Popular Posts

Thursday, August 31, 2023

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል ክፍል 2



በእውነት
ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል . . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 534-5

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሃጢያታችንን ወስዶ ፅድቅን እንደሰጠን ሁሉ ኢየሱስ በመገረፉ በሽታችንን ወስዶ ፈውስን ሰጥቶናል፡፡ መስቀል የእኛ የሆነውን በእርሱ የእርሱ የሆነውን በእኛ የመለዋወጫ ቦታ ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የእኛን ድካም ወስዶ ብርታትን ሰጥቶናል፡፡  ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሙሉ ዋጋ የከፈለው እና ተፈፀመ ያለው ከሃጢያት ድነን በስጋ እንድንደክም አይደለም፡፡ ኢየሱስ ለሃጢያታችን ዋጋ ሲከፍል ለነፍሳችን መዳን እና ለስጋችን ፈውስ ሙሉ ዋጋ ለመክፈል ነበር፡፡  

ከእግዚአብሔር  ጋር ለመታረቅ እና የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ነፍሳችን ከሃጢያት እስራት ነፃ መሆን እንዳለባት ሁሉ በምድር ላይ በብርታት ጌታን እንድንከተለው እና እንዳገለግለው ከበሽታ እና ከደዌ መፈታት ነበረብን፡፡ እግዚአብሔርን እንዳናገለግለው የሚያደርገን ደዌ እና ህመም መፍትሄ ባይገኝለት ኖሮ ነፍሳችን ከሃጢያት ድኖ ስጋችን በህማም እና በደዌ የጠላት መጫወቻ ይሆን ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን መፍትሄ ሰጥቶ ስጋችንን ባይፈወስ ኖሮ ልክ እንደዳንን ወደመንግስተ ሰማይ ካልሄድን በስተቀር በምድር ላይ በብርታት ጌታን ማገልግል አንችልም ነበር፡፡

በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።የማቴዎስ ወንጌል 816-17

የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን ክፍል እንደሆነ ሁሉ የስጋ ፈውስ የመቤዠታችን አንዱ አካል ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም #ደዌ #ወንጌል #ፈውስ #ጤንነት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #በመገረፉ #ቁስል #ተፈወሳችሁ


Tuesday, August 29, 2023

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል ክፍል 1

 

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል . . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡4-5

ኢየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎዋል፡፡ ነፍሳችን ከሃጢያት እስራት እንድትድን ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሚያስፈልገውን ቅጣት ሁሉ በመቀጣት ሃጢያታችንን ወስዶዋል፡፡

እንዲሁም ኢየሱስ ስለ ህመማችን እንዲሁ በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎዋል፡፡ ኢየሱስ ደዌያችንን በመስቀል ላይ ተሸክሞዋል፡፡

ኢየሱስ ስለ ሐጢያታችን በመስቀል ላይ ዋጋ በመክፈሉ የተነሳ በሃጢያት መኖር እንደሌለብን ሁሉ ኢየሱስ ስለ ፈውሳችን ስለተገረፈ በደዌ መኖር የለብንም፡፡

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ #በመገረፉ #ቁስል #ተፈወሳችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡24

የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን ክፍል እንደሆነ ሁሉ የስጋ ፈውስ የመቤዠታችን አንዱ አካል ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም #ደዌ #ወንጌል #ፈውስ #ጤንነት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል


ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 8

 

አብዛኛው ወንጌልን የሚሰሩ አብዛኛው አገልጋዮች ከእግዚአብሔር ነው አንጂ በሰው አይከፈላቸውም፡፡ አብዛኛዎቹ የወንጌል አገልጋዮች በስጦታቸው ብቻ ሳይሆን በገንዘባቸውም ጌታን በደስታ ያገለግላሉ፡፡

ለምሳሌ በዘማሪነት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እግዚአብሔር ከሰጣቸው ስጦታ በተጨማሪ ለስልጠና ተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ አውጥተው ጌታን ያገለግላሉ፡፡ አብዛኛዎቹ መክፈል ችለው በደስታ በገንዘባቸውም ጭምር ጌታን ያገለግላሉ፡፡ ቤተክርስትያን አቅሙ ኖሮዋት በተለይ መክፈል የማይችሉትን ብትከፍል ለቤተክርስቲያንም በረከት ነው፡፡ ምክኒያቱም ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ስጦታቸውን ከመስጠታቸው በተጨማሪ ገንዘባቸውን መስጠታቸው ተጨማሪ መስዋእትነት ነው፡፡

ሳይከፈላቸው የሚያገለግሉት የወንጌል አገልጋዮች አገልግሎት እጅግ እየሰፋ ይመጣል፡፡ አገልግሎቱ እየሰፋ በመጣ መጠን አገልግሎታቸው ተጨማሪ ጊዜያቸውን እየፈለገ መምጣት ይጀምራል፡፡ ታዲያ አገልግሎታቸው ይሰፋና በትርፍ ጊዜታቸው ብቻ ማገልገል የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ይደርሳሉ፡፡ በትርፍ ጊዜ ብቻ ማገልገል የማይቸሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ በሌላ ሙያ የሚሰሩትን ስራ ጥለው መውጣት ግድ ይላቸዋል፡፡ ታዲያ ቤተክርስትያን ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመሸፈን በተጨማሪ ጊዜያቸው በወንጌሉ ላይ እንዲያተኩሩ ትጠይቃቸዋለች፡፡

አገልጋዮቹም በእግዚአብሔር በመታመን በሌላ ሙያ የሚሰሩትን ስራቸውን ትተው በአብዛኛው ጊዜያቸው ወንጌልን ለማገልገል እና በወንጌል ለመኖር ይወስናሉ፡፡

ሁላችንም የወንጌል አገልጋዮች ነን፡፡ የወንጌሉም አገልጋዮች በትርፍ ጊዜያቸው ብቻ ለሚሰራ አገልግሎት ወጪያቸውን እንድትሸፍን ቤተክርስቲያን ላይ ሊከብዱባት አይገባም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


Monday, August 28, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 7

 

እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡14

ወንጌልን የሚሰብኩ ሁሉ በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ በግልፅ በተጻፈው በእግዚአብሔር አሰራር ማመን አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ አገልጋዮቹን በደንብ መንከባከብ እንዳለበት ሁሉ ወንጌልን የሚሰብኩ ስለኑሮዋቸው የገቢ ምንጭ የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

ወንጌልን የሚሰብኩ በወንጌል ከመኖር ይልቅ ከተፃፈው ውጭ ለራሳቸው ሌላን መንገድ ማዘጋጀት የለባቸውም፡፡

አንዳንድ የወንጌሉ ሰባኪዎች ስለመሰረታዊ ፍላጎታቸው መሟላት በእግዚአብሔር ላይ ከመታመን ይልቅ የራሳቸውን ዘዴ ይቀይሳሉ፡፡ አንዳንዶቹ እግዚአብሔር ሳይናገራቸው የቤተክርስቲያንን የገቢ ማስገኛ ንግድ ያቋቁማሉ፡፡

አንዳንዶቹ ደግሞ ቤተክርስቲያን በህዝቡ መስጠት ላይ እንዳትደገፍ የራስዋ የገቢ ማስገኛ ሌሎች መንገዶች ያደራጃሉ፡፡

የወንጌሉ ሰባኪዎች በዋነኝነት በመፅሃፍ ቅዱስ ስለእነርሱ በተፃፈው በእግዚአብሔር የአቅርቦት አሰራር ላይ ብቻ መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርም ያልተናገራቸውን ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ በማቋቋም ለቅዱሳን ነፍስ ከመትጋት መደናቀፍ የለባቸውም፡፡ ይልቁንም በእምነት በእግዚአብሔር አሰራር ላይ በመታመን ለቅዱሳን አገልግሎት መትጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡6

ከእግዚአብሔር አሰራር ውጭ የሆነ ማንኛውም የገቢ ማስገኛ ዘዴ የእግዚአብሔርን ምሪት የሚጠይቅ ነው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር በግልፅ ካልተናገረ በስተቀር የቤተክርስትያንን ውጤታማነት ሊቀንስ የሚችል አደገኛ አካሄድ ነው፡፡

ለራስህ ታላቅን ነገር ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልገው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 45፡5

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


Sunday, August 27, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 6

 


ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 6

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግንአስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።የማቴዎስ ወንጌል 632-33

ክርስቶስ ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን በህይወት የመጀመሪያው ስራችን የእግዚአብሔርን ፅድቅናመንግስቱን መከተል ነው፡፡ 

ለእኛ ለእግዚአብሔር ልጆች ስለምንበላው ስለምንለብሰው መጨነቅ አይመጥነንም፡፡ ይልቁንምትኩረታችን መሆን ያለበት የእግዚአብሔር  መንግስት ጥቅም መጠበቅ እና በመንግስቱ መስፋት ላይነው፡፡ 

የሰው አገልግሎት ሊከፍል የሚችል የገንዘብ መጠን የለም፡፡ ሰው የሚከፈለው ስለአገልግሎቱ ሳይሆንበምድር ላይ ለመኖር ስለሚያስፈልገው ወጪ ብቻ ነው፡፡ 

ሰው ስለአገልግሎቱ የሚከፈለው በእግዚአብሐር ብቻ ነው:: 

በተለይ የወንጌል አገልጋይ እግዚአብሔር ፍላጎቴን የሚያሟላው የእርሱ ልጅ ስለሆንኩኝ ብቻ ነውብሎ ማመን አለበት፡፡ ወንጌልን የሚሰራ የሚያገለግለው ህዝብ እንደሚገባው ባይንከባከበው እንኳንእግዚአብሔር ጉድለቱን እንደሚሸፍን በእግዚአብሔር አሰራር መታመን አለበት፡፡ 

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል#እግዚአብሔር #ገቢ


Saturday, August 26, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 5

 

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 5

ለሌዋውያንም እድል ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄዱ ተመለከትሁ። መጽሐፈ ነህምያ 13፡10

በብሉይ ኪዳን የሌዋዊያን እድል ፈንታቸው ከህዝቡ የሚሰበሰበው መዋጮ ነበር፡፡ ህዝቡ ሃላፊነቱን ስላልተወጣ ሌዋዊያኑ የእግዚአብሔር ቤት ስራ ትተው ወደ እርሻ ስራ ሄደው ነበር፡፡ 

በአዲሱም ኪዳን የእግዚአብሔር ቃል እንዲያሸንፍ ፣ የእግዚአብሔር ህዝብ በሚገባ እንዲመገብ እና እንዲጠበቅ  የእግዚአብሔር ህዝብ ለነፍሱ የሚተጉትን የወንጌል ሰራተኞችን የመንከባከብ ሃላፊነት አለበት፡፡ 

አብዛኛው ጊዜያቸውን በወንጌል ስራ ላይ የሚያሳልፉትን በሚያስፈልጋቸው ነገር መንከባከብ ለቤተክርስትያን ፣ ለእግዚአብሔር አሰራር ፣ ለወንጌል እና ለእግዚአብሔር መንግስት ያለንን አክብሮት ያሳያል፡፡

በቤተክርስቲያን የወንጌል ሰራተኞች የሚደረግልንን አገልግሎት ካከበርን እና ዋጋ ከሰጠን ለእነርሱ የእለት ተእለት ወጭ መሸፈኛ የሚሆንን ነገር መስጠት ትልቅ ነገር አይሆንብንም፡፡

እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡11

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ

Friday, August 25, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 4

በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል። መጽሐፍ፦ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥ ደግሞ፦ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5:17-18

በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያመንን ሁላችን  የመጀመሪያው ሙያችን ወንጌል ነው፡፡ ክህንነት ሁላችንም የምንሰራው የመጀመሪያው ጥሪያችን ነው፡፡ እንዲሁም የአለም ብርሃን እና የምድር ጨው ለመሆን የምንሰማራበት ሙያ ደግሞ ይኖረናል፡፡

በዋነኝነት ግን የምናገለግለው ጌታ ክርስቶስን ነው የርስትም ብድራት የምንቀበለው ከእርሱ ነው፡፡

ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና።ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡22-24

ወንጌል በመስበክ እና በማስተማር የሚተጉት አገልጋዮች ግን እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ከሌላ ሙያ ገንዘብ አያገኙም፡፡ ታዲያ በመስበክ እና በማስተማር የሚደክሙት ለኑሮ በሚያስፈልጋቸው የሚንከባከቡት በተለያየ ሙያ ላይ ተሰማርተው ገንዘብ የሚያገኙ ቅዱሳን ናቸው፡፡

ይህ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ አብዛኛው ጊዜያቸውን ለወንጌል ለሚሰጡት አገልጋዮች ገንዘብን መስጠት ሊደረግ የሚገባ ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ እንዲሁም ወንጌልን የሚሰሩ አገልጋዮች ደግሞ ካለ መሸማቀቅ እና ካለመሳቀቅ ከሌሎች ቅዱሳን ገንዘብን ሲቀበሉ ይገባቸዋል፡፡   

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


 

Thursday, August 24, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 3

 

እንዲሁ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቍጠረን። እንደዚህም ሲሆን፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡1-2

ወንጌልን የሚሰብኩት አገልጋዮችን የኑሮ ወጪ የመሸፈን ሃላፊነት ያለበት ወንጌል የሚሰበክለት እና በእግዚአብሔር ቃል እውቀት የሚመገበው ህዝብ ነው፡፡

ነገር ግን በቃሉ መጋቢዎች ዘንድ ለቃሉ እና ለፀሎት ራስን ለመለየት የታመነ ሆኖ መገኘት ይጠይቃል፡፡ መጋቢዎች ቃሉን ለማንበብ ፣ ለማጥናት ፣ ለማሰላሰል እንዲሁም ለህዝቡ በመፀለይ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ሊሰጡ ይገባቸዋል፡፡

መጋቢዎች የእግዚአብሔርን ፊት ለመፈለግ ከእግዚአብሔር የሆነን መልእክት ለማምጣት መንጋውን የለመለመ ሳር ለመመገብ በእግዚአብሔር ፊት መቆየት አለባቸው፡፡

መጋቢዎች በሌሎች ስራዎች ላይ ከተሰማሩ ክርስቲያኖች እኩል በተለያየ በወንጌል ባለሆነ ነገር ተጠምደው ቆይተው ህዝቡን በሚገባ ሊመግቡት በፍጹም አይችሉም፡፡

መጋቢዎች ሌላ ስራ እንዳይሰሩ የተፈለገበት ምክኒያት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቃል እና ለፀሎት እንዲለዩ ነው፡፡ መጋቢዎች ራሳቸው ወጥተው ከመስራት ይልቅ ሌሎች ሰርተው ለእግዚአብሔር ቤት በሰጡት ገንዘብ እንዲኖሩ ያስፈለገበት ምክኒያት የእግዚአብሔርን ፊት ለመፈለግ አብዛኛውን ጊዜያቸውን እንዲሰጡ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ



Wednesday, August 23, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 2

 

እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡11

አብዛኛው ጊዜያቸውን መንፈሳዊውን ነገር በመዝራት የሚያሳልፉ አገልጋዮች መንፈሳዊ ነገር ከሚዘሩባቸው አገልጋዮች ስጋዊውን ነገር ቢያጭዱ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡

እነዚህ አገልጋዮች አብዛኛውን ጊዜያቸውን በፀሎት እና በቃሉ አገልግሎት የሚተጉ አገልጋዮቻችን ናቸው፡፡

መንፈሳዊ ነገር የሚዘራበት ሰው ሁሉ አብዛኛውን ጊዜያቸውን መንፈሳዊውን ነገር ለመዝራት የሰጡትን አገልጋዮች በስጋዊ ነገር የመንከባከብ ሃላፊነት አለበት፡፡

መንፈሳውን ነገር የሚዘሩ አገልጋዮች በሚያገለግሏቸው ሰዎች ስጋዊ ፍላጎታቸው ካልተሸፈነ በስተቀር ለፀሎት እና ለቃሉ የሚተጉ አገልጋዮችን ማግኘት አይቻልም፡፡

በህይወቱ ላይ ለሚዘራው ለመንፈሳዊው ነገር አክብሮት ያለው ማንኛውም ሰው ስጋዊውን ነገር ለማካፈል ወደኋላ አይልም፡፡

በህይወቱ ላይ መንፈሳዊውን ነገር ለሚዘሩ አገልጋዮች እውቅና የሚሰጥ ማንኛውም ሰው ስጋዊ ነገርን መዝራቱ እንደ ትክክለኛ ነገር እንጂ እንደ እንግዳ ነገር አይመለከተውም፡፡

ቤተክርስትያን የምታድገው እና የምታሸንፈው እነዚህ ለቤተክርስትያን የተሰጡ አገልጋዮች ለፀሎት እና ለቃል እንዲተጉ በስጋዊ ነገራቸው ላይ የሚዘራ የቅዱሳን ህብረት ሲኖር ብቻ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


Tuesday, August 22, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል

 

በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን? እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡13-14

በወንጌል ስራ ላይ ለማተኮር አብዛኛው ጊዜያቸውን ለወንጌል ስራ የሚሰጡ አገልጋዮች በምድር ላይ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት የወንጌል ማህበርተኞች ከሚያዋጡት መዋጮ ነው፡፡

እውነት ነው ሁሉም ሰው ወንጌልን ይሰራል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው አብዛኛው ጊዜውን ለወንጌል ስራ አይሰጥም፡፡

አብዛኛው ጊዜያቸውን ለወንጌል ስራ የሚሰጡ አገልጋዮች ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት በስራ ቦታ ወጥተው ከሚሰሩት የወንጌል ሰራተኞች መዋጮ ነው፡፡

ሌሎች በስራ ቦታቸው ገንዘብ ሰርተው መጥተው ለወንጌል ሰባኪው ገንዘብ ሲሰጡ ለወንጌል ሰባኪ መልካም ስሜት ላይሰጠው ይችላል፡፡

ነገር ግን ጌታ የደነገገው የጌታ አሰራር ይህ ነው፡፡ የወንጌል ሰባኪው በስራ ቦታ ሰርቶ ገንዘብን ማግኘት ይችላል፡፡ የወንጌል ሰባኪው በስራ ቦታ ሰርቶ የራሱን ገንዘብ ማግኘት ሲችል ሌሎች የሰሩትን ገንዘብ አምጥተው ሲሰጡት ቢሰማውም የእግዚአብሔርን አሰራር ማክበር ግን አለበት፡፡

በዋነኝነት ወንጌልን የሚሰብክ ሰው ከስሜቱ ይልቅ  የእግዚአብሔርን አሰራር በትህትና ማክበር አለበት፡፡ በዋነኝነት ወንጌልን የሚሰብክ አገልጋይ የእኔነት ክብሩን ዋጥ አድርጎ ጌታ የደነገገውን አሰራር መከተል ይኖርበታል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


Monday, August 21, 2023

ንስሐ በራስ መንገድ እግዚአብሔርን እንደገና ማስደሰት አይደለም

እናንተም። እግዚአብሔርን በድለናል አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት። እግዚአብሔርም፦ እኔ በእናንተ መካከል አይደለሁምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው አለኝ። እኔም ተናገርኋችሁ እናንተ ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ ንብ እንደምታሳድድም አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ። ኦሪት ዘዳግም 1፡41-44

እስራኤላዊያን ጠላቶቻቸውን ተዋግተው ወደ ከንአን መግባት በነበረባቸው ጊዜ አንወጣም አንዋጋም ብለው በእግዚአብሔር ትእዛዘ ላይ አመፁ፡፡

እግዚአብሔር በአመፃቸው ላይ ተቆጣ እና እንዲገስጻቸው ሙሴን ላከላቸው፡፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሔር ደስ እንዳልተሰኘባቸው እና እንዳዘነባቸው ሲያውቁ አሁን እንወጣለን ጠላታችንን እንዋጋለን ብለው አቀዱ፡፡ እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት በመካካላችሁ አይደለሁም አትዋጉ ብሎ ተናገራቸው፡፡ በጠላቶቻችሁ ላይ የመውጣት ጊዜው አይደለም ብሎ የተናገራቸውን ትእዛዝ አልሰሙትም ቀጥለው አሞራዊያንን ለመግጠም ወደጦርነት ወጡ፡፡ ውጤቱም ሽንፈት ነበር፡፡

ከዚህ የእስራኤል ታሪክ እንደምንረዳው ንስሃ መግባት በጣም አስፈላጊ ቢሆንም ከንስሐ በኋላ እግዚአብሔርን ለማስደሰት በራሳችን የምንሄደው እርምጃ ትክክል እንዳልሆነ አንማራለን፡፡

እስራኤላዊያን ማድረግ የነበረባቸው ያለፈ አልፎዋል እግዚአብሔር አሁን ምን እንደሚለን እንሰማለን እንታዘዘዋለን በማለት ልባቸውን ለሚቀጥለው የእግዚአብሔር ትእዛዝ ማዘጋጀት ብቻ ነው፡፡

የእነርሱ በራሳቸው ጊዜ ለመዋጋት መውጣት አንዋጋም ለሚለው አመፅ ማካካሻ ሊሆን በፍፁም አይችልም፡፡ ያለፈው እግዚአብሔርን የመታዘዣ እድል አምልጦዋል፡፡ እስራኤላዊያን ሌላ እግዚአብሔርን የመታዘዣ እድል መጠበቅ አለባቸው እንጂ በራሳቸው ሌላን እድል መፍጠር አይችሉም፡፡

ንስሃ መግባት እግዚአብሔር አታድርግ ያለውን እሺ ጌታዬ አላደርግም ማለት እግዚአብሔር አድርግ ያለውን ደግሞ እሺ አደርጋለሁ ማለት ነው፡፡

ከዚህ ያለፈ ካለምንም የእግዚአብሔር ተጨማሪ ትእዛዝ ስለሰራነው ሃጢያት ማካካሻነት በራስ አነሳሽነት ለመካስ መሞከር ስህተት ውስጥ ይጨምረናል፡፡

በሰሩት ሃጢያት ተፀፅቶ በራስ አነሳሽነት ስህተትን በስህተት ለማስተካከል መሞከር ተጨማሪ ስህተተን መስራት ነው፡፡

ንስሃ እንደገባን እግዚአብሔርን ለመታዘዝ በተዘጋጀ ልብ ጌታ ሆይ አሁን ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ ብሎ መጠየቅ በቂ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ንስሐ #አእምሮንማደስ #አሳብንመቀየር #መንገድንመቀየር #በረከት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ክርስትና


 

Sunday, August 20, 2023

ንስሐ መዞር ነው

 

በስህተት ወደ ምእራብ 100 ሜትር የተራመደ ሰው ወደ ምስራቅ ለመዞር መቶ ሜትር መራመድ አይጠበቅበትም፡፡ ወደ ምስራቅ ለመዞር የሚጠበቅበት መዞር ብቻ ነው፡፡

ንስሐን ከሚገባው በላይ ውስብስብ የምናደርገው መፅሃፍ ቅዱስ ስለንስሐ ያላለውን ስንል ነው፡፡

እግዚአብሔር ለመፈፀም የሚቻልን እንጂ የማይቻልን ነገር እንድናደርገው አያዘንም፡፡ ንስሐ መግባት ይቻላል፡፡ መመለስ ይቻላል፡፡ ንስሐ መግባት የማይቻል እና የማይደረስበት ረቂቅ ነገር አይደለም፡፡

ንስሐ ማለት የተራመድነውን ርቀት ያህል ተመልሶ መራመድ ስለሚመስለን ስለንስሐ ስናስብ እንደክማለን፡፡ ንስሐ ለመግባት እና ለመመለስ የተሳሳትንበትን ጊዜ ሁሉ እንደገና ወደተቃራኒው አቅጣጫ መድገምን የሚጠይቅ ስለሚመስለን አስቀድመን ተስፋ እንቆርጣለን፡፡

ንስሐ የቀደመው ሐጢያታችንን ዋጋ ሁሉ ዋጋ መክፈል ስለሚመስለን ንስሐ ከመግባት ይልቅ በጥፋታችን መቀጠል እንመርጣለን፡፡

ንስሐ የቀደመውን መንገድ ትቶ ለእግዚአብሔር መንገድ እሺ ማለት ነው፡፡ በንስሐ ስለቀደመው ሃጢያታችን ዋጋ መክፈልን የሚያስተምር የተሳሳተ ሃይማኖት የአምልኮ መልክ እንጂ ክርስትና አይደለም፡፡

ንስሐ ለእግዚአብሔር ሃሳብ እሺ ማለት ነው፡፡ ንስሐ ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር መስማማት ነው፡፡ ንስሃ እንደገና እግዚአብሔርን ለማስደሰት መወሰን ነው፡፡

ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 1፡18-19

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ንስሐ #አእምሮንማደስ #አሳብንመቀየር #መንገድንመቀየር #በረከት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ክርስትና


Saturday, August 19, 2023

ንስሐ መንገድን መቀየር ነው

 

አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። ትንቢተ ኢዮኤል 2፡12-13

ንስሐ ማልቀስ አይደለም፡፡ ንስሐ መፀፀት አይደለም፡፡ ንስሐ ስለሃጢያታችን ራሳችንን መቅጣት አይደለም፡፡ ንስሐ ስለሃጢያታችን ራሳችንን ማጎሳቆል አይደለም፡፡

ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡7

ንስሐ ሃሳብን መቀየር ነው፡፡ ንስሐ መንገድን መቀየር ነው፡፡ ሰው ባያለቅስም እንኳን የተሳተ መንገዱን መንገዱን እስከቀየረ ድረስ የእግዚአብሔርብ ልብ ደስ ያሰኛል፡፡

አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው። ትንቢተ ኤርምያስ 18፡11

ንስሐ ያደርጉት የነበረው ነገር የተሳተ እንደሆነ ሲረዱ መመለስ ማለት ነው፡፡ ንስሐ ማለት መደረግ የነበረበት ነገር እንዳልተደረገ ሲረዱ ለማድረግ መወሰን ማለት ነው፡፡

#ኢየሱስ #ጌታ #ንስሐ #አእምሮንማደስ #አሳብንመቀየር #መንገድንመቀየር #በረከት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ክርስትና


Thursday, August 17, 2023

የንስሃ ጥሪ

 

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20

ንስሃ የመፅሃፍ ቅዱስ ዋና አስተምሮ ነው፡፡

ንስሃ የክርስትና ዋና ትምህርት ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ ትምህርትም ነው፡፡ ሰው የንስሃ ትምህርት ካልገባው እስከሚገባው መማር አለበት እንጂ ወደ ሌሎች ትምህርቶች ፈጥኖ ማለፉ ዋጋ የለውም፡፡ ሰው ንስሃ ካልገባው ክርስትና አይገባውም፡፡

ዴሪክ ፕሪንስ የተባሉት በብዙ የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የሚጠቀሱት ታዋቂው የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪ ስለንስሃ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ በቤተክርስትያን ውስጥ አጅግ አስቸጋሪ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች እንደሆኑ ፣ በቤተክርስትያን የማያድጉ እና የማይለወጡ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች እንደሆኑ እና በቤተክርስትያን ፍሬን የማያፈሩ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች እንደሆኑ ተናግረው፡፡

በክርስትና በቆየሁበት ዘመን ይህንን ተመልክቻለሁ አባባላቸው እውነት እንደሆነ እኔም እመሰክራለሁ፡፡

ክርስቲያን መስሎ ነገር ግን ንስሃ የማይገባ ሰው እግዚአብሔርን ለማሞኘት አንደሚሞክር ሰው ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ንስሃ #አእምሮንማደስ  #አሳብንመቀየር #መንገድንመቀየር #በረከት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ክርስትና


እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:7 ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29:11

 

እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1 የጴጥሮስ መልእክት 5:7

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29:11


Sunday, August 13, 2023

ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም

 

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 33

ሰው ከእናት እና ከአባቱ በመወለድ ወደዚህ ምድር ውስጥ ይገባል፡፡ ወደዚህ ምድር ለመግባት ከአባት እና ከእናት መወለድ የግዴታ ነው፡፡ ከእናት እና ከአባት ያልተወለደ ሰው ወደዚህ ምድር መግባት በፍፁም አይችልም፡፡ ከአባት እና ከእናት ከመወለድ ውጭ ወደዚህ ምድር የመግቢያ ሌላ ምንም መንገድ የለም፡፡

ሰው ወደዚህ ምድር ለመግባት ከሰው መወለድ እንዳስፈለገው ሁሉ ሰው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ከእግዚአብሔር መወለድ አለበት፡፡

ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። የዮሐንስ ወንጌል 3፡5

ሰው ከሰው መወለዱ ብቻ ከእግዚአብሔር ለመወለድ ብቁ አያደርገውም፡፡ ሰው ለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለእርሱ ሃጢያት እንደተለት እና ከሙታን እንደተነሳ በማመን ዳግመኛ መወለድ ያስፈልገዋል፡፡

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡9-10