Popular Posts

Monday, July 31, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 3

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።የሉቃስ ወንጌል 121

የፈሪሳዊያን ትምህርት ተጠበቁ ሲባል አንድን የህብረተሰብ ክፍል ወይም አንድን ሃይማኖት የሚመለከት በፍፁም አይደለም፡፡

የፈሪሳዊነት አስተሳሰብ እኔ ስጋ ውስጥ አለ ፣ አንተ ስጋ ውስጥ አለ እንዲሁም አንቺ ስጋ ውስጥ አለ፡፡

ፈሪሳዊነት ካለእውቀት የሆነ የሃይማኖት ቅናት ነው፡፡ ካለእውቀት መቅናት እያንዳንዳችን ይብዛም ይነስም በህይወት ዘመናችን የሚያጋጥመን ድካም ነው፡፡

በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡2-3

ፈሪሳዊነት ለመንፈሳዊ ችግር መንፈሳዊ ያልሆነ መልስ ለመስጠት መሞከር ነው፡፡ ፈሪሳዊነት መንፈሳነትን በወግ እና በስርአት መተካት ነው፡፡ ፈሪሳዊነት ከዳንን በኋላ እግዚአብሔርን ማስደሰቻ መንገድን ትቶ በፈጠራ ችሎታ ሌላ ማስደሰቻ መንገድ ለመፍጠር መሞከር ነው፡፡  

ስለፈሪሳዊነት ሲነሳ እነርሱ እና እኛ ብለን ካሰብን ከትምህርቱ ተጠቃሚ ሳንሆን እንቀራለን፡፡ በገርነት እና በየዋህነት "እኔ እሆንን?" ማለት ህይወታችንን እንድንፈትሽ እና እንድንለውጥ ያስችለናል፡፡

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። የዮሃንስ ወንጌል 8፡32

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳዊ #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ፃፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃዊያን

Sunday, July 30, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 2

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።የሉቃስ ወንጌል 121

ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ጊዜ ፈሪሳዊያን ሰዲቃዊያን እና ጻፎች የሚባሉ የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች የእግዚአብሔርን ነገር የሚያስቀድሙ መንፈሳዊ መሪዎች አልነበሩም፡፡ ይልቁንም መንፈሳዊ አይታ የጠፋባቸው በመንፈሳዊ ነገር ምትክ የአምልኮት መልክ ብቻ የነበራቸው ነበሩ፡፡  

ፃፎች እና ፈሪሳዊያን የሃይማኖቱ አላማ የጠፋባቸው በእውነተኛው አምልኮ ምትክ የውጫዊ ስርአትን የተኩ እና ይህ ነው ሃይማኖት ብለው ለመማርም ብሎም ለመለወጥም ያልተዘጋጁ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነርሱብ በተመለከተ ሰው ውጫዊውን ነገር ከጠበቀ ውስጣውን የልብ ህይወቱን ንፁህ ማድረግ አይጠበቅበትም ነበር፡፡ ለእነርሱ ሃይማኖት የውጭ ትእይንት ብቻ ነበር፡፡

እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች የውስጥ የልብ ነገራቸውን ስለረሱት ማተኮር ያለባቸው በልብ ነገር ላይ እንደሆነ ኢየሱስ ይናገራቸው ነበር፡፡

ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም። የማቴዎስ ወንጌል 15፡16-20

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ጻፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን

Saturday, July 29, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 1

“አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።” የሉቃስ ወንጌል 12፡1

ኢየሱስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ” በማለት ደቀመዛሙርቱን በብርቱ ያስጠነቅቃቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ በአፅንኦት ከፈሪሳዊያን እርሾ ተጠበቁ ብሎ ያስጠነቀቀበት ምክኒያቱ የፈሪሳዊያን ትምህርት ደቀመዛሙርቱን በክርስቶስ እውነተኛ እውቀት ፍሬ ቢስ ሊያደርገን የሚችል አደገኛ አካሄድ ስለሆነ ነው፡፡

የፈሪሳዊያን ትምህርት ማለት በውጫዊ ነገር ላይ ብቻ ያተኮረ የአስመሳይነት ትምህርት ነው፡፡ የፈሪሳዊያን ትምህርት ማለት በህይወት መውጫ በሆነው በዋናው በልብ ሁኔታ ላይ ያላተኮረ ነገር ግን በውጫዊ አነጋገር እና አለባበስ ላይ ብቻ ያተኮረ የእውነተኛው መንፈሳ ህይወት ርካሽ ማስመሰያ ትምህርት ነው፡፡

የፈሪሳዊያን ትምህርት ለታይታ ብቻ የሆነ በእውነተኛው መንፈሳዊ ህይወት ላይ የማያተኮር ትምህርት ነው፡፡ የፈሪሳዊያን ትምህርት ልብን የማይፈትሽ ለሃይማኖት መልክ እንጂ ለመንፈሳዊነት ምንም ግድ የሌለው ትምህርት ነው፡፡

የፈሪሳዊያን ትምህርት የሃይማኖት መልክ ያለው የእግዚአብሔርን ሃይል የካደ ትምህርት ነው፡፡

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2 ወደ ጢሞቴዎስ 3፡5

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳዊ #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ፃፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃዊያን

Friday, July 28, 2023

አንድነት ሌላው እንደራስ መቀበልን ይጠይቃል

የእይታ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አብዛኛውን ጊዜ አብዛኛው ሰው የሚያቀርበው አሳብ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የሚያስቡት እኛም በእነርሱ ሁኔታ ብንሆን የምናቀርበውን ተመሳሳይ አሳብ ነው፡፡  ታዲያ አንዳችን የአንዳችንን አሳብ እንዳንቀበል እና እንዳንተገብር የሚያደርገን የእይታ እጥረት ብቻ ነው፡፡ አንዳችን በአንዱ አሳብ መስማማት የማንችለው የራሳችንን አሳብ ብቻ ቅዱስ የሌላውን ሰው ሁሉ አሳብ እርኩስ የማድረግ ዝንባሌ ሲኖረን ነው፡፡

አሳባችንን ካቀረብን በኋላ ህሊና ያለው ሰው ይቀበለናል ብለን በራሳችን አሳብ ሃያልነት ማመን አለብን፡፡ ሰው ካልተቀበለው ደግሞ ዛሬ የተቀበሉት ሌላ የተሻለ አሳብ አለ ብለን ማመን ግድ ነው፡፡ ሁልጊዜ የራሱ አሳብ ተቀባይነት ካላገኘ አንድነትን ለማፍረስ ግድ የማይለው ሰው የአንድነት ጠላት ነው፡፡

እኛ ብቻ ህሊና እንዳለን ሌላው ሰው ሁሉ ህሊና እንደሌለው ማሰብ መጀመር የአንድነት ጠላት ነው፡፡ ከላእኛ በስተቀር ሌላውን ሁሉ እርኩስ ማድረግ የመከፋፈል የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡

አንድነት የልብ ስፋት ይጠይቃል፡፡ አንድነት በሌላው አሳብ የመመራት እምነት ይጠይቃል፡፡ አንድነት በራስ መተማመን ይጠይቃል፡፡ አንድነት በሌላው አሳብ ማመን ይጠይቃል፡፡ አንድነት በራስ አሳብ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ህይወት ውስጥ የእግዚአብሄርን አሰራር መረዳትን ይጠይቃል፡፡

ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡5

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

Thursday, July 27, 2023

በአንድ አሳብ ተስማሙ

በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 22-3

በአንድ አሳብ ተስማሙ የሚለው ትእዛዝ ለአእምሮ የሚከብድ ትእዛዝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን የማይቻል ትእዛዝ አያዘንም፡፡ በአንድ አሳብ መስማማት ይቻላል፡፡

በአንድ አሳብ ተስማሙ የሚለው ትእዛዝ የሚከብደን እኛ ጋር እውነት እንሰዳለ ስለሚመስለን እና አንድ ለመሆን እውነትን መተው እንዳለብን ስለሚመስለን ነው፡፡

ለአንድነት እውነትን መተው ትክክል አይደለም፡፡ ለአንድነት እውነትን መተው ማመቻመች እንጂ አንድነት አይደለም፡፡

በአንድ አሳብ መስማማት ማለት በእኔ ውስጥ አሳብ እንደመጣ ሁሉ በሌላው ሰው ውስጥ አሳብ ሎመጣ ይችላል ብለን የሌላውን አሳብ መቀበል ማለት ነው፡፡ በአንድ አሳብ የምንስማማው በሌላው ሰው አሳብ ተማምነን ሳይሆን "ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት" ላይ ተማምነን ነው፡፡

እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡1-5

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Wednesday, July 26, 2023

አድልዎ እና አንድነት አብረው አይሄዱም

በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡2-3

አንድነት የሚኖረው ሌላው የሌለውን ፍላጎት ልናሟላ ከመጣን ብቻ ነው፡፡ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያይ ችእና ለሌላው ጥቅም እውቅና የማይሰጥ ሰው አንድነት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ሰው በተፈጥሮው አድልዎ ሊኖርበት ይችላል፡፡ ሰው በተፈጥሮው ወገናዊ ሊሆን ይችላል፡፡ 

አድልዎ አንድነትን ያፈርሳል፡፡ አንዱን ከሌላው ከፍ አድርጎ ማየት የአንድነት ጠር ነው፡፡ አንዱን ከሌላው ዝቅ አድርጎ ማየት አንድነትን ይንዳል፡፡ ለሌላው ማድላት አንድነትን አያመጣም፡፡ ሌላውን መናቅ እና መጥላት አንድነት ያበላሻል፡፡

አድልዎን ማስወገድ ሰውን በእኩልነት ማየት አንድነትን ይገነባል፡፡ ሌላውን እንደራስ ማየት አንድነትን ይፈጥራል፡፡ ሌላውን በሰውነቱ መቀበል አንድነትን ያጠናክራል፡፡ በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ብቻ ፅኑ መሰረት አለው፡፡

በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡2-3

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Tuesday, July 25, 2023

አንድነት ከፍቅር ይመነጫል

መለያየት ከመምጣቱ በፊት ቀድሞ የሚመጣው ጥላቻ ነው፡፡ መለያየት ከመምጣቱ በፊት ቀድሞ የሚመጣው ንቀት ነው፡፡ ከምትጠላው ሰው ጋር አንድ ልትሆን አትችልም፡፡ ከምትንቀው ሰው ጋር አንድ ልትሆን አትችልም፡፡ ለጊዜው ልታስመስል ትችላለህ ነገር ግን ለሌላው ያለህን ንቀት እና ጥላቻን ልትደብቀው ግን አትችልም፡፡

አንድነት ከመቀበባል ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን በማንነቱ ከመቀበል ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን በእግዚአብሔር ፍጡርነቱ ከመቀበል ይጀምራል፡፡ አንድነት ሌላው በእግዚአብሔር መወደዱን ከመረዳት ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን እግዚአብሔር እንደሚያየው ከማየት ይመጣል፡፡ አንድነት እግዚአብሔር እርሱን ከሃጢያት ጥፋት እና ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ከመለያየት ለማዳን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን  እንደላከለት ከማየት ይመነጫል፡፡

አንድነት ሰው በክርስቶስ ያለውን የክብር ዋጋ ከመረዳት ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንደሚያየው ከማየት ይመጣል፡፡

ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Monday, July 24, 2023

አንድነት የትጉሃን ብቻ ነው

እኔ ከተረዳሁት ውጭ መረዳት የለም ፣ እኔ ካሰብኩት ውጭ ሃሳብ የለም ፣ እኔ ካየሁት ውጭ እይታ የለም የሚል አስተሳሰብ አንድነትን ይንዳል፡፡

እኔ ይህንን አይቻለሁ ከማለት ባሻገር አንተ ምን አየህ ብሎ የሌላውን እይታ በቅንነት ለመረዳት መሞከር ለአንድነት አንድ እርምጃ ነው፡፡

ነገሮችን ከሌላው ሰው ማእዘን በኩል ለማየት መሞከር አንድነትን ያመጣል፡፡ የራስን እይታ እንደ አንድ እና ብቸኛ እይታ አድርጎ ቀኑን ሙሉ ሌላውን ለማሳመን ብቻ መሞከር ይከፋፍላል፡፡ አንተ እንደተማመንከው ሁሉ እርሱም ይተማመናል፡፡ አንተ አሳብህ የተሻለ ሃሳብ ነው ብለህ በቅንነት እንዳሰብክ ሁሉ እርሱም የተሻለ አሳቡ የተሻለ አሳብ ነው ብሎ በቅንነት ያስባል፡፡ አንተ የተረዳሁት መንገድ ብቸኛው መንገድ ነው ብለህ እንዳሰብክ እርሱም እንዲሁ የተረዳው ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ያስባል፡፡ አንተ ሌሎቹ ሁሉ ተሳስተዋል ብለህ እንዳሰብክ ሁሉ እርሱም ሌሎቹ ሁሉ ተሳስተዋል ብሎ ያስባል፡፡

ሌላውን እንደራስ መቀበል ፣ ሌላውን እንደራስ ማክበር ፣ ሌላውን እንደራስ መረዳት አንድነትን ያመጣል፡፡

በራስ ማእዘን በኩል ነገሮችን ማየት ቅጽበታዊ ነው፡፡ ነገሮችን በራስ ማእዘን በኩል መረዳት ጥረት አይጠይቅም፡፡

በእኔም መንገድ ባንሄድ ነገር ግን በእርሱ መንገድ ብንሄድ ልንደርስ እንችላለን ብሎ ማሰብ አስተዋይነት ነው፡፡ እኛ ብቻ ሳንሆን ሌላው መልካም ሃሳብ ሊያመጣ ይችላል ብሎ ልብን ማስፋት አንድነት ነው፡፡ ፍቅር ራሱን እንደሚያምን ሌላውን ሰው ደግሞ ያምናል፡፡

ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡7

ራስን በሌላ ሰው ቦታ አስቀምጦ ነገሮችን ማየት ግን አንድነት ነው፡፡ ከእኛ የተለየን ሰው መስማት የተለመደ አይደለም፡፡ ከእኛ የተለየን ሰው ማክበር በቀላሉ አይመጣም፡፡ ከእኛ የተለየን ሰው እንደ ሰውነቱ መቀበል የአንድነቱ አንድ እርምጃ ነው፡፡

ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Sunday, July 23, 2023

አንድነት ሳይሆን ተመሳሳይነት ርካሽ ነው

አንድነት ሳይሆን ተመሳሳይነት ርካሽ ነው

አንድነት የተመሳሳይነትን ሙከራ አውጥቶ ጥሎ በአላማ አንድነት ላይ ማተኮርን ይጠይቃል፡፡

ተመሳሳይነት ርካሽ ነው፡፡ የሚመስሉንን ሰዎች ብቻ መቀበል ብርቅ አይደለም፡፡ ማንም መንገደኛ የሚመስሉትን ሰዎች ይሰበስባል ከእነርሱም ጋር ሊተባበር ይችላል፡፡

አንዳንድ ሰው አንድነት የሚለው መከፋፈልን ነው፡፡ እኛን የማይመስሉንን ሰዎች አውጥቶ መጣል መከፋል እንጂ አንድነት አይደለም፡፡

ስለዚህ ከእኛ የተለየውን ሰው ከህይወታችን አውጥተን መጣል እንደ አንድነት ጥረትን የማይጠይቅ ቀላል ነገር ነው፡፡ ማንም ሰነፍ ከእርሱ የተለየውን ሰው ከፊቱ አውጥቶ ይጥላል፡፡ ተመሳሳይነት ብዙም ጥረት አይጠይቅንም፡፡ ተመሳሳይነት ቅፅበታዊ ነው፡፡

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡46-48

አንድነት ግን ከመቀፅበት አይመጣም፡፡ አንድነት ለሰነፎች እና ለልፍስፍሶች አይደለም፡፡ አንድነት የልብ ስፋትን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ማስተዋልን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ትጋትን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ፍቅርን ይጠይቃል፡፡  

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Saturday, July 22, 2023

አንድነት የሚገለፀው በአላማ አንድነት ብቻ እንጂ በሌላ በምንም አይደለም

አንድነትን አንድነት የሚያደርገው የአላማ አንድነት ብቻ ነው፡፡ የተለያየ አሳብ ያለን ፣ የተለያየ ስጦታ ያለን ፣ የተለያየ ባህሪ ያለን የተለያየን ሰዎች ለአንድ አላማ መስራት እንችላለን፡፡

አላማችን አንድ እስከሆነ ድረስ ለአንድ መንግስት አላማ እንቆማለን፡፡ አላማችን አንድ እስከሆነ ድረስ በተለያየ ጦር ግንባር ብንዋጋም ለአንዱ መንግስት እንዋጋለን፡፡ አላማችን የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት እስከሆነ ድረስ የተለያየ ስጦታ ቢኖረንም ለአንድ መንግስት ጥቅም እንሰራለን፡፡

ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። የማቴዎስ ወንጌል 18፡20

ሁለት ወይም ሶስት የተለያዩ ሰዎችን አንድ በማድረግ በአንድነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈፅሙ የሚያደርጋቸው በስሙ መሰብሰባቸው ነው፡፡ በስሙ መሰብሰባቸው ፣ እርሱን ወክለው መሰብሰባቸው ፣ ለእርሱ ጥቅም መሰበስባቸው ፣ በእርሱ ቃል መሰብሰባቸው ፣ ለእርሱ መንግስስት አላማ መሰብሰባቸው ብቻ አንድ ያደርጋቸዋል፡፡

እግዚአብሔር ተመሳሳይ አድርጎ አልፈጠረንም፡፡ ልዩነታችን ውበታችን ጥንካሬያችን ነው፡፡ ልዩነታችንን የማይቀበል እና ተመሳሳይ ሊያደርገን የሚፈልግ ሁሉ አንድነታችንን እየናደው ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአንድ መንግስት የተለያየን ስራን እንድንሰራ የተለያዩ ሰዎች አድርጎ ፈጥሮናል፡፡ የእግዚአብሔር አላማ የእኛ ተመሳሳይነት ሳይሆን አንድነታችን ነው፡፡

ተመሳሳይነትን ከፈለግን ሰዎችን መቀበል ስለማንችል አውጥተን እንጥላቸዋለን፡፡ ተመሳሳይነትን ከፈለግን ሰዎችን በከንቱ እንጨፈልቃለን እንጂ የምናስበውን አንድነት ልናመጣ በፍፁም አንችልም፡፡ አንድነት እንዲመጣ ማንም ሰው መጨፍለቅ የለበትም፡፡ ሁሉንም ተመሳሳይ ለማድረግ በምናደርገው ሙከራ ሰውን በጨፈለቅን ቁጥር አንድነትን ከማምጣት ይልቅ አንድነትን እየበተንን ነው፡፡ ተመሳሳይነት በሰው ልብ እንጂ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ የሌለ የእውነተኛው አንድነት ማስመሰያ ቅጂ እንጂ እውነተኛው ኦሪጅናል አንድነት አይደለም፡፡

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Thursday, July 20, 2023

አንድነት ውጫዊ ተመሳሳይነት አይደለም

አንድነት ተመሳሳይነት አይደለም፡፡ አንድነት በአንድ ጣራ ስር መሰብሰብ አይደለም፡፡ አንድነት ተመሳሳይ ነገር ማሰብ እና ማድረግ አይደለም፡፡ አንድነት ተመሳሳይ ስጦታ መኖር አይደለም፡፡

አንድነትን በተመሳሳይነት መለኪያ ብቻ ከለካነው የማይደረስበት ህልም እናደርገዋለን፡፡ አንድነትን እና ተመሳሳይነትን ግራ ካጋባነው የአንድነት ነገር ተስፋ ያስቆርጠናል፡፡

ብዙ ሰዎች አንድ እየሆኑም አንድ እንደሆኑ የሚጠራጠሩት ስለዚህ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች አንድ ሆነው አንድ ለመሆን በከንቱ የሚጥሩት አንድነት እና ተመሳሳይነትን ግራ ስለሚያጋቡት ነው፡፡

ብዙ ሰዎች አንድ ሆነው በአንድነታቸው የማያርፉት እና የማይረኩት አንድነት ተመሳይነት ስለሚመስላቸው ብቻ ነው፡፡

አንድነት የሚጠይቀው አብሮ መሰብሰብን ሳይሆን የልብ አንድነትን ብቻ ነው፡፡ ምንም ያህል አብረው ቢሰበሰቡ የልብ አንድነት ከሌለ አንድነት የለም፡፡ የልብ አንድነት ካለ ደግሞ ሌላ ምንም አይነት ተመሳሳይነት ባይኖርም አንድነት አለ ማለት ነው፡፡

በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡46

በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ የሐዋርያት ሥራ 2፡1

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

አንድ የሚያደርገን

ከሚለያየን ነገር ይበልጥ አንድ የሚያደርገን ነገር ይበዛል፡፡ አንድ የሚያደርገን ላይ ካተኮርን አንድ የማንሆንበት ምንም ምክኒያት የለም፡፡

አንድ የሚያደርገን በእያንዳንዳችን ላይ ያለው የእግዚአብሔር አላማ ነው፡፡ አንድ የሚያደርገን የተሰጠን ተመሳሳይ ተልእኮ ነው፡፡ አንድ የሚያደርገን ለአንድ መንግስት መስራታችን ነው፡፡ አንድ የሚያደርገን አንድ ጦርነት መዋጋታችን ነው፡፡ አንድ የሚያደርገን የግብ አንድነታችን ነው፡፡

የእግዚአብሔር ነገር አንድ ካላደረገን ምንም ነገር አንድ ሊያደርገን አይችልም፡፡ የእግዚአብሔር ነገር አንድ ካደረገን ደግሞ አንድ ላንሆን አንችልም፡፡

በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡3-6

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Wednesday, July 19, 2023

አንድነትን የምንፈራው

ብዙ ሰው አንድ ለመሆን ይፈራል፡፡ የአንድነትን አሳብ በጥርጣሬ ይመለከተዋል፡፡

ብዙ ሰው አንድ ለመሆን የሚጠላበት ዋናው ምክኒያት አንድነትን ስለሌላው አሳብ የራስን አሳብ መጣል እንደሆነ ፣ አንድነት ስሌላው ፍላጎት የራስን ፍላጎት መተው እንደሆነ እና አንድነት ስለሌላው መረዳት የራስን መረዳት መተው እንደሆነ አድርጎ ስለሚወስደው ነው፡፡

እርግጥም አንዳንድ ሰዎች አንድነት የሚሉት ፍፁም የተሳሳተ አንድነት ነው፡፡ አንዳንዶች አንድነት አንድነት የሚሉት ለራሳቸው ጥቅም ስለማመቻቸት ብቻ እንጂ እውነተኛውን አንድነት ተረድተውትም አይደለም፡፡

እውነተኛው አንድነት ያስደስታል እንጂ አያስፈራም፡፡ እውነተኛው አንድነት ያኮራል እንጂ አያሸማቅቅም እውነተኛው አንድነት ፍሬያማ ያደርጋል እንጂ አያቀጭጭም፡፡ እውነተኛው አንድነት ያጠነክራል እንጂ አያደክምም፡፡

ማስመሰያው አንድነት ያለው እውነተኛው አንድነት ስላለ ነው፡፡ ማስመሰያው አንድነት አለ ማለት እውነተኛው አንድነት የለም ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ማስመሰያው አንድነት ካለ እውነተኛው አንድነት እንዳለ ማረጋጋጫው ነው፡፡ እውነተኛ ነገር ከሌላ የእርሱ ርካሽ ማስመሰያ አይሰራምና፡፡

በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡17

እውነተኛውን አንድነት መረዳት እና ራሳችንን መስጠት እንጂ ስለተሳሳተው የአንድነት አሳብ አንድነትን መፍራት የለብንም፡፡

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

Tuesday, July 18, 2023

አንድ መሆን ይቻላል

በእውነት አንድ መሆን ይቻላል ወይ? የሚለው ጥያቄ የሁላችንም ጥያቄ ነው፡፡ ሁሉም ሰው የራሱ ሃሳብ አለው፡፡ እውነት ነው ሰው የተያየ ነው፡፡ ሰው የተለያየ አሳብ ፣ የተለያየ መረዳት እና የተለያየ ፍላጎት እና አመለካከት ያለው የተለያየ ፍጡር ነው፡፡

አንድ የሆነው የተለያየ ሃሳብ ስለሌለን አይደለም፡፡ አንድ የሆነው የተለያየ የመረዳት ደረጃ እንዳለን ክደን አይደለም፡፡ ያለንን ልዩነት ክደን ልናደርገው የምንሞክረው አንድነት እውነታን የካደ ፣ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ እና ዘላቂነት የሌለው አንድነት ነው፡፡

አንዳንዶች እንደሚያስቡት አንድ ለመሆን ማንነታችንን መጣልም አያስፈልገንም፡፡

አንድ የምንሆነው የሚለያዩን ምክኒያቶች ስለሌሉ በፍፁም አይደለም፡፡

አንድ የሚያደርገን ከሚለያዩን ምክኒያቶች ይልቅ አንድ የሚያደርገዩን ምክኒያቶች ስለሚበዙ ብቻ ነው፡፡ አንድ የሚያደርግን ከሚለያዩን ምክኒያቶች  ይልቅ ስለሚከብሩ ብቻ ነው፡፡ አንድ የሚያደርግን ከሚለያዩን ምክኒያቶች  ይልቅ ስለሚገዝፉ ብቻ ነው፡፡

በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡3-6

Monday, July 17, 2023

ስለ አንድነት የተመለሰ ፀሎት

የእግዚአብሔር ፍፁም ፈቃድ አንድነታችን ነው፡፡

ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። የዮሐንስ ወንጌል 171120-23

ኢየሱስ የፀለየው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለሆነው ስለ አንድነታችን ነበር፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ "እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል" እንደሰማን ካወቅን እንደሚመልስ እናውቃለን እንደሚል የኢየሱስ በአብ ፀሎት ተሰምቷል ተመልሷልም፡፡

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15

በኢየሱስ ፀሎት ወደጥንቱ እና እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወደ አቀደው ወደ አንድነታችን ተመልሰናል፡፡

አንድ ነን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር