የማዳንህን
ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። መዝሙር 51፡12
እግዚአብሄር
እኛን ለማዳን ሳይራራ አንድያ ልጁን ከፍሎዋል፡፡ ስለመዳናችን እጅግ ታላቅቅ ዋጋ ተከግፍሎዋል፡፡ መዳመናችንም ታላቅ ነው፡፡
ስለመዳናችን የምንሰማውን ነገር ልንጠነነቀቅ ይገባናል፡፡
መዳናችንን የሚያሳንስ ነገር የምንሰማ ከሆነ ህይወታችን በአደጋ ውስጥ ነው፡፡ ከምንም ነገር በላይ መዳናችንን ቸል ለንለው አይገባንም፡፡
ስለመዳናችን እግዚአብሄርን በየጊዜው እንደ አዲስ ልናመሰግነው ይገባል፡፡
ስለዚህ
ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል። በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ዕብራውያን 2፡2
የዳንነው ከሞት ነው፡፡
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሃንስ 5፡24
የዳንነው ለዘላላም ከእግዚአብሄር ጋር ከመለያየት
ነው፡፡
በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ማቴዎስ 25፡41
የዳንነው
ከጨለማው ስልጣን ነው፡፡
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1፡13-14
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1-2
የዳንነው የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ ከመኖርና
ህይወትን ካለማየት አሰቃቂ ህይወት ነው፡፡ የፈለስነው ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት ነው፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር
ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
ይህንን
መዳን የሚገባውን ስፍራ ካልሰጠነው ፣ ይህን መዳን ስናቃልልና ይህ መዳን ሲያንስብን በክርስትና ህይወታችን ሁሉ ነገራችን ይዛባል፡፡
ይህን
ታላቅ መዳን በራሱ እንደሃብት ሳይሆን ግን እንደ መተላለፊያ ብቻ ስንቆጥረው ህይወታችን ይዛባል፡፡ ይህን መዳን በራሱ ታላቅ እድል
እንደሆነ ስንረሳና እንደ ማትረፊያ መንገድ ብቻ ስናየው ህይወታችን በአደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡
በትዕቢት
ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም
ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን
በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡4-5
ይህን
መዳን ስናከብረው በመዳናችን ደስ ስንሰኝ እግዚአብሄርን እንደሚገባው ማክበር እንችላለን፡፡ በዚህ መዳን ሳናቋርጥ ደስ ስንሰኝ ህይወታችን
ሁሉ በምስጋና ይለመልማል፡፡ ይህን ታላቅ መዳን ስናከብረው በሁሉ ነገር እግዚአብሄርን በደስታ እንታዘዘዋለን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት
#ደህንነት #ደስታ
#መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ቃል #ፍጥረት
#ልጅነት #ስራ
#እምነት #አምባሳደር
#ብርሃን #ጨው
#ልጅነት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment