እንግዲህ
በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ኤፌሶን 4፡1
እግዚአብሄር ለክብሩ ፈጥሮናል፡፡ ወደዚህ መደር
ከመፈጠራችን በፊት በምድር ላይ እንድናደርገው የታቀደው ነገር ስለነበረ ወደዚህ ምድር ተፈጥረናል፡፡ ወገጌታ መነግስት ከመጣረራታችን
ባሻገር እንወቀውም አንወቀውንም ወደምድር የመጣንበት ምክኒያት አለ፡፡ እያንዳንዳችን በምድር ላይ ልንሰራው የሚገባው ስራ ወይም
ጥሪ አለን፡፡
በራሳችን አነሳሽነት ለእግዚአብሄር ምንም ነገር
ከማድረጋችን በፊት ጥሪዬ ምንድነው ብሎ መጠየቅ ወሳኝ ነው፡፡ በምድር ላይ ያለን ህይወት አንድ ህይወት ነው፡፡ ይህንን ህይወት
እግዚአብሄር ለጠራን መጠቀም ብልህነት ነው፡፡ ይህን ህይወት እግዚአብሄር ላልጠራን ነገር ላይ ማዋል ብክነት ነው፡፡
የአካል ብልቶቻችን እያንዳንዳቸው የተለየ ስራና
ጥሪ እንዳለቸው ሁሉ እያንዳንዳችን በምድር ላይ እንድንሰራው የተላክነው የተለያየ ስራና ጥሪ አለን፡፡ ያንን ጥሪ ማግኘትና መከተል
የእኛ ሃላፊነት ነው፡፡
ጥሪ ከጎረቤት አይኮረጅም፡፡ ጥሪ የሚገኘው ከጠራን
ከእግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሀር ለእያንዳንዳችን ጥሪ አለው፡፡ የእኛ ሃላፊነት እግዚአብሄን መፈለግና ጥሪያችንን ማወቅ ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤
ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርሚያስ 29፡11-13
በምድር ላይ ያለሁት ለምን አላማና ጥሪ ነው?
ብሎ መጠየቅ ፣ ጥሪን አውቆ በትጋት መከተል ከምንም ነገር በላይ ስኬታማ ያደርገናል፡፡
ጥሪያችንን
ስንከተል ከጥሪያችን መንገድ ሊስወጡ የሚመጡ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ይገጥሙናል፡፡ የጥሪያችን አንዱ ክፍል ነውና እንታገሰዋለን፡፡
የተጠራችሁለት
ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡21
ከጥሪያችን ውጭ መኖር ምንም ዋስትና የለንም፡፡
በጥሪያችን ላይ መኖራችን ግን ክፉ ነገር እንኳን ቢሆን ለመልካምነታችን እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡
እግዚአብሔርንም
ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
ሰዎች
ከተለያየ ቦታ ሽልማትን ያገኛሉ፡፡ ከእግዚአብሄር የሆነ ሽልማት ያለው ጥሪን በመከተል ውስጥ ብቻ ነው፡፡
በክርስቶስ
ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡14
የጠራንን
ጥሪ ለማድረግ ስንተጋ እርሱ የእኛን ነገር ለመስራት ታማኝ ነው፡፡
የሚጠራችሁ
የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡24
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ
#ጌታ #ጥሪ #ምስክር #ፀጋ #ምናን ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment