አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡30
እግዚአብሄር መናቅ በፅንሰ ሃሳብ ደረጀ ብቻ ያለ በተግባር ግን የሌለ ነገር አይደለም፡፡ በየእለት ተእለት ኑሮዋቸው እግዚአብሄርን የሚንቁ ሰዎች አሉ፡፡ በአስተሳሰባቸው ለእግዚአብሄር ክብር የሌላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በአነጋገራቸው እግዚአብሄርን የማይፈሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በአደራረጋቸው እግዚአብሄርን የማያከብሩ ሰዎች አሉ፡፡
ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርህ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ 1ኛ ሳሙኤል 2፡30
ከእግዚአብሄር ይልቅ ታዋቂነታቸውን የሚያከብሩ ሰዎች እግዚአብሄርን ደስ አያሰኙትም፡፡ ከእግዚአብሄር ይልቅ ፍላጎታቸውን የሚያስቀድሙትን ሰዎች እግዚአብሄር አያከብሩትም፡፡ ከእግዚአብሄር ይልቅ ገንዘብን የሚያከብሩትን ሰዎች እግዚአብሄር አይደሰትባቸውም፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ስለኑሮ የሚጨነቁት ሰዎች እግዚአብሄርን አያስከብሩትም፡፡
ከእግዚአብሄር በላይ ማጣትን የሚያከብሩትን ሰዎች እግዚአብሄር አያከብርም፡፡
መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12
ከእግዚአብሄር በላይ የሰዎችን ፍላጎት የሚያርጉትን እግዚአብሄር አያከብርም፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ሰውንም ደስ ለማሰኘት የሚኖሩት እግዚአብሄርን አያከብሩትም፡፡
ወደ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ገላትያ 1፡10
የናቁትን ማክበር ለእግዚአብሄር አይሆንለትም፡፡ ያከበሩትን መናቅ ለእግዚአብሄር አይሆንለትም፡፡
የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። መዝሙር 51፡17
ያከበሩትን ያከብራል የናቁት ይናቃሉ፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2
አዳም እግዚአብሄርን ባላከበረ እና ባልታዘዘ ጊዜ ምድር እንኳን ለገመች እንደ ሃይሉዋ መጠንም መስጠት አቆመች፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ማክበር ሲያቆም እና ሲንቅ በተፈጥሮ ሁሉ ይናቃል፡፡
ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ። ዘፍጥረት 4፡12
አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡30
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #ሃዘን #ርህራሄ #የናቁኝም #ይናቃሉ #መልስ #ቁጣ #ፍርሃት #ናፍቆት #ቅንዓት #በቀል #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment