Popular Posts

Monday, March 14, 2022

The most important things in life are free


The most important things in life are free.

Many people exaggerate money. They gave it higher value than it ought to have.  They expect more than it can offer. They are disappointed when money fails to meet their expectations. Money is limited in many ways. There are still some things money can’t buy. There are many things money can buy. But there are things that can’t be bought with money. Love, satisfaction, joy, fulfillment, hope, friendship can’t be bought with money. They are given. They are gifts from God and men. Looking for the right thing in the right place saves us from disappointment and helps us achieve our goal. 

Failing to understand the great value of free gifts, people tend to change  the more valuable things for cheap substitutes. 


 

Friday, March 11, 2022

የእግዚአብሄር ቃል ብቸኛ አማራጭ

 


የህይወት ስኬት የሚመጣው ለእግዚአብሄር ቃል የመጀመሪያውን ስፍራ በመስጠትና በቃሉ ከባቢ ውስጥ ለመኖር በመወሰን ነው፡፡

ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።          እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙረ ዳዊት 1:1-3

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡8

የእግዚአብሄር ቃል ብቸኛ ተስፋችን ነው፡፡ ህይወታችን ከተለወጠ የሚለወጠው በእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ዕብራውያን 4፡12-13

ስለዚህ ነው ለእግዚአብሄ ቃል በህይወታችን የመጀመሪያውን ስፍራ የምንሰጠው፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የሙጥኝ የምንለው ስለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ነው በምናደርገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር ቃል ከባቢ ውስጥ መኖርን የምንፈልገው፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ከባቢ ውስጥ በፍፁም መውጣት የማንፈልገው የተፈጠርንበትን አላማ መፈፀም የምንችለው በቃሉ አማካኝነት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡  

እግዚአብሄርን በህይወታችን ብቸኛ አማራጭ ለማድረግ በህይወታችን የእግዚአብሄርን ቃል ብቸኛ አማራጭ ማድረግ ይጠይቃል፡፡

እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡4-9

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #ጥርጥር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ