Popular Posts

Friday, May 11, 2018

ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ

ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፤ መዝሙር 32፡11
ራሳችንን እንመርምር ራሳችንን እንፈትን፡፡ ደስ እንዳይለን ያደረገው ነገር ምንድነው? ሰላማችንን የወሰደው ነገር ምንድነው? በእግዚአብሄር እንዳንመካ ያደረገን ነገር ምንድነው? እግዚአብሄርን እንዳናይ ያደረገን ነገር ምንድነው? ነገሮችን ጭልምልም እንዲልብን ያደረገን ነገር ምንድነው? ከእግዚአብሄር በላይ የገዘፈብን ነገር ምንድነው?
ምንም ይሁን ምንም በእግዚአብሄር ደስ እንዳንሰኝ የሚያደርገን ነገር መኖር የለበትም፡፡ እኛ ለክብሩ የሰራን የእግዚአብሄር ህዝቦች ነን፡፡
በደስታም ለእግዚአብሔር ተገዙ፥ በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ። እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። መዝሙር 100፡2-3
ለክብሩ ተፈጥረናል፡፡ ኢየሱስን የምንከተል ሁላችሁ የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡  
በሌላ በሌላ ነገር ደስ ላይለን ይችላል፡፡ ዘመኑ የሚያስፈራ ሊሆን ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር ግን ደስ ላለመሰኘት ምንም ምክኒያት የለንም፡፡
በብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ውስጥ ብናልፍም እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ በእኛ ላይ ያለው አላማ የፍቅር አላማ ብቻ ነው፡፡ ብዙ ነገሮች ፈር የለቀቁ ቢመስልም እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ነው፡፡
ሰዎች ስለሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም በደስታ ዝለሉ ይለናል ጌታ ኢየሱስ፡፡
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ሉቃስ 6፡22-23
ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ እግዚአብሄር አባታችን ነው፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
መከራ በእኛ ውስጥ የሚሰራው እጅግ መልካም ነገር በመሆኑ በመከራ እንኳን ደስ እንዳንሰኝ ምክኒያት የለንም፡፡  
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ያእቆብ 2፡2-3
እግዚአብሄርን ለሚወዱ ነገሮች ሁሉ በመጨረሻ ለእነርሱ በጎነት እንደሚሰረሩ ስለምናውቅ ደስ ይለናል፡፡
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
ማንም ደስ ላለመሰኘት ምክኒያትን ቢያገኝ እኛ ግን በእግዚአብሄር ደስ ላለመሰኘት ምንም ምክኒያት አናገኝም፡፡
ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፤ መዝሙር 3211
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ሲጠሉአችሁ #ሲለዩአችሁም #ሲነቅፉአችሁም #ደስታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ሃሴት #ሰላም  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment