Popular Posts

Wednesday, May 2, 2018

የሰው መጠበቅና የእግዚአብሄር አሰራር

እግዚአብሄር የራሱ አሰራር መንገድ አለው፡፡ እግዚአብሄር በእኛ መጠበቅ ውስጥ የማይገባበት ጊዜ አለ፡፡  እግዚአብሄር ሁሉን ለራሱ ሊያስገዛ የሚችልበት አሰራር አለው፡፡ ከምንም ነገር ውስጥ የተሻለ ነገር ለማውጣት የሚችለበት አሰራር አለው፡፡
እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል። ፊልጵስዩስ 3፡21
ሰው የሚጠብቀው እግዚአብሄር ወዲያው እንዲፈርድ ነው፡፡
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? ኢሳያስ 40፡27
እግዚአብሄር የሚፈልገው እርሱ እስኪፈርድ ድረስ ሰው እንዲታገስ ነው፡፡
ሰው የሚጠብቀው በፊቱ ያለው ተራራ እንዲነሳ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው አንዳንዴ ሰው ተራራውን እንዲወጣው ነው፡፡ እግዚአበሄር ሃይልን ይሰጣል፡፡
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ኢሳያስ 40፡29
ሰው የሚፈልገው አስቸጋሪ ነገሮች ሁልጊዜ ከፊቱ እንዲነሱ ብቻ ነው፡፡  
እግዚአብሄር የሚፈልገው በአስቸጋሪ ነገር ውስጥም ቢሆን ሰው እግዚአብሄርን እንዲያከብር ነው፡፡
ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ 2 ጢሞቴዎስ 4፡2
ሰው የሚፈልገው እንዳይደክም ነው፡፡
እግዚአበሄር የሚፈልገው በራሳችን ብንደክምም እንኳን በክርስቶስ እንድንበረታ ነው፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9-10
ሰው የሚፈልገው በነገሮች ደስ እንዲለው ነው፡፡
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። ማቴዎስ 5፡4
እግዚአብሄር የሚፈልገው በነገሮችም ብናዝን በእርሱ በጌታ ሁልጊዜ ደስ እንዲለን ነው፡፡
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡4
ሰው የሚፈልገው በሁሉ ነገር ተስፋ እንዲኖረው ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው ተስፋ በሌለን ጊዜ የእግዚአብሄርን ተስፋ ብቻ ይዘን እንድናምን ነው፡፡
ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። ሮሜ 4፡18
ሰው የሚፈልገው የውጭን ሰላም ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው በውጭው መረበሽ መካከል ያለውን የውስጥ እውነተኛ ሰላም ነው፡፡
አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ፊልጵስዩስ 4፡7
ሰው የሚፈልገው ሰው በሚታየው ነገር ሁሉ እንዳይጎድል ነው፡፡  
እግዚአብሄር የሚፈልገው ብናገኝም ባናገኝም በክርስቶስ ሁሉን እንድንችል ነው፡፡
መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12-13
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መኖሪያህእግዚአብሄር #እውቀት #ጥበብ #ሃይል #እንፍዋለት #አልፋ #ኦሜጋ #መጀመሪያ #መጨረሻ #ክርስትያን #አማርኛ #መደገፍ #ማስተዋል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ፅድቅ #ማመን #አይመረመርም #ስልጣን

No comments:

Post a Comment