በፍርሃት ሽባ ያደርገናል፡፡ ሌላም ጊዜ በፀጋ ከተቀበልነው በሽታን በእኛ ላይ ሊያደርግ ይሞክራል፡፡

ተዘዋዋሪ የሰይጣን አላማ ቢሆኑም ንፅህናን ባለመጠበቅ የሚመጡ በሽታዎች ከሰይጣን አላማ ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ጥንቃቄያችንንም ተጠቅሞ ከጠላት ጥቃት ያስመልጠናል፡፡

ተጠንቅቀንም እግዚአብሄር አስመለጠን ነው የምንለው እንጂ ጥንቃቄያችንም ፍፁም በማይሆነው በጥንቃቄያችንም አንታመንም፡፡

እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለደህንታችን ያለውንም ነገር ሁሉ ይጠቀማል፡፡ እግዚአብሄር የዶክተሮችን ጥበብ ተጠቅሞ በሽታን ይዋጋልናል፡፡ የዲያቢሎስን ስራ ለማፍረስ ያለንን ምድራዊ እውቀት እና መንፈሳዊ እውቀርት ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ሰይጣን በህይወታቸን በጤናችን ምንም ስፍራ እንዳያገኝ እስከመጨረሻው ፀንተን እንቃወመዋለን፡፡

በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡9

ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡8

ከዶክተሮች እውቀት በላይ ያለ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ዶክተሮች በምድራዊ ጥበባቸው የማይደርሱበት መንፈሳዊ ክልል አለ፡፡

ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።  1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡14

እግዚአብሄር እምነታችንን ተጠቅሞ ከበሽታው ጀርባ ያለውን መንፈሱን በኢየሱስ ስም እንድንቃወመው አይናችንን ይከፍታል ይመራናል፡፡

ይህችን ሴት በወቅቱ ዶክተሮች ጋር ብትታይ ዶክተሮች በምድራዊ እውቀታቸው የማይረዱት መንፈሳዊ ክልል ስላለ ስለበሽታዋ አንድ ምክኒያት ይሰጧታል፡፡  

ኢየሱስ ግን ከዚህ በሽታ ጀርባ ያለውን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ የሚመጣውን ሰይጣንን አየው፡፡ ኢየሱስ በሽታውን ሳይሆን ከበሽታው በስተጀርባ ያለውን የበሽታውን ምንጭ አደረቀው፡፡

ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። የሉቃስ ወንጌል 13፡16

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


Monday, June 22, 2020

በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል የሉቃስ ወንጌል 18:27


ዓለቴ ነው ጌታዬ ጽኑ ነው መሠረቴ እኔ ክፉን አልፈራም ኢየሱስ አለ በሕይወቴ


ዓለቴ ነው ጌታዬ ጽኑ ነው መሠረቴ
እኔ ክፉን አልፈራም ኢየሱስ አለ በሕይወቴ

Lauren Daigle - You Say (Official Music Video)

Lauren Daigle - You Say (Official Music Video)

Lauren Daigle - You Say

I keep fighting voices in my mind that say I'm not enough
Every single lie that tells me I will never measure up
Am I more than just the sum of every high and every low?
Remind me once again just who I am, because I need to know, ooh oh
You say I am loved when I can't feel a thing
You say I am strong when I think I am weak
And You say I am held when I am falling short
And when I don't belong, oh, You say I am Yours
And I believe (I), oh, I believe (I)
What You say of me (I)
I believe
The only thing that matters now is everything You think of me
In You I find my worth, in You I find my identity, ooh oh
You say I am loved when I can't feel a thing
You say I am strong when I think I am weak
And You say I am held when I am falling short
When I don't belong, oh, You say I am Yours
And I believe (I), oh, I believe (I)
What You say of me (I)
Oh, I believe
Taking all I have and now I'm layin' it at Your feet
You'll have every failure God, You'll have every victory, ooh oh
You say I am loved when I can't feel a thing
You say I am strong when I think I am weak
You say I am held when I am falling short
When I don't belong, oh, You say I am Yours
And I believe (I), oh, I believe (I)
What You say of me (I)
I believe
Oh, I believe (I), yes, I believe (I)
What You say of me (I)
I believe (oh)

Sunday, June 21, 2020

ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 3፡12-13 ፣ 8፡5

ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። መጽሐፈ መክብብ 3፡12-13 ፣ 8፡5

Tuesday, June 16, 2020

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። መዝሙረ ዳዊት 136:1


እውነተኛ የህይወት ለውጥ የሚጀምረው



እውነተኛ የህይወት ለውጥ የሚጀምረው  
የህይወት ለውጥ ቀላል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ሰው በፈለገ ጊዜ ህይወቱን ይለወጥ ነበር፡፡ የህይወት ለውጥ ውሳኔን የሚጠይቅ ታስቦበት በእቅድ የሚራመዱት የጉዞ ውጤት ነው፡፡  
ብዙ ሰዎች መለወጥ ይፈልጋሉ ነገር ግን መለወጥ የሚያስችላቸውን ነገር አያደርጉም፡፡ ብዙን ጊዜ ሰዎች ለውጥን የሚፈልጉት ከተሳሳተ ቦታ ነው፡፡
ሰዎች እንዳይለወጡ ምክኒያት የሆኑዋቸውን ከእነርሱ ውጭ ነገሮች ሁሉ ላይ ያተኩራሉ፡፡ ነገር ግን በህይወታቸው እንዳይለወጡ ላደረጋቸው ሃሳብ ፣ ምርጫና ልምምድ ሃላፊነት መውሰድ በፍፁም አይፈልጉም፡፡
ሰው ስለደረሰበት ደረጃ ራሱ በትህትና ሃላፊነት ካልወሰደ ስለህይወቱ ሃላፊነት ወስዶ ሊለውጠው የሚችለው ሰው ስለሌለ አይለወጥም፡፡ ሰው ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጡር በመሆኑ ከተለወጠ የሚለወጠው በራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው ስለለውጡ አስተዋፆ ሊያደርግ ይችላል እንጂ ማንም ሰው ማንንም ሰው ሊለውጥ ግን አይችልም፡፡
የህይወት ለውጥ ከሌላ ሰው እና ከአካባቢ ሁኔታ ይመጣል ብሎ መጠበቅ ተመሳሳይ ነገርን እያደረጉ የተለየ ለውጥን እንደመጠበቅ እብደት ነው፡፡
ሰው ያለበትን ደረጃ ሲቀበል ፣ ወደአለበት ደረጃ ስላደረሰው ስለምርጫውና ስለአስተሳሰቡ ሃላፊነት መውሰድ ሲጀምር ለውጥ መምጣት ይጀምራል፡፡
ለውጥን ከፈለገን እንደዚህ የሆንኩት እከሌ እንደዚህ ስላደረገኝ ነው በማለት ተጠያቂነትን ማስተላፍ ማቆም አለብን፡፡ ሰው ስለውድቀታችን አስተዋእኞ አድርጎ ይሆናል እንጂ ውድቀታችን የመጣው ከህይወታችን ባለቤት ከራሳችን ነው፡፡ አዳም ስለውድቀቱ ሃላፊነት  አለመውሰዱና ጥፋቱን በሌላ ሰው ላይ ማለከኩ ከቅጣት አላዳነውምን፡፡
አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ። ኦሪት ዘፍጥረት 3፡12
ሌላ ሰው ወይም ሁኔታ ስለውድቀታችን አስተዋፆ እንዲያደርግ የምንፈቅድለት እኛ ብቻ ነን፡፡
ስላለሁበት ደረጃ መወቀስም መመስገንም ያለብኝ እኔ ነኝ ብሎ ሃላፊነትም መውሰድ ብስለት ነው፡፡ ሰው ሃላፊነት ሲወስድ ከገባበት ነገር የሚወጣበትን መንገድ በሃላፊነት ስለሚያቅድና ስለሚፈፅም ህይወቱ ይለወጣል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #እውቀት #ቃል #ወር #መዳን #ውሳኔ #መልካም #መታዘዝ #የህይወትለውጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ሃላፊነት #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #መናገር #አእምሮ #ነፍስ #ቃል #ልጅ

Monday, June 15, 2020

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል የማርቆስ ወንጌል 9:23


እግዚአብሔር የሚቀጣው እንዲበድል ያደረገውን ስጋዊ ፍላጎት ነው


ብዙ ሰዎች በደልን እንዴት እንደሚይዙ ስላማያውቁ በህይወታቸው ዘመን ይሰቃያሉ፡፡ ገንዘባችንን እንዴት እንድምንይዝ ፣ ጤናችንን እንዴት እንድምንጠበቅ ፣ ስራችንን እንዴት እንደምንሰራ የመሳሰሉትን ከምናውቀው እውቀት በላይ ከሰው ጋር እንዴት እንድምንኖር ማወቅ ከብዙ ኪሳራ ከብዙ የስሜት በሽታ ብሎም ከብዙ ችግሮች ይጠብቀናል፡፡

ሰውን እንድናምን ከሰው ጋር እንድንኖር ተፈጥረናል፡፡ ሰው ጠቃሚ እንደመሆኑም መጠን ግን በተለያየ ጊዜም ይበድለናል፡፡

ሰው አውቆም ይሁን ሳያውቅ ሰውን ስለሚበድል ሰው ሰውን የመበደሉ እውነት የማይቀር ነገር ነው፡፡ ዋናው ነገር ሰው ሰው ሰውን ይበድላለ ወይ የሚለው ጥያቄ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር የተበደለው ሰው በደሉን እንዴት ይይዘዋል የሚለው ጥያቁ ነው፡፡ ሰው ለበደል እንዴት እንደሚመልስ ካወቀ ያርፋል፡፡

ሰው በደሉን በትክክል ከያዘው ይማርበታል ያድግበታል የተሻለ ሰው ሆኖ ይለወጥበታል፡፡ ሰው በደሉን በትክክል ካልያዘው ይሰቃይበታል ህይወቱን ያባክንበታል፡፡

ሰው ሲበድለን በመጀመሪያ ደረጃ ነፃ የሚያወጣን ነገር ስለበደሉ የተቻለንን ያህል ሃላፊነት መውሰዳችን ነው፡፡ እርሱ 100 % ጥፋተኛ ነው እኔ 0% ጥፋተኛ ነኝ የሚለው ነገር አያዋጣም፡፡ ቢያንስ ሲያጠፋ እኛ ጥፋቱን የመለስንበት መንገገድ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡

ሁለተኛ እግዚአብሄር የሚቀጣው የበደለውን ሰውዬ ሳይሆን እንዲበድል ያደረገውን ስጋዊ ፍላጎት ነው፡፡

ሶስተኛ ማወቅ ያለብን እርሱን እንዲበድል ያደረገው ያው ስጋዊ ፍላጎት እኛም ውስጥ እንደሚኖር አውቀን ትምህርትና ግሳፄ መውሰድ ነው፡፡ እኔ እንደዚህ መበደል አልችልም ማለት ሞኝነት ነው፡፡ በበዳዩ ውስጥ ያየነውን የስጋ አስከፊነት ካየን እኛ ውስጥ ያለው ስጋ በሌሎች ላይ ተመሳሳይ በደል እንዳያደርግ እንጨክንበታለን፡፡

አራተኛ የበደለን ሰው እስኪወድቅ አለመጠበቅ ነው፡፡ ሰው ስራውን ትቶ የበደለኝ ሰው ከመቼ መቼ ይቀጣል እያለ ስለበደለው ሰው የሚከታተል ከሆነ የራሱን የህይወት አላማ ትቶ ስቶዋል ማለት ነው፡፡ ከበደለው ሰው ጋር በመፎካከር የህይወት አላማውን አሽቀንጥሮ የሚጥል ሰው የህይወት አላማው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የማያውቅ ሰው ነው፡፡

የበደለ ሰው ስጋ በአስቸጋሪ ነገር ውስጥ በማለፍ የስጋ ፍላጎቱ ሊገደል ይችላል፡፡ በደል ያስደረገው ያ ስጋዊ ፍላጎት ዛሬ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በምን መጠን በምን ሁኔታ ይቀጣ አታውቅምና ትተኸው ህይወትህን ኑር፡፡

ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡19

አንተን ስለበደለህ እንዲጠፋ ከመፈለግ ይልቅ ሰው እንዲለወጥ እንዲሻሻል እንዲመለስ ፀልይለት፡፡ አንተን ስለበደለ እንዲቀጣ ብቻ ሳይሆን በዚህ አጋጣሚ እንዲመለስ እንዲስተካከል ፈልግ፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡1

አንተ የበደለህ ሰው እርዳታህን በሚፈልግበት ጊዜ መርዳትህ እንዳልበደለህ አይናገርምና እርዳው፡፡ የበደለ ሰው ይታዘንለታል እንጂ አይቀናበትም፡፡

ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡20

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #ምህረት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 


Wednesday, June 10, 2020

The Source of Pride



Pride is one of the most dangerous attitudes we can have. It was pride that made Satan out of the great angel of God.
Sometimes pride is difficult to detect. But let’s see the other manifestations of pride to understand better about it.
Pride is discontentment.
Pride is to want more than we deserve. Pride is looking for luxury instead of being contented in necessity.
It shouldn’t be confused with confidence. Their sources are different and their motives are completely the opposite. Pride is poor me mentality in action. Pride is an overcompensation of the victim mentality.
The flip side of pride is an inferiority complex. Whoever wants to show him-self superior is suffering from an inferiority complex. The pride person is overcompensating his inferiority complex with that of the superiority one.
The person who is satisfied with who he is doesn’t need to prove anything. He just lives out his identity.
Abiy Wakuma Dinsa
For More Articles https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#God #Jesus #pride #humility #knowledge #rejoice # perseverance #trustgod #grace #salvation #church #testimony #rejoice #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

Wednesday, June 3, 2020

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ . . . ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ የማቴዎስ ወንጌል 21፡21

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ . . . ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ የማቴዎስ ወንጌል 21፡21